Bible Connected

እንኳን ወደ Bible Connected ቻናል በሰላም መጡ!
ይህ ቻናል ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ ድረስ የቅዱሳት መጻሕፍትን ታላቅ እና ወጥ የሆነ ታሪክ የሚቃኝበት ቦታ ነው። በሚተላለፉት ጥናቶች ወስጥም ዋናው ፍላጎታችን በተቻለ መጠን፥ የሰው ፍልስፍናዎችን ወይም አስተሳሰቦችን ሳንጨምር መጽሐፍ ቅዱሱ የሚያስተምረው ላይ ማተኮር ነው። በእዚህ ሰፍራ ብሉይ ኪዳን እና አዲስ ኪዳን እንዴት እንደሚያያዙ እንመለከታለን፣ መጽሐፍ ቅዱስ ከመጀመሪያው ፍጥረት እስከ አዲስ ፍጥረት ድረስ ያለውን የእግዚአብሔርን ዓላማ እንዴት እንደሚተርክ እንመለከታለን፣ ይህም ሁሉ ተያይዞ ከህይወታችን ጋር ያለውን ተዛምዶ የምንመለከት ይሆናል፡፡

ለመጽሐፍ ቅዱስ አዲስ ከሆኑ ወይም ለዓመታት አጥንተውት የሚያውቁ ቢሆንም፣ መረዳትዎን ለማጎልበት እና ከእግዚአብሔር ጋር የሚያደርጉትን ጉዞ ለማጠናከር አስፈላጊ ግብዓቶችን እዚህ ቻናል ውስጥ ያገኛሉ።

ዋና አዘጋጅ ሳሙኤል አክሊሉ