አምላክ ሆይ ወደኛ ባትመጣ Amlak hoy Wedegna batmeta
Автор: Solen ሶለን
Загружено: 2023-03-13
Просмотров: 6521
አምላክ ሆይ ወደኛ ባትመጣ
/ዘማሪት አዳነች አስፋው/
አምላክ ሆይ ወደኛ ባትመጣ ለብሰህ የማርያምን ሥጋ/2/
ባክኖ የነበረው የአዳም ልጅ ወጤቱ ነበር የሚያሰጋ/2/
በዚያ ዓመት በዚያች ወር በዚያች ቀን ድኅነትን ለሰው ልጅ ስትሰጥ
ምን የበዛ ነበር ትኅትናህ ትዕግሥትህ የማይለወጥ/2/
የሾህ አክሊል ደፍተው በራስህ ጐንህን ሲወጉህ በጦር
አንተ ግን ለእነርሱ ከአባትህ ምሕረትን ትለምን ነበር/2/
ግን መቼ አወቁህ እነርሱ በኃጢአት ደንዝዞ ልባቸው
መድኃኒታቸውን ገረፉህ ሰቀሉህ አንተም ሞትክላቸው/2/
ዳግም ስትመጣ ለፍርድ ከዓለም ፍፃሜ በኋላ
ኧረ እንዴት እድለኞች ናቸው በፊትህ የሚያገኙ ተድላ/2/
በዚያች በደብረ ዘይት ቦታ ደስታና ለቅሶ ሲፈልቅ
ከቶ ከየት ይሆን እጣዬ ያንጊዜ የእኔ አወዳደቅ/2/
የፀፀት እሮሮ በፊትህ እንዳያቃጥለኝ እኔን
እርዳኝ ፈጣሪዬ ከአሁኑ አድሰው የዛገው ልቤን/2/
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: