የመለኮታዊ ምሕረት የስምንተኛው ቀን (ፋሲካ አርብ) ታስዕት(ኖቬና) የጸሎት ሐሳብ ስቅለተ አርብ
Автор: የሮዛሪ ድምፅ | Voice of Rosary
Загружено: 2024-05-10
Просмотров: 168
የስምንተኛው ቀን (ፋሲካ አርብ) የመለኮታዊ ምሕረት ኖቬና የጸሎት ሐሳብ
ኢየሱስ፦"ዛሬ የታሰሩትን የንስሐ (በጊዚያዊ ፍርድ ቅጣት በመንጽኤ እሳት ያሉ) ነፍሳትን ወደ እኔ አምጡና በጥልቁ ምሕረቴ ውስጥ አስጥሟቸው። የደሜ ጅረት የሚያቃጥል እሳታቸውን ያቀዘቅዝ። እነዚህ ሁሉ ነፍሳት በእኔ በጣም የተወደዱ ናቸው። በፍትሔ ላይ ካሳን እየፈጸሙ ነው። እፎይታን ልታመጡላቸው አቅም አላችሁና። ከቤተ ክርስቲያኔ ግምጃ ቤት ሁሉንም የኃጢያት ካሳ (indalegeouns) ስርየት ይሻሉ እና ስለ እነርሱ በጸሎት አቅርቡ። ኦ፣ የሚሰቃዩትን ስቃይ ብታውቁ ኑሮ፣ ያለማቋረጥ የመንፈስ ምጽዋት ትሰጡላቸው ነበር እናም ለፍትሔም ዕዳቸውን ትከፍሉ ነበር።
ቅድስት ፋውስቲና፡- እጅግ መሐሪው ኢየሱስ ሆይ፣ አንተ ራስህ ምሕረትን እንደምትፈልግ ተናግረሃል። ስለዚህ በመንጽሔ ውስጥ ያሉትን ነፍሳትን በአንተ ሩሕሩህ የልብህ መኖሪያ እንድትቀበላቸው አቀርብልሀለሁ፣ ለአንተ በጣም ውድ ናቸው፣ ነገር ግን ለፍትህ ካሳ መበቀል አለባቸው። ከልብህ ፈልቀው የፈሰሱት የደም እና የውሃ ምንጮች የምሕረትህ ሀይል ይወደስ ዘንድ የንስሐ ነፍሳትን ነበልባሉን ያጥፉ።
እጅግ ከሚያስፈራው ከሚያነጻው እሳት
ስሞታ ይነሳል ለምሕረትህ
ተቀላቅሎ በሚፈሰው በደምና የውሀ ጅረት ውስጥ
መጽናናትንም ያገኛሉ ከጭንቅም ይወጣሉ እፎይ ይላሉ
ዘላለማዊ አባት ሆይ፣ እጅግ በጣም ሩህሩህ በሆነው የኢየሱስ ልብ ውስጥ በተካተቱት በንስሐ ነፍሳት ውስጥ በሚሰቃዩ ነፍሳት ላይ የምሕረት ፊትህን መልስ። በልጅህ በኢየሱስ አሳዛኝ ሕማም እና እጅግ የተቀደሰች ነፍሱ በተጥለቀለቀችበት ምሬት ሁሉ እለምንሃለሁ፡ ምሕረትህን በፍትሕ ቁጥጥርህ ሥር ላሉ ነፍሳት ግለጽ። ለምሕረትህ፥ ለመልካምነትህ፥ እና ለርሕራሔህ ገደብ እንደሌለው በእርግጠኝነት እናምናለንና ወደ እነሱ በተወዳጅ ልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ ቁስሎች ብቻ እንጂ በሌላ በኩል አትመልከት። አሜን።
የቅድስት ፋውስቲና ማስታወሻ 1226 - 1227
እንኳን ወደዚህ የዩትዩብ ገፅ በደህና መጣችሁ በዚህ ገፅ የሚከተለውን የቤተክርስቲያን ሐሳብ እናገለግላለን እንጋራለን "ቅዱስ ዜማ በቅዱስ መጽሐፍ ተመስግኗል(ኤፌሶን 5:19 ቆላስያስ3:16) ...ቅዱስ ዜማ ከሊጡርጊያ ተግባር ጋር ጥብቅ የሆነ ግንኙነት ካለው በቅድስና ያድጋል፤ በውበት ጸሎትን ይገልጻል ፤ አንድነትን ያስፋፋል ፤ ከፍ ባለ ሥነ-ስርዓትም ቅዱሳት ስርዓቶችን ያበለጽጋል። ቤተክርስቲያንም በእውነት ኪነ ጥበብ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ትቀበላለች ፤ በጥራታቸው ተስማሚና ተገቢ ከሆኑም በመለኮታዊ አገልግሎት ላይ ታውላቸዋለች።" የሁለተኛው ቫቲካን ጉባኤ ስለ ስርዓተ አምልኮ ምዕራፍ 6 ቁጥር 112
Join this channel to get access to perks:
/ @ethiopiancatholic
Social Media
Facebook / 478539786435992
Telegram https://t.me/Catholicsong
YouTube / @ethiopiancatholic
#EthiopianCatholicSong #HawassaCatholicSong #EthiopianCatholicMezmur#EthiopianCatholicChurch #Catholic #EthiopianCatholic #CatholicMezimurLyrics
#LyricsVideos #Mezmur #ካቶሊክ #ካቶሊክመዝሙር
Rosery, ሮዛሪ, ሮዘሪ, መቁጠርያ, መቁጸርያ, VoiceOfRosary, Rosary
hymns for mass, catholic hymns of praise, church songs catholic,holy rosary monday, virtual rosary, catholic diocese,thursday holy rosary,mass times online,livestream mass,daily mass,the daily mass,the daily mass,rosary for sunday,catholic church near me,spiritual praise songs,music for body and spirit
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: