"መቼ ነው ጌታ" ዘማሪት ፋንቱ ወልዴ "Meche New Geta" Zemarit Fantu Wolde
Автор: ሙራደ ቃል Murade Qal
Загружено: 2019-08-27
Просмотров: 5648
መቼ ነው ጌታ
መቼ ነው ጌታ ኧረ መቼ ነው
መቼ ነው ጌታዬ እንደ ቃልህ የሚሆን ጉዞዬ /፪/
አልተማርኩም አልል አሰተምረኸኛል /፪/
ቃልህን እንደ ወተት አጠጥተኸኛል /፪/
የታል አኗኗሬ አንተን የሚመስለው /፪/
በልማድ ሕይወት ነው የምመላለሰው /፪/
ይህ አንደበቴማ በቃልህ ሠልጥኗል /፪/
ልቦናዬ ካንተ ከፊትህ ኮብልሏል /፪/
አንተን እንደማውቅህ አብዝቼ ባወራም /፪/
የተዘራው ሁሉ ፍሬ አላፈራም /፪/
እዘንልኝ እና መንገዴን አቅናልኝ /፪/
የዓመፅ ሥራዬን በደሌን ተውልኝ /፪/
ቃልህ አይሰደብ በእኔ ድካም /፪/
አርመው እርሻህን መድኃኔ ዓለም /፪/
እስራቴን ፈትተህ ነፃነትን ሰጠኝ /፪/
በቀኝህ አቁመኝ ጌታ ሆይ ባርከኝ /፪/
ኃጢአት ሞትን ወልዶ እንዳያጠፋኝ /፪/
የብርሃን ፊትህ ይገለጽልኝ /፪/
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: