ሚካኤል ደግ ነው ብዬ እዘምራለሁ ብዬ እዘምራለሁ፤ ያደረገልኝን እኔ ብዙ አውቃለሁ እኔ ብዙ አውቃለሁ።
Автор: EOTC St.Michael ኮሎኝ ቅዱስ ሚካኤል AEOKD Cologne Germany
Загружено: 2025-11-25
Просмотров: 126
ሚካኤል ደግ ነው ብዬ ዘምራለሁ ብዬ ዘምራለሁ
ያደረገልኝን እኔ ብዙ አውቃለሁ እኔ ብዙ አውቃለሁ
ሚካኤል አምሳለ ኮከብ፤ ልብህ የዋህ የፍቅር መዝገብ
ገና ከልጅነት እኔን ተንከባክቦ
ከተዋበ ደጁ በረከት መግቦ
ከመንገዴ መርቶኝ አለሁ እስከ ዛሬ
ክብሩን እያሰበ ይቀኛል ከንሬ
አዝ . . .
ከአምላክ አገናኘኝ በፍቅር ቃል ጠርቶ
ግብጽን እንዳልሰማ ጆሮዎቼን ቃኝቶ
አሁን በሕይወት ነኝ ገብቼ ከርስቴ
ጥበቃው ሳይርቀኝ ሚካኤል አባቴ
አዝ . . .
ከኃላ ያጠረኝ ከፊት የቀደመ
ደመናን ዘርግቶ ጠላቴን ያስቆመ
ከእግዚአብሔር ተልኮ ፈጥኖ የደረስ
የዋህ ነው ሚካኤል እምባዬን ያበሰ
አዝ . . .
በእኩለ ሌሊት በእሥራት ሳለሁ
ከእንቅልፌ ቀስቅሶ ብርሃን አይቻለሁ
ሰንሰለቴ ወድቋል ከክብሩ የተነሳ
ውለታው ብዙ ነው ከቶ የማይረሳ
አዝ . . .
ኅዳር ፲፪ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም November 21/2025
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: