Yegna Maed #የኛ ማዕድ

Hey everyone,welcome to this channel My Name is Yegna Maed.I am from Ethiopia I am a wife,mother and YouTuber.I created this youtube channel to make friends all over the world and to create my own positive vibes.there is no room for negativity and haters .

ሰላም ለሁላችሁም ስሜ የኛ ማዕድ ይባላል የመጀመርያ ድግሪዬን በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ በጋዜጠኝነት በተለይም በፕሪንት እና ዌብ ጋዜጠኝነት ሰርቻለሁ ከዛም በመቀጠል ላለፉት ስምንት አመታት በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከጀማሪ ሪፖርተር እስከ ኤዲተር ሰርቻለሁ።

በስራ አለም ባሳለፍኩት ግዜያት በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዉስጥ ለአምስት አመታት የዉጭ ቋንቋዎች ሪፖርተር ሆኜ የሰራዉ ሲሆን ለሶስት አመታትም የማህበራዊ ሚዲያ አዘጋጅ በመሆን በተለይ ፌስቡክ፣ ዩቱብ፣ዌብሳይት እና ቲዉተር ገጾችን ማስተዳደር፣ማሳደግ እንዲሁም የይዘት ስራዎች ላይ ሰርቻለሁ።

ባሳለፍኩት የስራ ህይወቴ የማህበራዊ ሚድያ እንዴት ከዜሮ ጀምሮ ማሳደግ እንደሚቻል።የስራ ሀሳብ አመራረጥ እንዲሁም ማህበራዊ ሚዲያን ተጠቅሞ ራስን ማሳደግ እንደሚቻል ተምሬበታለሁ።

አሁን በዚህ የዩቱብ ቻናል በተለይ ለጀመሪ ዩቱበሮች በትምህርት አለም ባገኘዉት እዉቀት፣በተለያዩ ስልጠናዎች ባዳበርኩት ልምድና በስራ አለም ከስራዬ ባከበትኩት ልምድ ካለኝ ሳልሰስት እዉቀቴን ለማካፈል ወደናንተ መጥቻለሁ።

ጀማሪ ዩቱበሮች ይሄ ቻናል ለናንተ የተከፈተ በመሆኑ ስለዩቱብ የምሰጣቸዉን ትምህርቶች በአጫጭር ቪድዮና በቀጥታ ልትከታቱሉ ትችላላቹ።