ስምህን እንባርካለን Dawit Getachew @ Ketena Hulet Mulu Wongel Church Amnihalehu Concert April 2022
Автор: Dawit Getachew
Загружено: 2023-01-05
Просмотров: 309483
ስምህን እንባርካለን
ሁሉን የምትችል የዘላለም ንጉስ እግዚአብሔር
ያለህ የነበርህ ወደፊትም የምትኖር
ታላቅነት ሞገስ የሚገባህ ምስጋና ክብር
ሀይል ጥበብ ብርታት መንግስት ያንተ ነው በሰማይ በምድር
ስምህን እንባርካለን(2)
እግዚአብሔር አዳኝነትህን ዘውትር እንወድሳለን
በቅዱሱ ክንድህ አስመልጠኸናል
በድንቅ በተአምራት ማዳንህን አይተናል
ጸጋ ባያግዘን ፍቅርህ ባይዘን
ምህረትህ ደግፎ እዚህ ባያደርሰን
በጠፋን ነበረ አንተ ባትደርስልን
ግን ምህረት ቸርነትህ በቤትህ አቆመን
በጠፋን ነበረ አንተ ባትደርስልን
ግን ምህረት ቸርነትህ በህይወት አኖረን
ሁሉ ካንተ በአንተ ለአንተ ነው እኛ ምን አለን
የተቀበልነውን ከደጉ እጅህ እንሰጥሀለን
ስለቸርነትህ ሰላደረክልን ምን እንከፍላለን
እግዚአብሔር ሆይ ስምህን ለዘላለም አንባርካለን
ስምህን እንባርካለን(2)
እግዚአብሔር አዳኝነትህን ዘውትር እንወድሳለን
ከድቅድቅ ጨለማ ወደሚደነቅ ብርሀን
በምህረት አምልጠን ካህናት ያደረከን
በኃያሉ ክንድህ አምልጠናልና
ዘውትር እንሰዋለን ለስምህ ምስጋና
በጠፋን ነበረ አንተ ባትደርስልን
ግን ምህረት ቸርነትህ በቤትህ አቆመን
በጠፋን ነበረ አንተ ባትደርስልን
ግን ምህረት ቸርነትህ በህይወት አኖረን
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: