እወድሃለሁ Ewedehalehu ሳሙኤል ንጉሤ Samuel Nigussie Protestant mezmur
Автор: Official Kirubel mulugeta
Загружено: 2025-04-14
Просмотров: 9965
የምወደው የምወደው ሁልግዜ
ደስ የሚለኝ ደስ የሚለኝ እኔስ ሁሌ (2x)
ሳወራው ነው ሰው የመሆን ምክንያቴን
ሳወራው ነው የመዳኔን ምክንያቴን
ስለኔ በመስቀል ሞተሃል እወድሃለሁ እወድሃለሁ
ስለኔ ደምን አፍሥሰሃል እወድሃለሁ እወድሃለሁ
ስለኔ ያልሆንከው የቱ ነው እወድሃለሁ እወድሃለሁ
ምክንያትህ ለኔ ያለህ ፍቅር ነው እወድሃለሁ እወድሃለሁ
እወድሃለሁ እወድሃለሁ እንዳንተ ሚሆንልኝ ማነው
እወድሃለሁ እወድሃለሁ ኢየሱስ ታሪኬን ቀየርከው
እወድሃለሁ እወድሃለሁ እንዳንተ ሚያስብልኝ ማነው
እወድሃለሁ እወድሃለሁ ዘላለሜ ያማረው ባንተ ነው
ተስፋ ያልነበረውን ያንን ሂወቴን
የሞት ድምፅ ቢሰማ ጨለማው ቤቴ
በፍቅር ዘልቀህ ወደ ውስጠኛው ልቤ ውስጥ ገብተህ
አበራህልኝ የህይወቴን ብርሃን ከሰማይ ሰጠህ
ሰላምህ ህይወቴን አጥለቀለቀው
የደስታ ዘይት ውስጤን አራሰው
ዝምብዬ አይደለም በጥዋት ማታ ኢየሱስ የምለው
ፍቅርህ ታሪኬን ህይወቴን ሁሉ መልካም አርጎት ነው
እወድሃለሁ እወድሃለሁ እንዳንተ የሚመቸኝ ማነው
እወድሃለሁ እወድሃለሁ ኢየሱስ ታሪኬን ቀየርከው
እወድሃለሁ እወድሃለሁ ዘላለሜ ያማረው ባንተ ነው
እወድሃለሁ እወድሃለሁ እንዳንተ ሚያስብልኝ ማነው
የምህረት ልብህ ለእኔ ያለህ
ሁሌ የሚፈልገኝ ማይሰለቸኝ ነህ
ምክንያቱ ሆነህ ከዘላለም ሞት ጥፋት መትረፌ
እንዲህ በሰላም እንዲህ በደስታ በህይወት መኖሬ
ወደድከኝ ወደድከኝ እስከሞት ድረስ
ተሰቃየህልኝ ህመሜን ታመምክ
ያን ሁሉ ስቃይ መራራን ፅዋ እንዲያ የጠጣኸው
ዛሬየን አይተህ በእረፍት እንድኖር ነው እወድሃለሁ
ለእኔ ነው ለእኔ ለእኔ ነው ለእኔ ዛሬዬን አይተህ ሁሉን ታገስከኝ ኢየሱስ ወዳጄ
ለእኔ ነው ለእኔ ለእኔ ነው ለእኔ እወድሃለሁ ከሞት ያዳንከኝ አንተ ነህ ውዴ
(መስከረም ጌቱ)
እወድሃለሁ እወድሃለሁ እንዳንተ ሚሆንልኝ ማነው
እወድሃለሁ እወድሃለሁ ኢየሱስ ታሪኬን ቀየርከው
እወድሃለሁ እወድሃለሁ እንዳንተ ሚራራልኝ ማነው
እወድሃለሁ እወድሃለሁ እንዳንተ የታገሰኝ ማነው
ሰላሜ ነህ ሰላሜ ነህ ሰላሜ
እረፍቴ ነህ እረፍቴ ነህ
በጣም የምወድህ በጣም የምወድህ
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: