Kitfo Pizza ክትፎ ፒዛ
Автор: Melegna | መለኛ
Загружено: 2024-09-17
Просмотров: 4207
ክትፎ ፒዛውን ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ ግብዓቶች አይነት ፣ መጠን እና የቅመሞች ዝርዝር
ይህ ከስር ያስቀመጥንላችሁ ዝርዝር ብዛት ለ3 ክትፎ ፒዛዎችን ለማዘጋጀት የሚረዳችሁ ነው፤ ነገር ግን አነስ አድርጋችሁ ማዘጋጀት ፈልጋችሁ የግብዓት መጠኑን መቀነስ ይኖርባችሃል፡፡
1. ጎመን ክትፎውን ለማዘጋጀት
የጎመን መጠን 1 እስር የሃበሻ ጎመን
አስቀድማችሁ ጎመኑን በደንብ ማራገፍ ፣ ግንዱን መቀንጠስ እና በሚገባ ውስጡን እየከፈታችሁ ማጠብ ይኖርባቹሃል
ሰፋ ባለ ድስት ጎመኑን ለ1 ሰዓት ያህል ወይም ውሃውን እስኪጨርስ ድረስ መቀቀል
በቢላ ፣ በጭማቂ ወይመ በሽንኩርት መፍጫ ላም እስኪል መፍጨት
ጎመኑን ለመጥበስ፡
1 ቁንጥር የተፈጨ አብሽ መጥበሻ አግሎ ሞቅ ማድረግ
2 ጠብታ ውሃ ጠብ አድጎ ማማሰል
5 የሾርባ ማንኪያ የቀለጠ የተነጠረ ቂቤ መጨመር
1 የብና ማንኪያ ኮረሪማ ማድረግ
የምድጃችሁን የሙቀት መጠን ትቀንሱ እና የፈጫችሁት ጎመን ጨምራችሁ ማላወስ
የምትፈልጉትን ያህል ጨው መጨመር
2. ክትፎውን ለማዘጋጀት
300 ግራም የክትፎ ቀይ ስጋ
ስጋውን በላስቲክ በደንብ አስራችሁ እታቹን በሹካ ወጋ ወጋ ታደርጉት እና ጎድጓዳ ሳሃን ላይ ከላዩ ተለቅ ያለ እቃ ጭናቸሁ ደሙ እንዲወጣ ከ30-45 ደቂቃ መተው
1 የቡና ማንኪያ ኮረሪማ
ግማሽ የሾርባ ማንኪያ ሚጥሚጣ
1 ቁንጥር ጨው
የምትፈልጉትን ያህል የቀለጠ ቂቤ
3. አይቡን ለማዘጋጀት
300 ግራም ነጭ አይብ
አይቡ በማንኪያ ዘርዘር ታደርጉ እና
1 የቡና ማንኪያ ኮረሪማ
ግማሽ የሾርባ ማንኪያ ሚጥሚጣ
4 የሾርባ ማንኪያ የቀለጠ የተነጠረ ቂቤ ጨምራችሁ ቀለሙን እሰኪቀይር ድረስ ማሸት
ግማሽ የቡና ማንኪያ ኮረሪማ መጨመር
1 የሾርባ ማንኪያ ሚጥሚጣ መጨመር
የምትፈልጉትን ያህል ጨመው መጨመር
8 የሾርባ ማንኪያ የቀለጠ ቂቤ ከላይ መጨመር
4. ጥብሱን ማዘጋጀት
300 ግራም የጥብስ ስጋ ለአበላል እንዲመች በትንንሹ መክተፍ
1 ፍሬ ቃሪያ እና ሽንኩርት መክተፍ
ምድጃችሁ ላይ መጥበሻ አግላችሁ ዘይት መጨመር
በዘይቱ ፈንታ ስጋው ላይ ሞራ ካለው እሱን መጠቀም ትችላላችሁ
5 ፍሬ በቀጭኑ የተከተፈ ነጭ ሽንኩርት ጨምራችሁ መጥበስ
ስጋውን ጨምሮ ቀለሙን እኪቀይር ድረስ መጥበስ
በቡና ማንኪያ ልኬት ግማሽ ከሙን ፣ ሮዝሜሪ ፣ ቁንዶ በርበሬ እና ጨው መጨመር
የምትፈልጉትን ያህል ቂቤ መጨመር
ሽንኩርት እና ቃሪያውን ጨምሮ ሞቅ ማድረግ
የፒዛ ቂጣውን ለማዘጋጀት ከዚህበፊት ያዘጋጀነውን ቪዲዮ ተመልከቱ • Pizza Dough Recipe የፒዛ ቂጣ
የፒዛ ስልሱን ለማዘጋጀት ከዚህ በፊትያዘጋጀነውንቪዲዮ ተመልከቱ
• Pizza Sauce የቲማቲም ስልስ ለፒዛ
ፒዛው ከመጥበሻው ጋር እንዳይያያዝ እንዲሁም ጀርባው በደንብ እንዲጠበስ ዘይት መለወስ
የማባያ ስልስ
የቃሪያ ስልስ • Ethiopian Chilli Sauce የቃሪያ ስልስ
ዳጣ
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: