የዉርስ ህግ/የሰበር ዉሳኔ የዉርስ ጉዳይ ላይ የወራሽነት ማስረጃና የይርጋ ጉዳይ/Ethiopia succession law
Автор: Tadesse G/silassie-ታደሰ ገ/ስላሴ
Загружено: 2025-02-07
Просмотров: 8856
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌደራል ጠቅላይ
ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
የሰ/መ/ቁ. 243973 1 ቀን ፡- ጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ/ም
1. ጉዳዩ:- ውርስን ነዉ፡፡ የወራሽነት ማስረጃ ማውጣት ተፈጻሚ በሚሆነው የይርጋ ድንጋጌ ተፈጻሚነት ላይ ያለውን ውጤት ምንድን ነዉ የሚለዉን የሚመልስ ነዉ፡፡
በዚህ ጉዳይ ላይ የፌ/ሰ/ሰ/ችሎት የሰጠዉን ትንታኔ ስንመለከት
1. የፌ/ሰ/ሰ/ችሎት የያዘዉ ጭብጥ፡-የወራሽነት ማስረጃ አስቀድሞ ማውጣት የውርስ ንብረቱን ለመረከብ ወይም ለመከፋፈል የሚቀርብ ክስ በይርጋ መብቱ ሳይታገድ በማናቸውም ጊዜ ለማቅረብ የሚያስችል ሕጋዊ ውጤት ያለው መሆን አለመሆኑን?
2. ከዚህ በፊት ሁለት አይነት የሰበር ዉሳኔዎች ነበሩ፡-
አንደኛው፡- በመ/ቁ. 186329 (የመ/ቁ. 26422፣ 20295፣ 26422-የፍ/ሕ/ቁ. 1000 መሰረት በማድረግ 3 ዓመት የይርጋ ጊዜ
ሁለተኛው፡- በመ/ቁ. 205248 (መ/ቁ. 44237፣38533-የጊዜ ገደብ የሌለው
3. ይህን ቅራኔ በማስቀረትና ወጥ የሆነ ትርጉም ለመስጠት ጉዳዩ በሰባት ዳኞች ችሎት ታይቶል፡
4. ጥቅም ላይ የዋሉ ድንጋጌዮች፡-
የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1000 እና 1062 ሲሆኑ
የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1062
ወራሾች በማናቸውም ጊዜ የውርስ ሐብት እንዲከፋፈል መጠየቅ እንደሚችሉ
የውርስ ማጣራት ተከናውኖ ካለቀ በኋላ
ከፍ/ሕ/ቁ. 1053የውርስ ማጣራት ተጠናቆ- የሚተርፈው ንብረት ከወራሽ ሐብት ጋር የሚቀላቀል ወይም በወራሾች በጋራ እንደሚያዝ
የጋራ የሆነ ንብረትን ለመከፋፈል የሚቀርብ ጥያቄን የሚመለከት ነው
ስለክፍያ ጊዜ የሚያወራ ድንጋጌሲሆን በይዘቱ ስለይርጋ ሳይሆን የጋራ ወራሾች ውርሱን እንከፋፈል ብለው የሚጠቁበትን ጊዜ፣ ማብቂውን ሳይሆን መጀመሪያን የሚበይን ነው
ወራሾችም ሆነ የውርሱ ሐብት ተለይቷል፣
በጋራ የሚያዘውና የግል የሚሆነው ታውቋል
ዕዳም ሆነ የኑዛዜ ስጦታዎች ተከፍለዋል
የቀረበው የተጣራ የውርስ ሐብት የጋራ በመሆኑ ድንጋጌው የሚያወራው ይህ በጋራ የተያዘ ሐብት ስለሚከፋፈልበት ሁኔታ ነው
በነጠላ ውርስን ሳይሆን የጋራ ባለሐብትነትም/1060/
ጉዳይ በፍ/ሕ/ቁ. 1000 የሚሸፈን አይሆንም
የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1000
5. በፍ/ሕ/ቁጥር 996 የተመለከተው የምስክር ወረቀት የሚፈጥረው መብት በአንቀጽ 1062 የጋራ ባለሐብት መሆንን የሚጨምር መሆን አለመሆን፡-የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 996-998 ከ1900ዉ የጀርመን የፍትሐብሔር ሕግ አነጻጽሮ ሲተነትን
የምስክር ወረቀት በሁለቱም አገሮች ወራሽነትንና የውርስ ድርሻን የሚያረጋግጥ ነዉ፡፡
ከሟች ወደ ወራሾች ንብረት የሚተላለፍባቸዉ መንገዶች
ሞትን ተከትሎ ንብረቱ ወዲያውኑ ለሕጋዊ ወራሾች የሚተላለፍበት
ንብረቱ የወራሾች ፈቃደኝነት ተረጋግጦ የሚደረግ ዝውውር
የንብረት መተላለፊያ መንገድ የውርስ ንብረቱ በጊዜያዊነት በሌላ ሰው እጅ ቆይቶ የማጣራት ሂደቱ ካለቀ በኋላ የሚደረግ ዝውውር
የኢትዩጵያ ሕግ
የንብረት መተላለፊያ መንገድ የውርስ ንብረቱ በጊዜያዊነት በሌላ ሰው እጅ ቆይቶ የማጣራት ሂደቱ ካለቀ በኋላ የሚደረግ ዝውውር
ሶስተኛ ወገን በአጣሪነት ተሳትፎበት የተረፈውን ንብረት የሚያስተላልፍበት
በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 996
ወራሽነትንና ወራሽነቱ የተረጋገጠለት ሰው ከውርስ የሚያገኘውን ድርሻ ሲመለክት
በውጤት(የፍ/ሕ/ቁ. 997) ደረጃ ግን ወራሽ ስለመሆን ግምት የሚያስወስድ ብቻ ነው፡፡
ወዲያውኑ በውርስ ንብረቱ ላይ መብትየሚረጋግጥ አይደለም፡፡
ከንብረት ጋር በተያያዘ የሚፈጥረው መብት ስለመኖሩ የሚናገረው ነገርም የለም፡፡
(የፍ/ህ/ቁ 1083) ስንመለከት፡- የውርስ ማጣራት አልቆ የተረፈው ንብረት የጋራ መሆኑ ከተረጋገጠ በኃላ ንብረት ክፍፍል በሚጠየቅበት ጊዜ የወራሾችን ትክክለኛ ድርሻ የሚለየው በጋራ በሚመረጥ ሰው ወይም በፍርድ ቤት በሚሾም ባለሙያ ሊሆን እንደሚችል መመልከቱ የወራሽነት ምስክር ወረቀት የመጨረሻ ውሳኔ ተደርጎ የሚወሰድ አለመሆኑን ያሳያል፡
ግምት የሚሰወስድ እንጂ የንብረት መብት የንብረት መብት አይፈጥርም፡፡
የወራሽነት የምስክር ወረቀት የሚያስገኘው መብት የመውረስ ወይም የወራሽነት መብት ብቻ ነው፡፡/1124(1 እና 2)
የወራሽነት መብት ውርስ በማጣራት ሂደት ለመሳተፍ እና ከውርስ ማጣራት የሚገኘውን ሐብት ለመካፈል የሚያስችል እና የውርስ መጣራትን የማይጠብቁ መብቶችን (እንደ ጡረታ ክፍያ፣ የሰራተኛ ጉዳት ካሳ፣ በተወሰነ ሁኔታ የሕይወት መድን ክፍያ፣ ወዘተ) ለመጠቀም የሚያስችል ነው፡፡
በፍ/ህ/ቁ.1053 መሰረት፡-ወራሽ የሆነ ሰው የውርስ ሐብቱ ላይ መብት የሚገኘው የማጣራት ሂደቱ መጠናቀቅን ተከትሎ መሆኑን ነዉ፡፡
የክፍፍል ጥያቄ የሚቀርበው-የማጣራት ሂደቱ ሲጠናቀቅ/1062/
ውርሱ እስከሚጣራ ድረስ የተለየ ንብረት ሆኖ እንደሚቆጠር/942/
ለገንዘብ ጠያቂዎች ደግሞ ዋስትናቸው/943)
ወራሾች አጣሪ እንደሆኑ የሚቆጠሩት /947/
በውርስ ማጣራት ሂደት በውርሱ ሐብት የሚደርሳቸውን ሰዎች መለየት ዋና ተግባር በመሆኑ/1062/
ጥያቄ ሲነሳበት የምስክር ወረቀቱ ሊሰረዝ የሚችል የመጨረሻ ፍርድ ተብሎ ሊወሰድ የማይችል ነው /998/
ስለዚህ የወራሽነት የምስክር ወረቀት ንብረት ላይ የማያርፍ ከዛ በመለስ ያለ የወራሽነት መብት የሚያስገኝ በመሆኑ ከንብረት መብት ጋር አያይዞ ውጤት መስጠት አያስችልም፡፡
ይህን ማስረጃ በመያዙ ብቻ የንብረት መብት ጥያቄ ለማንሳት የሚያስችለው ስላልሆነ የፍ/ሕ/ቁጥር 1062 ለሚታየው ጉዳይ ተገቢነት ያለው ድንጋጌ አይሆንም
6. የወራሽነት የምስክር ወረቀትና የወራሽነት ጥያቄ
የወራሽነት የምስክር ወረቀት
የተደነገገ የይርጋ ገደብ የለም፡፡
ፍርድ ቤቶች አንድ ሰው ከሟች ጋር ባለው ዝምድና ወይም በኑዛዜ መነሻነት ወራሽ መሆኑን በማረጋገጥ የሚሰጡት ውሳኔ ነው፡፡
ሕጉ የሚወሰደውን ግምት የሚያረጋግጥ እንጂ በተከራካሪ ወገኖች መካከል ላለ ክርክር መፍትሔ የሚሰጥ አይደለም፡፡
የወራሽነት ጥያቄ
አንድ ሰው ከሟች ንብረት ለመውረስ የሚያቀርበው ክስ ነው፡፡
አንድ ሰው ወራሽነቱ እንዲታወቅለትና የተወሰዱት የውርስ ንብረቶች እንዲመለስለት የሚያቀርበው ክስ ነው፡፡/999/
ሁለት ነገሮች ያረጋግጣል፡፡የህግ ሁኔታና የንብረት መብት ነው፡
የንብረት ክርክርም በውስጡ ይይዛል
የክሱን ውጤትም ተከሳሹ በእጁ ያለውን ንብረት እንዲመልስ የሚስደርግ ነዉ/1001/
ስለዚህ እውነተኛ ወራሽ መሆንን ለማረጋገጥና የውርስ ንብረት ለማስለቀቅ የሚቀርብ ክስ ነው፡፡
1000 በግልጽ የሚናገረው የወራሽነት ጥያቄ ተቀባይነት የማያገኝበትን ጊዜ አለዉ፡፡
የይርጋ ጊዜው ቅድመ ሁኔታ፡-
ይርጋዉ የሚቆጠረዉ፡-ከሳሽ መብቱንና የውርስ ንብረቶችቹ በተከሳሹ መያዛቸውን ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡
ስለወራሽነት መብቱ እና ስለንብረቱ
ሟች ከሞተበት ወይም ከሳሽ ስለመብቱ መስራት ከቻለበት ቀን አንስቶ በአስራአምስት ዓመታት ውስጥ/1001(2)/
ስለዚህ የይርጋ ድንጋጌ ይዘትም የሚያወራው ስለምስክር ወረቀቱ ሳይሆን ስለወራሽነት ጥያቄ ነው፡፡
7. ማጠቃለያ፡-
1. ወራሽነት የምስክር ወረቀት የተሰጠው ውጤት፡-ወራሽ ተደርጎ ከመገመት ባለፈ የንብረት መብት የማይፈጥር ነዉ፡፡
2. የወራሽነት ጥያቄ በጽንሰ ሐሳብም ሆነ በውጤት የተለየ በመሆኑና በይዘቱ በተመለከተው አግባብ የሚቀርብ ጥያቄ የጊዜ ገደብ የተቀመጠለት በመሆኑ የይርጋ ጊዜው ተፈጻሚነት በወራሽነት ጥያቄ ላይ ነው፡፡
3. ስለሆነም የወራሽነት ማስረጃ መያዝ አለመያዝ ልዩነት ሳይኖረው በተጠቀሰው የሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ የወራሽነት ጥያቄ ካልቀረበ ክሱ በይርጋ የሚታገድ ይሆናል፡፡
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: