DYKKG EOTC
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በሰሜን አሜሪካ፣ ሰሜን ካሊፎርኒያ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት የደብረ ይባቤ ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የቀጥታ ስርጭት ማስተላለፊያ ድህረ ገጽ ነው !
አድራሻችን፡ 587 N 6th St, San Jose, CA 95112።
በዚህ መድረክ፣ የጌታችንና የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል ለትውልድ ይሰበካል። ይህ ድህረ ገጽ የሚያስተላልፈው መልእክት ሰማያዊና መንፈሳዊ ብርሀን ሲሆን፣ ለእርስዎም ሆነ ለሁሉም በረከት ያለው ነው። ስለዚህ፣ ይህ መልእክት እንዳያመልጥዎ፣ ለሌሎችም እንዲዳረስ፣ በመመዝገብ (subscribe) የድህረ ገጻችን ውድ አባል ይሁኑ። እንዲሁም ይህን መልካም ዜና ለወዳጅዎ እና ለቤተሰብዎ በማካፈል (share)፣ ሰዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያድርጉ።
የመረጃ ክፍላችን ይህን አገልግሎት በተሻለ መልኩ እንዲቀጥል፣ በጸሎታችሁ እንድታስቡን ተማፅነን እንጠይቃለን። ከዚህ በላይ፣ ይህን ተግባር ለማጠንከር በሃሳቦችዎ፣ በመገልገያዎች፣ ወይም በማንኛውም መንገድ መደገፍ ከፈለጉ፣ የአስተዳደር ክፍላችንን በማነጋገር የዚህ ቸር ሥራ ተካፋይ ይሁኑ። እንኳን ወደዚህ መንፈሳዊ ቤተሰብ በደህና መጡ!