Популярное

Музыка Кино и Анимация Автомобили Животные Спорт Путешествия Игры Юмор

Интересные видео

2025 Сериалы Трейлеры Новости Как сделать Видеоуроки Diy своими руками

Топ запросов

смотреть а4 schoolboy runaway турецкий сериал смотреть мультфильмы эдисон
dTub
Скачать

ገድለ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ

Автор: መባ

Загружено: 2025-10-14

Просмотров: 147

Описание:

"የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው" ምሳ. 10፥7

"ከኢትዮጵያ ሰዎች ኃጢአት ይልቅ ገድልህ ትሩፋትህ ሃይማኖትህ ስለበለጠ በዚህም ምክንያት ያለ ልክ ያለመጠን የኢትዮጵያ ሰዎች ኃጢአት ተሰረየላቸው፡ ፡ ስለ ሠራኸው መልካም ሥራ ሁሉ ፈጽሜ ይቅር አልኳቸው...."

የገድልህን መጽሐፍ የጻፈውም ያጻፈውም ካንተ ጋር በግልጥ ይለፍ፤ የእሳት ባሕርን ይሻገር ማደሪያውም በብርሃን ቤቶች ይሁን፤ ስሙንም ግሩም በሚሆን መንበሬ ላይ እጽፋለሁ።

አምኖ ሳይጠራጠር ሳያወላውል መታሰቢያህን ያደረገ የእሳት ባሕርን ይሻገር ያለ ፍርሀትም በፊቴ ይቁም ለተራቡት እንጀራ ቢሰጥ በመጨረሻይቱ ቀን እኔ የሕይወት ኅብስትን እሰጠዋለሁ በዚህም ዓለም አላስርበውም።

ለተጠማ ሰው ጽዋ ውኃ ቢያጠጣ እኔ ከሕፃናት ጋር በመንግሥተ ሰማያት መንፈሳዊ ወተትን አጠጣዋለሁ በመታሰቢያ ቀንህ ዕጣን የሰጠ ሰው ቢኖር ኃጢአተኛም ቢሆን እንደ አበው ንጹሕ ይሆናል ለመታሰቢያህ ንጹሕ ሥንዴ የሰጠ በኢየሩሳሌም ሰማያዊት ቁርባን ይቀበላል።

በመታሰቢያህ ቀን ዘይት የሰጠ ቢኖር ርስቱ ከአብርሃም ከይስሐቅ ከያዕቆብ ጋር ይሁን መባዕ መብራት ቢያገባ የእሳቱን የጨለማውን ባሕር ከፀሐይ ሰባት እጅ በሚያበራ በዐሥራ ሁለት መብራት [ይለፍ] በበዓልህ የተሰበሰቡትን ከቅዱሳን ጋር በደብረ ጽዮን እሰበስባቸዋለሁ።

ከዚህ በኋላ አባታችን ተነሥቶ ጌታችንን እንዲህ ብሎ ለመነው አምስት መቶ ስሳ ሁለት ዘመን ስኖር ውኃ አልጠጣሁም እህል ለመብላት አላሰብኩም የዛፍ ፍሬም አልቀመስኩም ለሰውነቴም ልብስ አልፈለግሁም ራቁቴን ኖርኩ እንጂ በባሕር ውስጥም ከዓሣ ከባሕር ዘንዶና ከአዞ ጋር ኖርኩ ከዛፍ በታችም ከአዕዋፍ ጋር ኖርኩ ከተራራ ወደ ተራራ እየተዘዋወርኩ ከአንበሳና ከነምር ከድብና ከዘንዶ ጋር ኖርኩ።

እኔ እለምንሃለሁ እማልድሃለሁ እሺ በለኝ አንድ ሰው ኃጢአት ቢሠራ መታሰቢያዬንም ቢያደርግ ንስሐ ሳይገባ ድንገት ቢሞት ትምርልኝ ዘንድ።

መድኅንም ለአባታችን እሺ ምሬልሃለሁ ብሎ መለሰለት፤ ነፍስህ ከሥጋህ ከተለየችበት ከመጋቢት ፭ ቀን ጀምሮ መታሰቢያህን ያድርጉ አሁንስ ወደ ሰማይ ከፀሐይ ሰባት እጅ ወደሚያበራው ወደ ብርሃን ቤት ውጣ እነሆ ዐሥራ ሁለት አክሊላት ሰጥቸሃለሁ።

ከዚህ በኋላ ቅዱስ ሚካኤል ሦስት አክሊል አቀዳጀው ቅዱስ ገብርኤልም ሦስት አክሊል ሰጠው ሱራፌልም ሦስት አክሊል ሰጡት ኪሩቤልም ሦስት አክሊል ሰጡት።
 
ዳግመኛም እነሆ መብራት ሰጥቸሃለሁ ዐሥር እልፍ በቀኝህ ዐሥር እልፍ በግራህ ዐሥር እልፍ በፊትህ ዐሥር እልፍ በኋላህ እያንዳንዱ ብርሃን ከፀሐይ እጥፍ የሚያበራ ነው።

ዳግመኛ እነሆ የብርሃን ድባብ ሰጥቸሃለሁ ዐሥር እልፍ በቀኝህ ዐሥር እልፍ በግራህ ዐሥር እልፍ በፊትህ ዐሥር እልፍ በኋላህ ይሁኑልህ የያንዳንዱም የድባብ ብርሃን ከፀሐይ ብርሃን እጥፍ የሚያበራ ነው።

አምስት መቶ ስልሳ ሁለት ዓመትም ያለ ልብስ ራቁትህን ስለኖርክ የብርሃንን ልብስ እነሆ ሰጥቸሃለሁ አለው። የደስታ ሞጣሕት ሰጠሁህ ዓይነቱ መብረቅ የሚመስለውን እንደ ንስር የሚበሩ ክንፍ ያላቸው ፈረሶችን እነሆ ሰጥቸሃለሁ አለው።

አባታችንም ጌታችንን አቤቱ የኢትዮጵያን ሕዝብ አንድ ሳታስቀር በሙሉ ማራቸው አለው።

ጌታችንም አባታችንን እነሆ የኢትዮጵያን ሕዝብ በሙሉ ዐሥራት እንዲሆኑህ ሰጥቸሃለሁ፤ እንደወደድክ ላንተ ይሁኑ መታሰቢያህን ያድርጉ፤ በጸሎትህ ይታመኑ ደስ ብሏቸው ለዘላለም ይኑሩ። አባታችንም እንዲህ አለው፤ ቀድሞ እስከ ዐሥራ አምስት ትውልድ እምርልሃለሁ ብለኸኝ ነበር ልጅ ባይኖራቸው መካን ቢሆኑስ ምን ትሰጣቸዋለህ።
ጌታም እኔ ልጅ እሰጣቸዋለሁ ሴቲቱም መካን ብትሆን ለመውለድ ማሕፀንዋን እከፍታለሁ ወንዱም መካን ቢሆን ከሰውነቱ ዘር አስገኝለታለሁ።
ዳግመኛም መታሰቢያህን የሚያደርገውን እናት አባቱ ቢሞቱ ወደ ሲኦልም ቢወርዱ ከእሳት ውስጥ አወጣቸዋለሁ ነፍሳቸውን እሰጥሃለሁ ያንተ ገንዘብ እንዲሆኑህ ዐሥራትም ይሆኑህ ዘንድ።

መነኩሴውም የሥጋው መርከብ ቢሰበር የሥጋ ጉስቁልና ቢያገኘው እኔ የድንግልና ክንፍ አበቅልለታለሁ ንጽሕናንም አጎናጽፈዋለሁ።" #ethiopia #eotc #tewahedo #duet #orthodox #abunegebremenfesqidus

ገድለ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ

Поделиться в:

Доступные форматы для скачивания:

Скачать видео mp4

  • Информация по загрузке:

Скачать аудио mp3

Похожие видео

የመስከረም ገድለ ቅድስት አርሴማ

የመስከረም ገድለ ቅድስት አርሴማ

ዘወትር የሚደመጡ መዝሙሮች ስብስብ || የማለዳ

ዘወትር የሚደመጡ መዝሙሮች ስብስብ || የማለዳ

የቦሌ ቡልቡላ ልበ ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል

የቦሌ ቡልቡላ ልበ ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል

ЧТО ПИТЬ, Чтобы Быстро Улучшить Кровообращение В Ногах? После 60! Доктор Мясников

ЧТО ПИТЬ, Чтобы Быстро Улучшить Кровообращение В Ногах? После 60! Доктор Мясников

Segenet Studioመስማማት ተስኖት እየተተራመሰ ያለው የአረጋ ከበደ ካቢኔ እና መፍረሳቸውን በፕሮፓጋንዳ የመሸፈን ዘመቻ ! Dec 22/2025

Segenet Studioመስማማት ተስኖት እየተተራመሰ ያለው የአረጋ ከበደ ካቢኔ እና መፍረሳቸውን በፕሮፓጋንዳ የመሸፈን ዘመቻ ! Dec 22/2025

የታኅሣሥ ገድለ ቅድስት አርሴማ

የታኅሣሥ ገድለ ቅድስት አርሴማ

የአቡነ_ገብረ_መንፈስቅዱስ_-_መንፈሳዊ ፊልም |Abune Gebre menfeskidus menfesawi film

የአቡነ_ገብረ_መንፈስቅዱስ_-_መንፈሳዊ ፊልም |Abune Gebre menfeskidus menfesawi film

Христианская молитва. Разговор с Богом. Преподобный Исаак Сирин

Христианская молитва. Разговор с Богом. Преподобный Исаак Сирин

Как на самом деле был построен Ноев ковчег | Повседневная жизнь избранных Богом ДОКУМЕНТАЛЬНЫЙ ФИЛЬМ

Как на самом деле был построен Ноев ковчег | Повседневная жизнь избранных Богом ДОКУМЕНТАЛЬНЫЙ ФИЛЬМ

የኅዳር ድርሳነ ሚካኤል

የኅዳር ድርሳነ ሚካኤል

ገድለ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ

ገድለ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ

🔴 ጭንቅ ውስጥ ያላችሁ❗️👉እንዲህ አድርጉ || በመልአከ ኤዶም ሕርያቆስ @Mataniya23

🔴 ጭንቅ ውስጥ ያላችሁ❗️👉እንዲህ አድርጉ || በመልአከ ኤዶም ሕርያቆስ @Mataniya23

🟠

🟠"ወደ ንስሃ የሚመሩ የማለዳ ዝማሬዎች" #በመንበርከክ #ማነው_እንደኔ #የታል_አንተን_መፍራት #ፍቅር_ነህ #መበርቻዬ_ነህ_መጽናኛዬ #የእውነትን_መንገድ

Просыпаетесь между 3 и 5 утра? Сделайте ЭТИ 5 вещей | Еврейская Мудрость

Просыпаетесь между 3 и 5 утра? Сделайте ЭТИ 5 вещей | Еврейская Мудрость

አባ ጽጌ ድንግል ማን ነው ? #ማህሌተጽጌ - መባዕ ቲቪ ( MEBA TV ) @Meba_tv

አባ ጽጌ ድንግል ማን ነው ? #ማህሌተጽጌ - መባዕ ቲቪ ( MEBA TV ) @Meba_tv

መዝሙረ ዳዊት እንዴት እንጸልይ? I እጅግ ድንቅ ትምህርት በመጋቤ ሃዲስ እሸቱ አለማየሁ

መዝሙረ ዳዊት እንዴት እንጸልይ? I እጅግ ድንቅ ትምህርት በመጋቤ ሃዲስ እሸቱ አለማየሁ

Псалом 26, 50, 90 | Защитные молитвы от врагов, нечистых сил и зла (7 раз)

Псалом 26, 50, 90 | Защитные молитвы от врагов, нечистых сил и зла (7 раз)

የስሕበት ህግ ጭንብል!!!..በአዲሱ መጽሀፌ ፊጣሪን የሚያስክድ አስተሳሰብ የተደበቀ ሚስጢር ማጋለጥ ነው... መምህር ዶ/ር ዘበነ ለማ | Seifu on EBS

የስሕበት ህግ ጭንብል!!!..በአዲሱ መጽሀፌ ፊጣሪን የሚያስክድ አስተሳሰብ የተደበቀ ሚስጢር ማጋለጥ ነው... መምህር ዶ/ር ዘበነ ለማ | Seifu on EBS

🛑 ፍካሬ ኢየሱስ - የዓለም መጨረሻ - Fkare Eyesus | @mahtebmedia21 | #eotc #ethiopia

🛑 ፍካሬ ኢየሱስ - የዓለም መጨረሻ - Fkare Eyesus | @mahtebmedia21 | #eotc #ethiopia

የዓርብ ገድለ አቡነ ሃብተ ማርያም

የዓርብ ገድለ አቡነ ሃብተ ማርያም

© 2025 dtub. Все права защищены.



  • Контакты
  • О нас
  • Политика конфиденциальности



Контакты для правообладателей: [email protected]