በህይወት ግባ በእልልታ የዚህ ሁሉ አለኝታ//አስደናቂው የጥምቀት ትውስታ//ጥር 2017 ዓ.ም
Автор: YehuluSaccos
Загружено: 2025-01-19
Просмотров: 133
📌በኢትዮጲያ ውስጥ ከሚወደዱ እና የተለየ ቦታ ከሚሰጣቸው ወራቶች መሃከል የ ጥር ወር አንዱ ነው፡፡
ህፃን እና አዋቂው ፤ ሴት እና ወንዱ
በአንድ ላይ በህብር ቀለም እና በአልባሳት የሚያጌጡበት ለየት ያለ ምስጋና እና ሀይማኖታዊ ክንውን የሚስተዋልበት ወር ነው፡፡
የጥምቀት በዓል ሁል ጊዜ ልዩ እና ደማቅ ሲሆን ከዋዜማው ጀምሮ እስከ በዓሉ መገባደጃ፤ ከከተራው እስከ አስተሰርዮ የተለያዩ ሀያማኖታዊ ክንውኖች እና በዓላዊ ጨዋታዎችን ማየት የተለመደ ነው፡፡
ወጣቱ ያለውን አቅም እና ጥንካሬ ለመልካም የሚጠቀምበት በዓሉ ደምቆ እንዲከበር የድርሻውን የሚወጣበት ሲሆን ከተማዎች ተውበው እና ደምቀው መመልከት የተለመደ ነው፡፡
ከማይዳሰሱ ታሪካዊ ቅርፆች መሃከል በዩኔስኮ በይፋ የተመዘገበው ታህሳስ 2 2012 እለተ ሀሙስ ቀን ነበር፡፡
ከበዓሉ ቀድመው ሁሉም በየዐቅሙ አምረው እና ደምቀው ለመታየት መሰናዳት ይጀምራሉ፡፡
ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ ሲባል በምክንያት ነው፡፡
ያለው በአዲስ ልብስ ፤ ያጣው ባለው ደምቆ እና ተውቦ ለመታየት ሲሯሯጥ ማየት የተለመደ ነው፡፡
ሴቶቹ በሚያምር አልባሳት የሚዋቡበት ልዩ በሆነው የፀጉር አሰራር እና ለውበት ማድመቂያ በሚጠቀሙበት ጌጣጌጥ ውብ ሆነው የሚታዩበት ፡
ወንዱም የወደዳትን በእጁ ለማስገባት ከእጁ ሎሚ አልያም ፕሪም ማየት የተለመደ ነው፡፡
ድሮ ድሮ ይህ የጥምቀት በዓል ለብዙዎች ጎጆ መቃናት እና ትዳር የራሱ የሆነ ድርሻ ነበረው፡፡
አሁን አሁን ይህ የሎሚ መወራወር በዓላችን ቢቀዘቅዝም አልፎ አልፎ ግን ይስተዋላል፡፡
በታቦት አጀብ ውስጥ ሀይማኖታዊ ዝማሬ የሚዘምሩ የተለያዩ የበዓሉ ድምቀት የሆኑ እንቅስቃሴዎችን የሚያሳዩ መዘምራንን ማየት በፅናፅል እና በከበሮ ምስጋናቸውን የሚያቀርቡ የቤተክርስቲያን አገልጋዮችን በሀሴት ሲያዜሙ መመልከት የተለመደ ነው፡፡
ትከሻቸውን በእስክስታ የሚፈትሹ ወጣቶች …. ከዳር ቆመው በጭብጨባ የሚያደምቁ ብዙ ናቸው፡፡
ለጥምቀት በዓል ያልዘፈነች ቆንጆ ፡ ቆማ ትቀራለች እንደ ዘላን ጎጆ የሚባለውም ለዚሁ ነው፡፡
ድምፅ ያለው በማዜም፣ እስክስታ የሚቀናው በእስክስታ በተለያዩ ክንውኖች ደምቀው ይታያሉ፡፡
ገጣሚው ወንድሜ እንዲህ ይላል ይሄኔ..
አረ አዘቀዘቀች ፀሀይ የቆንጆ አንገት ልታይ በማለት አድናቆቱን ይችራል፡፡
በዳር ሆኖ በዝምታ ለሚታዘበው ጭብጨባ ሆነ እልልታ ለነፈገው / ገጣሚው ወንድሜ አለው ቅኔ…
የዛሬው ኩራት ለማን ነው፤ ሁሉም የተሰራው ለአፈር ነው፡፡
እርሱ አይደል እንዴ ባለቤቱ ቀጭን ኩታ ለብሶ ምንድነው ኩራቱ!
በማለት ይወርፋል፡፡
እማሆይ በድካም አረፍ ያሉእንደ ሆን..
አረ ተይ እማሆይ ተነሺ መድሃኒያለም ቆሞ ምነው
ቁጭ አልሽ፤ እያለ የማሆይን ድካም በወኔ ይቀይራል፡፡
እማሆይ በወኔ ነጠላቸውን ወገባቸው ላይ አደግድገው ያዜማሉ፡፡
በእልልታ ያመሰግናሉ፡፡
ይህን ያየው ቀድሞ የወረፈው ገጣሚው ወንድሜ በወኔ ስታዜም ላያት እማሆይ በደስታ እንዲህ ይላል..
እማሆይ ባለአበባ ከላይ ቁብ ከታች ዳባ፡
በታቦት አጀብ አልሞላለት ብሎ ቤቱ ለቀረው ወዳጄ ገጣሚው ወንድሜ አለው ሌላ ቅኔ
ከቤት ይውላል ሞኛ ሞኝ እናት እና ልጁ በጥምቀት ሲገኙ፤
እኛስ መልካም ገበያ ገበየን እናት እና ልጁን በአንድ ላይ አየን፤
አሞራ በሰማይ ሲያየን ዋለ በነጭ ልብስ አምረው ተዋቡ እያለ፤
በህብር ሲያዜሙ እንዴት ያምሩ፤
እንዲህ ተባብረው ሲቆሙ ደጀን ሆኑ፤
ውበታቸው የአንድነት የጋራ ደምቀው ይታያሉ እንደ መስቀል ደመራ..
በህይወት ግባ በእልልታ
የዚህ ሁሉ አለኝታ በህይወት ግቢ እምዬ
እንድበላ ፈትዬ
ሲያምር ዋለ ሲታይ የሁላችንም ሲሳይ በማለት ተሳታፊውን ፣ታቦቱን የሚቀበለውን እና የሚሸኘውን ያወድሳል፡፡
ውድ የየሁሉ ቤተሰቦች
ከብዙ በጥቂቱ ስለ ጥምቀት በዓል አጋራናችሁ ፤
ስለ ተከታተላችሁን ከልብ እያመሰገንን
መልካም የጥምቀት በዓል ተመኘን
ቸር ቆዩልን!
አካታች እድገት ለሁሉ በሁሉ!
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: