🛑 ፍትህ ለአማራ ክልል ሙስሊሞችና ለአክሱም ከተማ ነዋሪዎች | እዉነት ተቻችለን የምንኖረው ወይስ ሙስሊሙ ችሎ ነው | የሀጂ ዑመር ሞት ያን ያህል ሊከፋፍለን
Автор: Ehtio Z Islam
Загружено: 2025-10-23
Просмотров: 662
አሜሪካ በኢትዮጵያ የሚገኙ ዜጎቿ የአገሪቱን ህግ አክበረው እንዲንቀሳቀሱ አሳስበች።
" ኢትዮጵያ ውስጥ በምትቆዩበት ጊዜ በህጋዊ ሁኔታ መቆየት በጣም አስፈላጊ ነው " ብላለች።
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ምን አሉ ?
" በኢትዮጵያ የምትገኙ አሜሪካውያን ሁሉ የኢትዮጵያን የኢሚግሬሽን ደንቦች እንድታከብሩ እና ቪዛዎቻችሁን እና/ወይም የመኖሪያ ፈቃዶቻችሁን ጊዜ ከማለፉ በፊት እንድታሳድሱ አሳስባለሁ።
በህዳር 2017 (እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር) የኢትዮጵያ መንግስት የቪዛ ጊዜ አሳልፎ መቆየትን እና ህገወጥ ስደትን ለመቀነስ ሲል የቪዛ ጊዜ አሳልፎ የሚቆይ ግለሰብ የሚጣልበትን የገንዘብ ቅጣት በአንድ ቀን ወደ 30 የአሜሪካ ዶላር አሳድጓል፤ ይህም በፍጥነት ሊጠራቀም የሚችል ነው።
የኢትዮጵያ ኢሚግሬሽን ባለስልጣናት ቪዛ አሳልፎ በመቆየት የገንዘብ ቅጣት ያለባቸው የአሜሪካ ዜጎች ዕዳቸውን ሙሉ በሙሉ በዶላር እስኪከፍሉ ድረስ ከአገር እንዳይወጡ ለመከልከል እንደሚችሉ እባክዎ ልብ ይበሉ።
የአሜሪካ ኤምባሲ ቪዛ አሳልፎ በመቆየት ምክንያት የሚጣለውን የገንዘብ ቅጣት ለመክፈል ብድር የመስጠት ፍቃድ ከአሁን በኋላ የለውም።
ስለዚህ በኢትዮጵያ ለቱሪስት ቪዛ ከሚፈቀደው 30 ወይም 90 ቀናት በላይ መቆየት ከፈለጉ ቪዛዎ ከማብቃቱ በፊት ከኢትዮጵያ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤት የቪዛ ማራዘሚያ ወይም የመኖሪያ ፈቃድ (በተለምዶ “ቢጫ ካርድ” የሚባለውን) ይጠይቁ።
እዚህ ኢትዮጵያ የተወለዱ እና የአሜሪካን ፓስፖርት እንደ ብቸኛ መታወቂያቸው የሚጠቀሙ ልጆችን ጨምሮ የውጭ ፓስፖርት ያላቸው ሁሉም ልጆች ለቪዛ አሳልፎ የመቆየት ቅጣት ተገዢ ናቸው። ስለዚህ እባክዎ በኢትዮጵያ የሚገኙ የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ልጆች የአሜሪካ ፓስፖርታቸው ውስጥ የፀና የኢትዮጵያ ቪዛ ወይም “ቢጫ ካርድ” እንዳላቸው ያረጋግጡ።
በኢትዮጵያ የምትገኙ አሜሪካውያን ሁሉ የኢትዮጵያን የኢሚግሬሽን ደንቦች እንድታከብሩ እና ቪዛዎቻችሁን እና/ወይም የመኖሪያ ፈቃዶቻችሁን ጊዜ ከማለፉ በፊት እንድታሳድሱ አሳስባለሁ።
የውጭ ዜጎች በአሜሪካ ውስጥ ሲሆኑ ለአሜሪካ ህጎች ተገዢ እንደሚሆኑ ሁሉ በውጭ ሀገር በምትሆኑበት ጊዜ ለምትገኙበት ሀገር ህጎች ተገዢ መሆናችሁን አስታወሱ።
ኢትዮጵያ ውስጥ በምትቆዩበት ጊዜ በህጋዊ ሁኔታ መቆየት በጣም አስፈላጊ ነው። ይህ እንደ ዓለም አቀፍ ዜጋ ያለባችሁ ግዴታ እና ኃላፊነት ሲሆን ከዚህም በላይ ገንዘባችሁን ለመቆጠብ ብልህ ውሳኔ ነው " ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
#USA #ETHIOPIA
@tikvahethiopia
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: