አዩኸል ሙሪድ(ايها المريد)||የፍላጎት ፅንሰ ሀሳብ መረዳት||ሸይኽ ሐቢብ ዓሊ ጂፍርይ||ምዕራፍ 1||ክፍል 1|| @almarifa.alfaruk1
Загружено: 2025-11-14
Просмотров: 2509
«አዩኸል ሙሪድ» ደርስ በ ሸይኽ ሐቢብ አሊ ጂፍሪ
አላህ በናፍቆት ባሮቹን "ተመለሱ፣ ቅረቡኝ”በሚል ሹክሹክታ ይጣራል። ወደ እዝነቱ ሰገነት ይጋብዛል። ታዲያ ከሩሃችን ጋር ተግባብተን ምላሽ ልንሰጠ ምን ከለከለን? እንቅፋቶቹን፣እንዴት እንለፋቸው?
በሁለቱም ዓለም መሸለምን የሚያድለውን ቀና መንገድ ይዘን፣ እውነተኛ የ አሏህ ወዳጆች ምንሆነው በምን መንገድ ነው? ለ እነዚህና ተያያዥ ጥልቅ ሃሳቦች ምላሽ ያያዘ ደርስ ነው “አዩሃል ሙሪድ”
“አዩሃል ሙሪድ”…የዘመናችን ድምቀት የሆኑት አህለል በይቱ፣የተዝኪያ ጠቢብ፣ የዒልም ማደርያ፣ የፍቅር ሰባኪ፣የትህትና መመህር፣ የተሰውፍ ማሳያ የሆኑት እውቁ ዓሊም እና ዓለማቀፍ ዳዒ ሸይኽ ሀቢቢ አሊ ጂፍሪይ ጥልቅ መንፈሳዊ አስተምህሮትን የቃኙበት ደርስ ነው።
“አዩሃል ሙሪድ” ደርስ ብቻ አይደለም። የነፍስ የጥሞና ጉዞ፣የተረሱ የስነ ምግባር፣ የቅንነት፣ የተውበት፣ የትዕግሥትና የፍቅር ትርጉሞችን የሚያድስ ሰንቅ ነው።
ይህ 90 ክፍሎች ያሉት ተከታታይ ደርስ በጩኸት መካከል ሰላምን፣ በውዝንብር ውስጥ ሰኪናን ለሚፈልግ ነፍስ የተዘጋጀ ፈውስ ነው። መለኮታዊውን መንገድ በስኬት ለመራመድ ለሚሻ ሁሉ ሐዲድ ነው። ሙሪድ ሆይ! መንገዱ ረጅም አይደለም እና ንቃ።ለመንቃትም እነዚህን ያዝ…… ብለው ሼኽ አሊ ጂፍር ከጥልቅ እውቀታቸው ያቋድሱናል።
ታዲያ ይሄን 90 ክፍሎች ያሉት መንፈሳዊ የጥሞና ጉዞ፣ጠቀሜታውን በማሰብ…በ አል ፋሩቅ መልቲ ሚዲያ ተዘጋጅቶ በ በተርጓሚ አቡ ከውሰር ወደ አማርኛ ተተርጉሞ በቅርቡ በአልፋሩቅ አልማዕሪፋ ዩቱዩብ ቻናል ላይ የሚለቀቅ ይሆናል!
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: