ተወኩል ያለ ሰበብ... | ቢስሚከ ነሕያ ቆይታ ከኡስታዝ በድሩ ሁሴን ጋር | ኸሚስ ምሽት ክፍል 243 Khemis Mishit Ep. 243
Загружено: 2025-11-06
Просмотров: 21817
በቢዝነስ አሊያም በሌላ ለናንተ በጣም አስፈላጊ በሆነ ጉዳይ ሃሳብ እየተለዋወጣችሁ ሳለ፤ በመሐል ስልካችሁ ደጋግሞ ይጠራል። ላፍታ አየት ታደርጉትና ምላሽ ሳትሰጡ የጀመራችሁትን ነገር ትቀጥላላችሁ!! ምናልባትም በድጋሚ ይደወላል፡፡
አሁንም ይቀጥላል… የዚህ ስልክ ተደጋጋሚ ጥሪ እና ከበራችሁ ላይ ቆሞ የሚያንኳኳ ሰው ሁኔታ አንድ ዓይነት ይመስላል፡፡ ይህ የሥልክ ጥሪ ከወላጆቻችሁ የአንዱ ቢሆን ወይም ደጃችሁ ላይ ቆማ እስኪከፈትላት ድረስ የምትቆረቁረው እናታችሁ ብትሆን ምላሻችሁ ምን ይሆናል?
ከዕለታት በአንዱ ቀን ጁረይጅን የገጠመው ይህ ነበር፡፡ ወረት ያላሸነፈው ዓቢድ እንደነበር በታሪክ የሚነገርለት ጁረይጅ፤ ሶላት ላይ በተመስጦ ቆሞ እናት ከደጅ ቆማ ይከፍትላት ዘንድ ትጣራለች!! ጁረይጅ… ጁረይጅ…
ለሶስት ቀናት ያህል ተመላልሳ ብትጣራም ከዓቢዱ ጁረይጅ ምላሽ ስላላገኘች የወሰደችው እርምጃ ጨርሶ ከወላጅ እናት የሚጠበቅ አልነበረም፡፡ እርሷ ግን ጨክና አደረገችው፡፡ "ሰላቱን ላለመተው" ሲል ለእናቱ ጥሪ ምላሽ ያልሰጠው ጁረይጅም ለደቦ ፍርድ ቀረበ!!
የዛሬ ምሽቱ የሸይኻችን ሰዓት ወግ ይህን እጅግ አስተማሪ ታሪክ እያነሳና ከዘመኑ የስልክ አጠቃቀማችን ጋር እየነጻጸረ የሚዘልቅ ነው፡፡
በጉዞ ወደ አላህ ዝግጅቱ የተለያዩ ፌርማታዎችን እያስተዋወቀን የቆየውና፤ ለተወሰኑ ሳምንታት ጠፋ ብሎ የነበረው ተወዳጁ ኡስታዝ በድር ሁሴን ዛሬም የተወኩልን ጥልቅ ትርጓሜና የተለያየ መልክ እያስተዋወቀን ምሽቱን ከኛ ጋር ቆይታ ያደርጋል፡፡
በነገራችን ላይ ዛሬ ምሽት ኡስታዝ በድርን ብትሹ በቲቪ መስኮት፣ አሊያም በቀጥታ በሚንበር ዩቱብ እና ቲክቶክ ገፆቻችን ላይ ማግኘት ትችላላችሁ!!
ምሽት ከ02:30 ጀምሮ!
#ለይሉ_ጁምዓ_ነው!
#ፕሮግራሙ_ደግሞ_ኸሚስ_ምሽት!
ሚንበር ቲቪ!
በሚዛናዊ ዕይታ ... ዳግም ወደ ከፍታ!!
#MinberTV
#5Years
#MinberTV5thYearAnniversary
Copyright @MinberTV
👨👩👧👦 Join Minber Family 🔗 https://t.me/Minber_Merkuz_Discuss
★★★★★
የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ሊንኮች👇🏽 ይወዳጁን 👍🏽 ያጋሩ ⤴️
📍YouTube 👉 / @minbertv1
📍Facebook👉 / minbertv1
📍Telegram👉 https://t.me/minbertv
📍TikTok 👉 / minber_tv
📍Instagram 👉 / minbertv
📍X / Twitter 👉 / minbertv
📍Website 👉 https://www.minbertv.com
#MinberTV
#ሚንበር_ቲቪ
#5Years
#MinberTV5thYearAnniversary
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: