በቤት ውስጥ ሚዘጋጅ የስጋ ከባብ //Homemade Kebab || Special Kebab Cooking Amii Fofana
Автор: DIY Ethiopian
Загружено: 2020-07-28
Просмотров: 1088
#ከባብ ላህም
ለመስራት ሚያስፈልገን :-
1#ስጋ
2 #ቀይ ሽንኩርት አንድ ራስ
3 #ቲማቲም
4 #የፈረንጅ ቃሪያ
5 #በቅዱኒስ
6 #የቲማቲም ድልህ
ቅመማ ቅመም :-
1 #ድብልቅ ቅመም
2#ቀረፋ
3 #ቁንደበርበሬ
ተጨማሪ :-
#ፍርኖ ዱቄት እና የተፈጨ ደቃቅ #ጨው
በሽንኩርት መክተፊያ ማሽን አንድ ቲማቲም፣ አንድ ሽንኩርት ፣ አንድ ቃሪያ በደቃቁ ከተፍኩ ።
በወንፊት አጠለልኩት ያለለልነውን ውሃ ለብቻ እናስቀምጥና ከላይ ወንፊቱ ላይ ያለውን የተፈጨ ስጋ ላይ በማድረግ እንጨምራለን።
በቅዱኒስ፣ ፍርኖ ዱቄት ቅመማቅመም እና ጨው የቲማቲም ድልህ ጨምረን በደንብ እንለውሳለን።
የቲማቲም ድልህ ከሌለ ወይም መጨመር ካልፈለጋችሁ ፍልፍል አህማር ( በርበሬ ) መጨመር ይቻላል ።
ኦቩ በመጀመሪያ ለ አስር ደቂቃ ከታች ለኩሳችሁ አሙቁት ።
በረዶ የሰራውን ከባብ የጋለው ኦቭን ውስጥ ካደረግን በኋላ ከታች ሲበስል እንደመቅላት ሲል ከታች የለኮሳችሁትን አጥፍታችሁ ከላይ ለኩሱ ስታቀርቡ ትኩሱን አቅርቡ።
ወዲያው ማይበሉ ከሆነ ከድናችሁ አስቀምጡት እንዳይደርቅ። መብላት ስትፈልጉ በማይክሮዌቭ አሙቁት ትኩስ ይሆናል ።
ኦቭን ከሌላችሁ በመጥበሻ ላይ ትንሽ ዘይት አድርጋችሁ በማይዝ መጥበሻ ልብ ልብ አርጉት ምርጥ ነው።
ስጋው እኔ የተጠቀምኩት የበግ አንድ እጅ እና የበሬ ሁለት እጅ የተፈጨ ስጋ ነው። የተፈጨ ስጋ ቢሆንም መልሼ በሽንኩርት መክተፊያ ማሽን ደግሜ ፈጭቼዋለሁ ላም እንዲል በተጨማሪም ጮማ ስጋ ለብቻ ፈጭቼ ጨምሬበታለሁ ።
የበግና የበሬ ስጋ ማደባለቅ ለጣእሙ አሪፍ ነው።
ጥሬ ስጋ አስቆርጣችሁ እምትፈጩ ከሆነ ይበልጥ ቆንጆ ነው ።
በዚህ የከባብ አሰራር ላይ ጮማ ስጋ መኖሩ ጥቅሙ ከባቡ እንዳይደርቅ ልስልስ ያለ እና ወዛም እንዲሆን እንዳይደርቅ ያደርገዋል
የፍሮ ዱቄቱ ጥቅም ደሞ ስጋው በጣም ላም ተደርጎ ስለተፈጨ እንዳይቀጥን ቅርፅ ስናወጣ አልያዝ እንዳይለን ነው። ስለዚህ ዱቄት አታብዙ ከበዛ ያደርቅብናል እጃችሁ ላይ ስጋው ከተያዘላችሁ ፍርኖዱቄቱ ብዙ አስፈላጊ አደለም።
ካዘጋጃችሁ በሁዋላ እከፈለጋችሁበት ቀንና ወር ፍትህ ውስጥ ማለትም በረዶ ቤት ማስቀመጥ ይቻላል ከዛ በምትፈልጉበት ቀን ቀደም ብላችሁ ከፍሪጅ በማውጣት መጠቀም ትችላላችሁ።
ታርዲያ በመጀመሪያ በረዶ እስኪሰራ ጠብቃችሁ ከዛ ነው ክዳን ባለው እቃ ከባቡን ምታስቀምጥቱ ማለትም መጀመሪያ በረዶ ይስራ ካለዛ እርስ በእርስ ይጣበቃል ። በሌላ ግዜ የዶሮ ስጋከባብ ይዤ እመጣና የስጋውንም ደግሜ ሰርቼ አሳያችሁኋለሁ በዚህ ፊድዮ ፈጠንኩ መሰለኝ ይቅርታ ቪድዮ እንዳይረዝምባችሁ ብዬ ነው እንጂ ለኔ ሚጠቅመኝ ቪድዮው ሲረዝም ነው።
ላይክ ሼር በማድረግ አበረታቱኝ በቀጣይ አዳዲስ የ አረብ ሃገር ምግብ እንዲደርሳችሁ ሰብስክራይብ ያላደረጋችሁ ሰብስክራይብ አድርጉና ቤተሰብ እንሁን እንዲሁም የደውል ምልክቱን መጫን አትርሱ ! God Bless you all !
#ከባብ #Kebab #ስጋ
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: