Arta'i - TV

አርታኢ ቲቪ - Arta'i - TV (በጋዜጠኛና አርታኢ መልዓከ ተሰማ)

አርታኢ ቲቪ እንደ አንድ ማኅበራዊ ሚዲያ የመረጃ ማእከል በመኾን ማሳወቅ፣ ማስተማር እና የማዝናናት ተልዕኮን ያነገበ ቻናል ነው።

በዚህም፣በማኅበራዊ ጉዳዮች፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ጤና፣ትምህርትና የኪነጥበብ ስራዎች ላይ በማተኮር ፕሮፌሽናል በሆነ መንገድ በልዩነት ለሚዲያ ልዕልና በነጻነት በመስራት ማኅበረሰብን በታማኝነት ያለገደብ ያገለግላል።

በፕሮግራሙ የስርጭት አድማሱም ፍጹም ከወገንተኝነት የፓለቲካ አመለካከት፣ የብሔር ልዩነት እና ሃይማኖት የጸዳ፣በየትኛውም ዘውግ ማኅበራዊ ሕጸጽን በመንቀስ ጭምር የመረጃ ፍሰትን ያሳልጣል!
ሚዛናዊ በመኾን ለእውነትና እውነት ይተጋል!

መረጃ ለእውቀት፣ ለአእምሮ ማበልጸግያ እና የመዝናኛ ግብዓት ሲኾን ጤናማ ትውልድን መገንባት ያስችላል። በዚህም ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍል ተደራሽ በማድረግ ፣በቀጣይ ዐምስት ዓመታት በ2022 ከሀገራችን አልፎ በምስራቅ አፍሪካ ተጽዕኖ መፍጠር የሚችል የሚዲያ ተቋም ለመኾን ርእይ ያነገበ ቻናል ነው።