የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 1 - ክፍል 1 "እንዴት የመሲሁ ማንነትና ሥራ በመጥምቁ ዮሐንስ አገልግሎት ተገለጠ?"
Автор: LoveIsrael Ethiopia - የመፅሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች
Загружено: 2023-07-29
Просмотров: 1953
#LoveIsrael_Ethiopia #የማርቆስ_ወንጌል#ማርቆስ_1_ክፍል_1
ይህ ቪዲዮ የማርቆስ ወንጌልን ክፍል አንድን ትምህርት የሚቀርብበት ሲሆን ዋናው ርዕስ “መሲህ ማን ነው?” የሚለውን ጥያቄ የሚመልስ ሲሆን መሲህ ማን እንደሆነ እና የእርሱ ሥራ ምን እንደ ሆነ ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲኖረን እያንዳንዱን ምዕራፍ፣ እያንዳንዱን ጥቅስ እና እያንዳንዱን ቃል እንሄድበታለን። ይህ ትምህርት በትክክል የቃሉን ቅደም ተከተልና ትርጉም እንዴት አብረው እንደሚሠሩና የሰዋስው ምልክቶች በመመልከት ሲሆን መሲሑን በተመለከተ የእግዚአብሔር መገለጥ ሙሉ ግንዛቤ እንዲኖረን እና መሲሁ ለምን እንደመጣ እና ለምን እንደሚመለስ ሙሉ ግንዛቤ እንዲኖረን ጭምር ነው። ክፍል አንድ ስለ መጥምቁ ዮሐንስ የሚናገር ሲሆን ዮሐንስ መንገዱን በምድረ በዳ እንዲያዘጋጅ የተጠራው በእግዚአብሔር ላይ እንድንታመንና እንድንደገፍ ለማስተማር ነው። ጥምቀት የመጥለቅ ፅንሰ-ሀሳብ የመጣው በአይሁድ ህዝብ ላይ ሽግግርንና ለውጥን ለማሳየትና ለአንድ ዓላማ መቀደስ ነበር። ስለዚህ እዚህ ላይ ዮሐንስ ለዚሁ ዓላማ እንደተለየና ሌሎችንም ለዚሁ ዓላማ እንዲያዘጋጅ እንደተጠራ እናያለን። ይህን ቪዲዮ በማድመጥ እንዲባረኩና ለሌሎችም እንዲያጋሩ እነጋብዛለን።
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: