Paulos Fekadu

Paul's Pulpit (ምስባከ ጳውሎስ) የጳውሎስ ፈቃዱ አገልግሎት ነው፤ እንዳስፈላጊነቱ ሌሎች የአገልግሎት ተባባሪዎችም ይኖሩታል። “ምስባከ ጳውሎስ” በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጭ የሚገኙ ክርስቲያኖችና አብያተ ክርስቲያናት በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ዕውቀት እንዲጎለብቱ መትጋትን በዓላማነት አንግቧል።

ይህንም ከግብ ለማድረስ የሚያቀርባቸው ዝግጅቶች የሚከተሉት ናቸው፤

• ትምህርታዊ ስብከቶች፣
• የክርስትና መሠረታውያን፣
• የጠንካራ ምንባባት ትርጓሜ
• ነገረ መለኮት
• ዕቅበተ እምነት
• ጥሞና
• ጥያቄና መልስ
• ልዩ ልዩ ጽሑፎች።

“ምስባከ ጳውሎስ” ዩቲዩብን፣ ቴሌግራምን፣ ፌስቡክንና እንዲሁም ዘመኑ ያመጣቸውን ሌሎች የቴክኖሎጂ አማራጮች ለመልእክቱ ማድረሻነት ይጠቀማል።

ለበለጠ መረጃ በሚከተሉት አድራሻዎች ይጠቀሙ፡-

Telegram:- @poyefekadu
ኢሜይል፡- [email protected]