Популярное

Музыка Кино и Анимация Автомобили Животные Спорт Путешествия Игры Юмор

Интересные видео

2025 Сериалы Трейлеры Новости Как сделать Видеоуроки Diy своими руками

Топ запросов

смотреть а4 schoolboy runaway турецкий сериал смотреть мультфильмы эдисон
dTub
Скачать

የሕዳር 12ሥንክሳር

Автор: kesisephrem

Загружено: 2025-11-20

Просмотров: 9193

Описание:

ስንክሳር ዘወርኀ ኅዳር 12

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ኅዳር አሥራ ሁለት በዚች ቀን ለሰው ወገን የሚያዝንና የሚራራ በእግዚአብሔር ጌትነት ዙፋን ፊት ሁልጊዜ በመቆም ለፍጥረቱ ሁሉ የሚማልድ የመላእክት አለቃ በሰማያትም ለሚኖሩ ኃይሎች ሁሉ አለቃቸው ለሆነ ለቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው ።

ይህም በንጉሥ ጭፍራ አምሳል በታላቅ ክብር ሁኖ የነዌ ልጅ ኢያሱ ያየው ነው ከእኛ ሰዎች ወገን ነህን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ አለው ። እኔስ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ አሁንም ወዳንተ መጥቻለሁ አለው ።

ኢያሱም ወደ ምድር በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደለትና በእኔ በባሪያህ ዘንድ ምን አቁሞሃል አለው ። የእግዚአብሔርየሠራዊቱም አለቃ ሚካኤል ኢያሱን የቆምክባት ምድርየከበረች ቦታ ናትና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ አለው ኢያሱም እንዳለው አደረገ ።

እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለው በውስጧ ያለውን ንጉሧን ከኃያላኑና ከአርበኞቹ ጋር በእጃችሁ ኢያሪኮን እነሆ አስገባታለሁ ። ይህም የከበረ መልአክ ከቅዱሳን ሰማዕታት ጋርበመሆን ገድላቸውን እስከ ሚፈጽሙ የሚያጸናቸውና የሚያስታግሣቸው ነው ።

ስለዚህም ስለ ልዕልናውና ስለ አማላጅነቱ በየወሩ በዐሥራ ሁለት ቀን ለመታሰቢያው በዓል ተሠራለት እርሱ ስለ እኛ የምድሩን ፍሬ ይባርክልን ዘንድ ዝናሙንም በጊዜው እንዲአወርድልን የወንዙንም ውኃ እንዲመላልን ነፋሱንም የምሕረት ነፋስ እንዲአደርግልን ሁሉንም የተስተካከለ እንዲአደርግልን ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ይማልድልናልና

እንዲህም ሆነ የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ ስሙ ዱራታዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ የሚስቱም ስም ቴዎብስታ ነው እነርሱም ሁልጊዜ ያለ ማቋረጥ የዚህን የከበረ መልአክየሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ ያደርጉ ነበር ከዚህም በኋላ በሀገር ውስጥ ችግር በሆነ ጊዜ ገንዘባቸው አለቀ ለዚህም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ለበዓሉ መታሰቢያ የሚያደርጉት አጡ ዱራታዎስም ሽጦ ለበዓሉ መታሰቢያ ያደርገው ዘንድ የእርሱን ልብስና የሚስቱን ልብስ ይዞ ወጥቶ ሔደ ።

የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም በታላቅ መኰንን አምሳል ለዱራታዎስ ተገለጠለት ወደ ባለ በጎች ሒዶ በእርሱ ዋስትና በአንድ ዲናር አንድ በግ እንዲወስድ ሁለተኛም ወደ ዓሣ አጥማጅ ሒዶ አንድ ዓሣ እንዲወስድ ግን መልአኩ ወደ ቤቱ ሳይደርስ የዓሣውን ሆድ እንዳይቀድ ወደ ባለ ሥንዴም እንዲሔድና የሚሻውን እንዲሁ በርሱ ዋስትና እንዲወስድ አዘዘው ዱራታዎስም ቅዱስ ሚካኤል እንዳዘዘው አደረገ ።

ወደ ቤቱም በተመለሰ ጊዜ በረከትን ሁሉ ቤቱ ተመልቶ አገኘው ። እጅግም አደነቀ የዚህንም የከበረ መልአክ የበዓሉን መታሰቢያ እንዳስለመደ አደረገ ። የተራቡ ድኆችን ሁሉንም ጠርቶ መገባቸውና ወደየቤታቸው አሰናበታቸው ።

ከዚህም በኃላ ለዱራታዎስና ለሚስቱ ቅዱስ ሚካኤል ሁለተኛ ተገለጠላቸው ። ዱራታዎስንም የዓሣውን ሆድ እንዲሠነጥቅ አዘዘው ። በሠነጠቀውም ጊዜ ሦስት መቶ የወርቅ ዲናርበዓሣው ሆድ ተገኘ ። ቅዱስ ሚካኤልም ዱራታዎስንና ቴዎብስታን እንዲህ አላቸው ከዚህ ዲናር ወስዳችሁ ለባለ በጉ

ለባለ ዓሣውና ለባለ ሥንዴው ዕዳችሁን ክፈሉ የቀረውም ለፍላጎታችሁ ይሁናችሁ እግዚአብሔር አስቧችኋልና በጎ ሥራችሁን መሥዋዕታችሁንና ምጽዋታችሁን አስቦ በዚህ ዓለም አሳመረላችሁ ። በኋላኛውም መንግሥተ ሰማያትን አዘጋጅቶላችኋል ።
እነርሱም ሲሰሙ ስለዚህ ነገር ደነገጡ ። እርሱም ከመከራችሁ ሁሉ ያዳንኳችሁ የመላእክት አለቃ እኔ ሚካኤል ነኝ መሥዋዕታችሁንና ምጽዋታችሁን ወደ እግዚአብሔር ፊት ያሳረግሁ እኔ ነኝ አሁንም በዚህ ዓለም ከበጎ ነገር እንድታጡ አላደርጋችሁም አላቸው ። ይህንንም ብሎ ወደ ሰማያት ወጣ ። እነርሱም ሰገዱለት ተአምራቱም የማይቁጠር ብዙ ነው ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ በከበረ መልአክ ጸሎትና አማላጅነት ይማረን ለዘላለሙ አሜን ።

በዚችም ዕለት የመጥምቁ ዮሐንስ ራስ በደብረ ማህው የታየችበት ነው በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።

በዚችም ቀን የኢትዮጵያ ንጉሥ የጻድቁ በእደ ማርያም የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው ።

በዚችም ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ስልሳ ሦስተኛ የሆነ የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ፊላታዎስ አረፈ ። በሹመቱ ወራትም የኢትዮጵያ ንጉሥ ወደ ኖባ ንጉሥ ወደ ጊዮርጊስ እንዲህ ብሎ የመልእክት ደብዳቤ ጻፈ ወንድሜ ሆይከሊቀ ጳጳሳት ቆዝሞስ ጊዜ ጀምሮ ለረጅም ጊዜ ጳጳስ ስለ ሌለን እኛ በታላቅ ችግር ውስጥ እንዳለን ዕወቅ ።

ይህም የሆነው ተንኰለኛው ሚናስ በተንኰልና በሐሰት ነገርየከበረ ጳጳሳችንን ጴጥሮስን ከሹመቱ ወንበር እንዲሰደድ ስለ አደረገው ነው ። ስለዚህ አምስት ሊቃነ ጳጳሳት እስቲአልፉ ለሀገራችን ጳጳስ አልተላከልንም ።

አሁንም ስለ እግዚአብሔር ብለህ ስለ ቀናች ሃይማኖትም በድካም ከእኛ ጋር አንድ በመሆን ስለእኛ ወደ ግብጽ ሊቀ ጳጰሳት ወደ ቅዱስ ፊላታዎስ ጳጳስ ይልክልን ዘንድ ከራስህ ደብዳቤ እንድትጽፍለት እለምንሃለሁ የሚል ነበር ።

በዚያንም ጊዜ የኖባ ንጉሥ ጊዮርጊስ ለኢትዮጵያ አገር ጳጳስን ይሾምላቸው ዘንድ የልመና ደብዳቤ ወደ አባ ፊላታዎስ ጻፈ

ይህ ቅዱስ ፊላታዎስም ልመናውን ተቀብሎ ከአስቄጥስ ገዳም ስሙ ዳንኤል የሚባል አንድ ጻድቅ መነኰስ አስመጣ እርሱን ጵጵስና ሹሞ ወደ ኢትዮጵያ አገር ላከው ወደ እነሱም በደረሰ ጊዜ የኢትዮጵያ ሰዎች በታላቅ ደስታ ተቀበሉት ። በዚህም አባት ፊላታዎስ ዘመን ብዙ ተአምራት ተገልጠዋል በሰላምም አረፈ ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ፊላታዎስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።

ኅዳር ፲፪ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

፩.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት

፪.ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ

፫.ቅዱሳን ዱራታኦስና ቴዎብስታ

፬.አፄ በዕደ ማርያም ጻድቅ

፭.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ

፮.ቅዱስ ባሕራን ቀሲስ

፯.አባ ፊላታዎስ ሊቀ ዻዻሳት

ወርኀዊ በዓላት

፩.ቅዱስ ላሊበላ ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮዽያ

፪.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ

፫.ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ ሰማዕት

፬.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ

አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ

፮.ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ

፯.ቅዱስ ድሜጥሮስ ሊቅ

በሰማይም ሰልፍ ሆነ ። ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ ። ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ ። አልቻላቸውምም ። ከዚያም ወዲያ በሰማይ ሥፍራ አልተገኘላቸውም ። ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ወደ ምድር ተጣለ ። ራዕይ. ፲፪ ፥ 2

‪@እናታችንማርያምሆይእንወድ‬​ ‪@kesishenokweldemariam2240‬​ ‪@EfoyZeOrthodox‬

የሕዳር 12ሥንክሳር

Поделиться в:

Доступные форматы для скачивания:

Скачать видео mp4

  • Информация по загрузке:

Скачать аудио mp3

Похожие видео

🔴የቅዱስ ሚካኤል መዝሙሮች ስብስብ/saint micahel mezmur collection/#mezmur #orthodoxmezmur@መዝሙረ ዳዊት ሚዲያ Mezmure-Dawit Media

🔴የቅዱስ ሚካኤል መዝሙሮች ስብስብ/saint micahel mezmur collection/#mezmur #orthodoxmezmur@መዝሙረ ዳዊት ሚዲያ Mezmure-Dawit Media

ሰላምን ዕዉትን መዓልቲ ክንውዕል #LbonaMedia

ሰላምን ዕዉትን መዓልቲ ክንውዕል #LbonaMedia

🔴NEW 🔴 አዲስ ዝማሬ

🔴NEW 🔴 አዲስ ዝማሬ " ማር ሚካኤል " | Mar Michael | ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ @-mahtot

🔴የእመቤታች ቅድስት ድንግል ማርያም  መዝሙሮች ስብስብ/St.Mariam mezmur collection 2025#mezmur #orthodoxmezmur

🔴የእመቤታች ቅድስት ድንግል ማርያም መዝሙሮች ስብስብ/St.Mariam mezmur collection 2025#mezmur #orthodoxmezmur

⛔ ቅዱስ ሚካኤል ማን ነው ? 🤔 የ ሚካኤል ታሪክ / የ ህዳር 12 አመታዊ ክብረ በዓል / የ አባ ገብረ ኪዳን ስብከት 🙏 ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ

⛔ ቅዱስ ሚካኤል ማን ነው ? 🤔 የ ሚካኤል ታሪክ / የ ህዳር 12 አመታዊ ክብረ በዓል / የ አባ ገብረ ኪዳን ስብከት 🙏 ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ

ዓለም ጉድ ዘበለ ሕብረት ማርያም ጉጉሳ መቐለ

ዓለም ጉድ ዘበለ ሕብረት ማርያም ጉጉሳ መቐለ

7ተ ሰዓታት ጸሎት ኣብ መዓልቲ! ናይ ንግሆ ጸሎት New Eritrean tigrigina morning prayer ፡ ነሕዋትኩም ውን ስደዱሎም ብጸሎት ክባረኹ።

7ተ ሰዓታት ጸሎት ኣብ መዓልቲ! ናይ ንግሆ ጸሎት New Eritrean tigrigina morning prayer ፡ ነሕዋትኩም ውን ስደዱሎም ብጸሎት ክባረኹ።

በማይነገር ስጦታ || ምስጢረኛዬ || ማር ሚካኤል ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ@21media27 @Mutansa_Mar_St_Michael

በማይነገር ስጦታ || ምስጢረኛዬ || ማር ሚካኤል ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ@21media27 @Mutansa_Mar_St_Michael

ህዳር 12 ቅዱስ ሚካኤል | ድርሳነ ሚካኤል | Ethiopia Orthodox Tewahedo | Dirsane Mikael

ህዳር 12 ቅዱስ ሚካኤል | ድርሳነ ሚካኤል | Ethiopia Orthodox Tewahedo | Dirsane Mikael

መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit  - ረቡዕ (መዝ 61-80)

መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit - ረቡዕ (መዝ 61-80)

ሚካኤል ይለይብኛል|| የእግዚአብሔር መልዓክ|| የስሙ ትርጓሜ || #የቅዱስ_ሚካኤል መዝሙሮች በተዋዳጅ ዘማሪያን

ሚካኤል ይለይብኛል|| የእግዚአብሔር መልዓክ|| የስሙ ትርጓሜ || #የቅዱስ_ሚካኤል መዝሙሮች በተዋዳጅ ዘማሪያን

የቅዱስ ሚካኤል መዝሙሮች ስብስብ | Ethiopian Orthodox Mezmur Collection | St. Michael ye mikayel mezmur

የቅዱስ ሚካኤል መዝሙሮች ስብስብ | Ethiopian Orthodox Mezmur Collection | St. Michael ye mikayel mezmur

የኪዳነ ምህረት ተወዳጅ መዝሙሮች || Ye kidane mihiret mezmur

የኪዳነ ምህረት ተወዳጅ መዝሙሮች || Ye kidane mihiret mezmur

🛑አዲስስብከት//መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ያልደረሰለት ማን አለ የጭንቅ ደራሻችን ሚካኤል እንባ አባሻችን ሚካኤል ድንቅ ትምህርት //በመልአከ ኤዶም አባ ሕርያቆስ

🛑አዲስስብከት//መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ያልደረሰለት ማን አለ የጭንቅ ደራሻችን ሚካኤል እንባ አባሻችን ሚካኤል ድንቅ ትምህርት //በመልአከ ኤዶም አባ ሕርያቆስ

በዘላለም ኪዳን ቁጥር ፬ (4) -  ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን (Full Album)

በዘላለም ኪዳን ቁጥር ፬ (4) - ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን (Full Album)

የቅዱስ ሚካኤል መዝሙሮች ስብስብ

የቅዱስ ሚካኤል መዝሙሮች ስብስብ

#ዳናይት የአቤል መክብብ መዝሙሮች - Abel Mekbib Mezmur Collection

#ዳናይት የአቤል መክብብ መዝሙሮች - Abel Mekbib Mezmur Collection

ተስፋ🙏 ተስፋ አትቁረጡ! እጅግ ድንቅ ትምህርት በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን #Orthodox #tewahedo #ተስፋ #Tesfa #Hope #አባገብረኪዳን

ተስፋ🙏 ተስፋ አትቁረጡ! እጅግ ድንቅ ትምህርት በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን #Orthodox #tewahedo #ተስፋ #Tesfa #Hope #አባገብረኪዳን

የእመቤታችን ጥዑም ዝማሬዎች

የእመቤታችን ጥዑም ዝማሬዎች "ስብስብ | በሊቀ ልሣናት ቸርነት ሰናይ| Ethiopian Orthodox Tewahdo Mezmur 2023 - Chernet Senai

ነይ ነይ እምዬ ማርያም || ገብርኤል በሰማይ || በዘባነ ኪሩብ || ዘማሪ ዲያቆን ፍሬዘር ደሳለኝ@21media27

ነይ ነይ እምዬ ማርያም || ገብርኤል በሰማይ || በዘባነ ኪሩብ || ዘማሪ ዲያቆን ፍሬዘር ደሳለኝ@21media27

© 2025 dtub. Все права защищены.

  • Контакты
  • О нас
  • Политика конфиденциальности

Контакты для правообладателей: [email protected]