1. ያዕቆብ፦ እውነተኛ እምነት
Автор: Evangelist Yared Tilahun
Загружено: 2022-01-12
Просмотров: 42050
የያዕቆብ መልዕክት አማኝ ነኝ የሚል ሁሉ እንደ ታካሚ ሐኪም ፊት ቀርቦ የሚመረመርበት፣ እንደ ወርቅ በእሣት የሚፈተንበት፣ በአውድማ እንዳለ እህል በመንሽ የሚበጠርበት፣ እንደ ከበረ ድንጋይ በእውነት ሚዛን የሚመዘንበት መልዕክት ነው። በያዕቆብ መልዕክት እምነት “አለኝ” የሚባል ስውር የቃላት ክምር ሳይሆን በሥራ የሚገለጥ ተግባር መሆኑ ይተነተናል።
ይህ በኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን ውስጥ አዕማድ በነበረው የጌታ ወንድም (ከፊል) ያዕቆብ ለተበተኑት አይሁድ አማኞች በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ የተጻፈ ደብዳቤ የክርስቶስ ኢየሱስን አስተምህሮ ማዕከል በማድረግ፣ የእግዚአብሔርን ማንነት፣ የሰውን ተፈጥሮ፣ የምኞትን ክፋት፣ የዓለምን ማታለል፣ የአንደበትን ኃይል፣ የጸሎትን ጉልበት በረቀቁ ቃላት ይተነትናል። ዕቡያንን ይዘልፋል፣ ተግባር የራቃቸውን ቃላተኞች ይወቅሳል፣ ጌታ፣ ጌታ የሚሉትን ዓለመኞች ያስጠነቅቃል፣ ለምስኪኖች ይሟገታል፣ የተናቁትን ድሆች በውስጣቸው ያለውን ክብር እያሳየ ያበረታታል።
ይህን መልዕክት በስፋትና በጥልቀት የተረዳ ሰው አእምሮው ይታደሳል፣ ባሕሪው ይቀረጻል። ከእንጭጭነት ወጥቶ ይበስላል፣ ከሞኝነት ወጥቶ ጥበብ ይጎናጸፋል። ከሚጠፋው ዓለም ተርፎ ለሚመጣው ክብር ይዘጋጃል። ይህን መልዕክት በምንማርበት ጊዜ ይህ ሁሉ በሕይወታችሁ እንዲሆን ምኞቴና ጸሎቴ ነው።
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: