ሐዋርያዊ መልሶች - Apostolic Answers

ማን ነን..??
በእግዚአብሔር አብ ፍቅር በወልድ ደም በመንፈስ ቅዱስ አሰራር በተመሰረተችው አንዲት፣ ቅድስት፣ አለም አቀፋዊት እና ሃዋርያዊት በምትሆን ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እየተማርን የምናስተምር ክርስቲያን ወንድሞች ነን።

ቻናሉ አጠቃላይ ይዘቱ ምን ይሆናል..??
በዋናነት ዕቅበተ እምነት ላይ የምናተኩር ሲሆን ከሙስሊሞች እና ከፕሮቴስታንቶች ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ መመለስ.. እንዲሁም ፈቃዳቸው ቢሆን እያመጣን የቀጥታ ውይይቶችን ማድረግ። ከዚህ ባለፈ ተከታታይ መሰረታዊ የዶግማ ትምህርቶችን መስጠት እና እናንተ ክርስቲያኖች ጥያቄ የሚፈጥርባችሁን ነገሮች ከእናንተው በቴሌግራም በኩል በመቀበል አጫጭር ቪዲዮዎችን በእነሱ ላይ ማዘጋጀት እንዲሁም ክርስቶስን በመምሰል ሕይወት ውስጥ ከማደግ ጋር በተያያዘ መንፈሳዊ ትምህርቶችን ማቀበልና የመሳሰሉትን ይይዛል።

አላማችን..??
ዋናው አላማችን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን አጋዥ በማድረግ ክርስቲያን ወንድም እህቶቻችንን በእምነት ማጽናትና እነርሱም እምነታቸው በደንብ ገብቷቸው በእምነታቸው እየኖሩ ለሌላውም መድረስ እንዲችሉ ማድረግ ሲሆን እንዲሁም በሩቅ ያሉትን ከቤቱ የጠፉትን በጎች ደግሞ መመለስ ነው።

ለእናንተ፡
ይህ ቻናል ጠቃሚ ነው ብላችሁ የምታምኑ ክርስቲያኖች ሁላችሁ በጸሎት እንድታስቡን እንዲሁም ይህንን ቻናል ሰብስክራይብ አድርጎ ሼር በማድረግና ለሌሎች ወንድም እህቶቻችንም በማድረስ ታግዙን ዘንድ ያስፈልገናል።

እግዚአብሔር ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቅ.. አሜን።