⭕️ አዲስ መዝሙር "ካህነ እግዚአብሔር" | Abune Teklehaymanot New Mezmur 2018 | Bella Felege Selam አቡነ ተክለሃይማኖት
Загружено: 2026-01-01
Просмотров: 1673
በቤላ ፈለገ ሰላም መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወአቡነ ተክለሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን የተዘመረ የአባታችን የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ድንቅ መዝሙር።
ይህ መዝሙር የኢትዮጵያ ብርሃን፣ ሐዲስ ሐዋርያ፣ የኢቲሳው ፀሐይና የደብረ ሊባኖሱ ኮከብ ለሆኑት ለታላቁ አባት ለቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት የተበረከተ ነው። አባታችን በምልጃቸው ሀገራችንን እንዲጠብቁልን እየለመንን፤ የእሳቸውን ገድልና ትህትና የምናወድስበት ነው።
የመዝሙሩ ግጥም (Lyrics)
ካህነ እግዚአብሔር የተሸለመ አክናፍ
ቆሞ የሚለምን ከሥላሴ ደጃፍ
ዳግማዊ ዮሐንስ ወንጌል የማረከው
ተክለሐይማኖት ነው በፍቅር የመነነው
ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስቅዱስ
እንደ ሱራፊ ያጠንክ ሰማይ ድረስ
የጸጋ ዘአብ ልጅ የእግዚዕኃረያ
ካህንና ነቢይ የጽድቅ ባለሙያ
ወደ እግዚአብሔር መንገድ ህዝቡን የመራኸው
በማይጠፋው ቃሉ ተክለህ ያፀናኸው
የወንጌሉ አርበኛ ተክለሃይማኖት
ንዑድ ነህ ክቡር ነህ ያበራህ በእምነት
ተክለሃይማኖት ብፁዕ ኮከበ ኢትዮጵያ
ፀሎት አሳራጊ ሐዲስ ሐዋርያ
የጠላት መድኃኒት የእቲሳው ፀሐይ
ገድሉ ያበራ አባት በምድርና ሰማይ
ተነስ አባታችን ዛሬም ለህዝቦችህ
ኢትዮጵያን አስምራት በጸሎት በምልጃህ
በመከራ ጊዜ በእምነት እንድንፀና
ልጆችህን ባርከን መስቀልክን ያዝና
የምዕመናን አባት የአህዛብ መምህር
መስቀል የተሸከምክ የተሸነፍክ ለፍቅር
ታላቅ ተጋድሎህን ስራህን ተምረን
በረከት አገኘን ስምህን ዘክረን
የሰንበት ትምህርት ቤታችንን አገልግሎት ለመደገፍና አዳዲስ መዝሙራትን ለማግኘት፦
✅ ሰብስክራይብ (Subscribe) ያድርጉ
✅ የደወል ምልክቷን ይጫኑ
✅ ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ (Share)
#AbuneTeklehaymanot #አቡነ_ተክለሃይማኖት #ተክለሃይማኖት #Mezmur #EthiopianOrthodox #BellaFelegeSelam #NewMezmur #TewahedoMezmur #ደብረ_ሊባኖስ #መዝሙር #Ethiopia #Orthodox
አቡነ ተክለሃይማኖት, Abune Teklehaymanot, ተክለሃይማኖት, Teklehaymanot, አቡነ ተክለሃይማኖት መዝሙር, Abune Teklehaymanot Mezmur, ተክለሃይማኖት መዝሙር, Teklehaymanot Mezmur, የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት መዝሙር, አዲስ መዝሙር, New Mezmur 2026, Ethiopian Orthodox Mezmur, ተክለሃይማኖት ገድል, ጻድቁ አባት, ደብረ ሊባኖስ, Debre Libanos, ኢቲሳ, Etisa, ካህነ እግዚአብሔር, Bella Felege Selam, ሰንበት ትምህርት ቤት መዝሙር, Orthodox Tewahedo, መንፈሳዊ መዝሙር, ሐዲስ ሐዋርያ, ባለ ስድስት ክንፍ, የታህሳስ 24 መዝሙር, የግንቦት 12 መዝሙር, የነሐሴ 24 መዝሙር, Ethiopian Orthodox Tewahedo Church.
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: