yekidusan zekere የቅዱሳን ዝክር

ይህ የእኔ የመጋቢ በረከት አሮን የግሌ መንፈሳዊ ትምህርት,ገድላት ድርሳናት እና ስንክሳር እንዲሁም ዝማሬዎችን የማስተላልፍበት የዩቱብ ቻናሌ ነው።
❤️የቅዱሳን መታሰቢያ ለበረከት ነው❤️
ወገኖቼ ዛሬ የተሰጠን አንደበት ነገ በመቃበር ይዘጋል ፤ ዛሬ የምናወራበት ምላስ ነገ በአፈር ይታሰራል ፤ ቀኑ አጥሮብን ሌሊቱንም የምንራወጥበት እግርም በሳጥን ይገደባል፤ በትንሹ የግንባር ሜዳ ላይ የተሰቀሉት ዐይኖቻችን በአራቱም የዓለም ማዕዘናት እንዳልቃኘንበት በአስከሬን ሳጥን ዉስጥ ዉሃ ሆነው ስም አጠራራቸው ይጠፋል። እንግዲህ ሁሉም ነገር መጨረሻው እንዲህ ከሆነ ዛሬ አንደበታችን መልካም ነገር ይናገር፤ ምላሳችንም የምስራቹን ቃል ይመስክር። መሞታችን ካልቀረ ዘንድ ቅንና መልካም ሰዎች ሆነን እንሙት፤ ለቅኖችና ለመልካሞች ከሞት በኋላ ትንሣኤ ከመቃብር በኋላ ሕይወት ለእነርሱ ይሆናልና። በየዕለቱ ተከብረው የሚውሉትን የቅዱሳን መለአክትን ድርሳን እና የቅዱሳን ጻድቃን ሰማዕታትን ገድል የማቀርብበትን ቻናል ነው እንድትደግፉኝ በእግዚአብሔር ስም እጠይቃለሁ አመሰግናለሁ::
❤️መልካም ነገሮች የሆኑትን ሁሉ የማስተላልፍበት እንደሆነ ስገልጽላችሁ በደስታ ነው። ❤️
📍👉ሰብስክራይብ፤ ሼር፤ ላይክ ( subscribe, share and like ) እንድታደርጉ በክርስቶስ ስም እጠይቃለሁ