ABEJEHU | አበጀሁ Mikiyas Ahmed | ሚኪያስ አህመድ Original Song
Автор: Mikiyas Ahmed
Загружено: 2025-11-25
Просмотров: 4129
መጣህልኝ በቤቴ ከማልጠብቀው ቦታ
በር አንኳኳህ ከደጄ ልትቀይር የኔን እጣ
አቤት ፍቅርህ ትልቀቱ እኔን የታገስክበት
ሀጢያት ያቅበዘበዘው ታሪኬን ለወጥክበት
አጠናኸው እጣዬን
አበጀህ ዘላለሜን
ገመዴ ምቹ ስፍራ
ወደቀችልኝ አምራ
አበጀሁ አበጀሁ
ጌታዬ አደረኩህ
አበጀው አበጀው
ኢየሱስ ኢየሱስ አልኩህ
የህይወቴ ትርጉም በቤቴ አስገባሁህ
1-በምድር እጣ ርስት እንደሌለው
ሽልማት ጌጡ ጌታ እንደሆነው
እንደ እንግዳ ሰው በዚህ ኖራለሁ
ርስቴን በላይ ሄጄ ወርሳለሁ
አበጀሁ
አበጀሁ አበጀሁ
ጌታዬ አደረኩህ
አበጀው አበጀው
ኢየሱስ ኢየሱስ አልኩህ
የህይወቴን ትርጉም በቤቴ አስገባሁህ
2-ለጠፊው አለም ጌታን ያመነ
እንደሚል ቃሉ ያ ሰው ተሞኘ
ለማይጠፋና እድፈት ለሌለው
ለሰማይ ተስፋ ጌታን ያመነው
አበጀው
አበጀው አበጀው ዘላለሙ አማረ
አበጀው አበጀው ህይወቱ ሰመረ
የሰማዩን ኑሮ በጊዜ ጀመረ
ተቀብዬ ሳስገባህም ህይወቴ አማረ ባንተ
ነፍሴ ድና ቀረችብህ እሰይ እንኳን አመንኩህ
አበጀሁ አበጀሁ
ጌታዬ አደረኩህ
አበጀው አበጀው
ኢየሱስ ኢየሱስ አልኩህ
የህይወቴ ትርጉም በቤቴ አስገባሁህ
This is a song about how the person who has made Jesus his Lord has made a profit beyond measure. It is a song that highlights the fact that God is our ultimate treasure, and living for Him is a privilege.
ይህ መዝሙር ኢየሱስን ጌታው ያደረገ ሰው ምን ይህል አትራፊ እንደሆነ የሚገልፅ መዝሙር ነው። እግዚአብሔር የመጨረሻ ሀብታችን መሆኑን የሚያጎላ መዝሙር ነው ፤ ለእርሱ መኖር ደግሞ መታደል ነው።
-----
Don't forget to subscribe!
#mezmur #ethiopianmezmur #abejew #abejehu #mikiyasahmed
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: