#ቴዎድሮስ
Автор: ጃንቶም መልቲሚዲያ-JANTOM MULTIMEDIA
Загружено: 2022-04-20
Просмотров: 2352
ቴዎድሮስ ታሪካዊ ተውኔት በሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን የተጻፈ ሲሆን፤ በወልቂጤና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ጥበባት ትምህርት ክፍሎች ተመራቂ በሆኑ ተማሪዎች በ2014 ዓ.ም መጋቢት ወር ላይ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ጥበባት ትምህርት ክፍል መድረክ ላይ የቀረበ ነው፡፡
ቴዎድሮስ ገብሬ የታሪካዊ ተውኔት ምንነትን ሲገልፅ "ታሪካዊ ተውኔት፣ "ታሪክ" እና "ሥነ ጽሑፍ" ብለን የምንጠራቸው የሁለት ሙያዎች ማደሪያ ነው፡፡ የሁለት ሙያዎች ማደሪያነቱ ለሥልቱ ከታሪክ እና ከሥነ ጽሑፍ ጥበብ የሚከፈሉ መንታ ባሕሪያትን ሲያስገኝለት፣ ባለመንታ ባሕርይነቱ ደግሞ በምላሹ ድርሰቱን ከሁለቱም ዘርፎች የሚሰምሩ መንታ ሙያዎች ይኖሩት ዘንድ ያስችለዋል፡፡ . . . "ታሪካዊው ቴዎድሮስ በሥብእናው ዝንቅነት እና አይገመቴነት(ambivalence and unpredictability) በአገራችን ታሪክ ውስጥ እጅግ አከራካሪው ንጉሥ ነው፡፡ ዝንቅነትና እና አይገመቴነት በኪነጥበብ ውስጥ ሥብእናውን ከውስን ግዜና ሥፍራ እስር አውጥቶ፣ በፍካሬ ወደሚደረስባቸው ሁለንተናዊ ፍቺዎች እና እሴቶች ማደሪያነት ለማሸጋገር የተመቸ ቢሆንም ይህ እድል በጸጋዬ ሥራ ውስጥ የባከነ ይመስለኛል፡፡ በዚህ ታሪካዊ ትራጄዲ ውስጥ ቴዎድሮስ፣ ያለምንም ትራጄዲያዊ ስሃ( hamartia/ tragic flaw) የቀረበ ትራጄዲያዊ ጀግና ነው፡፡ የቴዎድሮስ ''ፍጹምነት'' ሌሎችን ከፍ ያለ ዋጋ በማስከፈል ጭምር የተገኘ ነው፡፡ በተውኔቱ ውስጥ "ጥሩነቷን" ሁሉ የተነጠቀችውና በምትኩ የሰውን ልጅ ክፋትና ንፍገት ጠቅልላ የያዘችው እቴጌ ጥሩ ወርቅ ለዚህ ዓይነቱ ሚዛን መፋለስ ጥሩ ማሳያ ነች፡፡"
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: