Abba Dawit's song: Ye Geta Tsebay; የአባ ዳዊት ውብሸት መዝሙር፡ የጌታን ጠባይ
Автор: Abba Dawit Wubishet - አባ ዳዊት ውብሸት
Загружено: 2022-11-19
Просмотров: 1154
Abba Dawit's song: Ye Geta Tsebay;
የአባ ዳዊት ውብሸት መዝሙር፡ የጌታን ጠባይ (ፊል 2፡5)
Lyrics, የመዝሙር ግጥም
ባሕርይህ ጠባይህ የእኛ እንዲሆን ወደህ
ልብህን ቀርበነው ስናይ ውስጣችንን
ፊትህ ዝቅ ማለት እጅጉን ግድ አለን
መፈወስ የሚችል ቃልህ በቂ ሆኖት (ሉቃስ 7:1-10)
ሊታዘዝህ ቀርቦ የምትለውን በእምነት
በገሃድ መሰከርክ ያለህን አድናቆት
ደጉን ደግ ብለህ በስሙ ስትጠራው
ይህንን ባሕርይህ ሁሌ ከአንተ ያለው
ሳትሰለች ለግሰን ብርታትን የሚሰጠው 2ቴ
ለወዳጅህ ሕመም ልዩ ትኩረት ሰጥተህ
(ዮሐ 11:1-37)
ክብርህን መግለጫ አጋጣሚ አድርገህ
ዕንባህን አፈሰስክ በቦታው ተገኝተህ
የሚፈልቀው ከፍቅርህ የሚችል ማዘን
በተመስጦ ቀርበን የምናየው ማርኮን
አስችለን መልበስን ርሕሩህነትህን 2ቴ
እጅግ ጸያፍ ሆና አመንዝራ ተብላ
(ዮሐ 8:11)
ብያኔን ስትጠብቅ ከፊትህ ተጥላ
ማንም የማይምራት ሆና ተወንጅላ
ምሕረትን ሰጠሃት የሚሆን ከለላ
ይቅር ባይነትህን እንድንመርጥ ከሌላ
ፍርድን ላንተ ትተን መራኸን ለተድላ 2ቴ
ቅዱሱን በመቅደስ ሳታገኘው ቀርተህ
(ማር 11፡15-19)
ሕገወጥ ብዝበዛ አርክሶት በፊትህ
ጠንከር ቆጣ ብለህ ለቤትህ ተጨንቀህ
ለጽድቅ መቆምህ ስናየው ማርኮን
አሻፈረን ብለን ክፋትን ጠልተን
ጨከን ብሎ መፅናት ከአንተ አካፍለን 2ቴ
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: