Популярное

Музыка Кино и Анимация Автомобили Животные Спорт Путешествия Игры Юмор

Интересные видео

2025 Сериалы Трейлеры Новости Как сделать Видеоуроки Diy своими руками

Топ запросов

смотреть а4 schoolboy runaway турецкий сериал смотреть мультфильмы эдисон
dTub
Скачать

አዳብና መክፈቻ በአል አናቲ // ethio gurage caltural music mesekel

Автор: ሶዶ ሚዲያ /SODO MEDIA

Загружено: 2025-09-27

Просмотров: 4147

Описание:

የሶዶ ክስታኔ ቤተ-ጉራጌ መገለጫ የሆነው አዳብና ባህላዊ ይዘቱን ጠብቆ ለቀጣይ ትውልድ እንዲተላለፍ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።

መስከረም 12/2018

አዳብና በሶዶ ክስታኔ ቤተ ጉራጌ ከመስከረም 16 እስከ ጥቅምት 5 ባሉት ቀናት ውስጥ በተለያዩ የገበያ ቦታዎችና ሀይማኖታዊ ስፍራዎች በወጣት ሴቶችና ወንዶች የሚከበር የአደባባይ ባህላዊ ክዋኔ ነው፡፡

በምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዳነ መለሰ በሶዶ ክስታኔ ቤተ_ጉራጌ የወጣቶች መተጫጫ የሆነው አዳብና በምዕራቡ አለም መጤ ባህሎች ሳይበረዝ ከትውልድ ትውልድ እንዲተላለፍና በቱሪዝሙ ዘርፍ የማይዳሰስ የአለም ቅርስነት እውቅና እንዲያገኝ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

አዳብና መስቀል ከዋለበት መስከረም 16 እስከ ጥቅምት 5 የሚከበር ሲሆን ልጃገረዶች እና ወጣት ወንዶች የሚተጫጩበት ባህል እንደሆነ ገልጸዋል።

ባህሉ በውስጡ ከያዘው ባህላዊ ክዋኔና ትዕይንት ባለፈ በዋናነት ወንዱ አይኑ ያረፈባት ሴት ከተመለከተ ሎሚ ወርውሮ ሲመታት ሎሚውን የምታነሳው ከሆነ ፈቃደኛ መሆኗን በማሳየቷ ጉዳዩ እስከ ቤተሰብ በመውሰድ ይጠናናሉ ነው ያሉት።

የማህበረሰቡ የጋብቻ ባህል በሚፈቅደው መሰረት ወደ ሴቷ ቤት ሽማግሌ ተልኮ ተቀባይነት ካገኘ በጽኑ መሰረት ላይ የተገነባ ጋብቻ ስርዓቱን ጠብቆ እንዲመሰረት የሚያግዝ ድንቅ ባህል መሆኑ አስረድተዋል።

ሊቀ ሂሩያን ብርሃኑ ዋካ እና አቶ አማረ ሀይሉ በሰጡት ማብራርያ አዳብና አዳምና ሄዋን የሚል ጥሬ ትርጉም የያዘ ወጣት ወንዶችና ሴቶች ለመተጫጨት የሚገናኙበት እንዲሁም በተለያዩ ባህላዊ ጨዋታዎች የእርስ በእርስ ግንኙነታቸው የሚያጠናክሩበት ጥንተ መሰረት ያለው የማህበረሰቡ ድንቅ ባህል ነው ብለዋል።

በአዳብና ስነስርዓት የክረምቱ ጭጋግ ተገፎ መስከረም ሲጠባ ሴት ልጃገረዶች ጸጉራቸው በመሰራት መልካም መዓዛን ለመፍጠር አደስና ቅቤ ተቀብተው ለበዓሉ የሚሆን ባህላዊ ልብስ በመልበስ ተውበው በየአቅጣጫው "ሀዬ ሀዬ ዬዎ አበቢየ የመስከረሚየ" እያሉ በማዜም የሚገኙበት ሲሆን ወጣት ወንዶችም የሚያጯትን ለመምረጥ ደምቀው የሚወጡበት ባህል መሆኑን አስረድተዋል።

አዳብና በተለያዩ የገበያ ስፍራዎችና ቤተክርስቲያናት ከወጣት ሴቶችና ወንዶች ጭፈራና ሙየቶች ትዕይንት ባሻገር ለየት ባለ አለባበ የተነፋፈቁ የሚገናኙበት፤ ያላገቡ የሚተጫጩበት፤ አዲስ ሙሽሮች አደባባይ የሚወጡበት፤ የፈረስ ጉግስ የሚከናወንበት፣ ወጣት ወንዶች ለአቅመ አዳም መድረሳቸውን በዝላይ በማሳየት እራሳቸውን የሚፈትሹበት እና ሌሎች በርካታ ባህላዊ ሁነቶች የሚከናወኑበት ቱባ ባህል ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ይህ ባህል በጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ማለትም በጠለፋና በአላስፈላጊ ዘመናዊነት ተገትቶ የቆየ ቢሆንም አሁን ላይ በመንግስት እና ማህበረሰቡ የጋራ ርብርብ እያንሰራራ ነው ብለው አዳብና በቱሪዝሙ ዘርፍ እውቅና እንዲሰጠው ይበልጥ በማስተዋወቅ ጠብቆ ሊይዘው እንደሚገባ አሳስበዋል።

ወ/ሪት ጽጌረዳ አሸናፊ፣ አበባ ከበደና ይስሐቅ አዳነ በሰጡት አስተያየት አዳብና ከጥንት ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ የወጣቶች የመተጫጫና መገናኛ የአደባባይ ባህል ነው ብለዋል።

ባህሉ ወጣት ወንዶችና ልጃገረዶች የተለያዩ ባህላዊ አልባሳት በመልበስና ጸጉራቸውን በመሰራት ወደተመረጡ ገበያዎችና ሀይማኖታዊ ቦታዎች በማምራት በጭፈራና በተለያዩ ባህላዊ ትዕይንቶች የሚያከብሩትና አዳዲስ ሙሽሮችም ተውበው የሚወጡበት እንደሆነ ገልፀዋል።

አዳብና ወጣቶች ተጠናንተው የሚተጫጩበት ባህል ብቻ ሳይሆን በየአመቱ በጉጉት የሚጠብቁት የክረምቱ ጭጋግ ተገፎ ወደ ብርኃን መሸጋገራቸውን በደስታ የሚገልጹበትና ማህበራዊ መስተጋብራቸውን የሚያድሱበት ድንቅ ባህል ነው ብለዋል።

ለአዳብና መደብዘዝና መረሳት ዋነኛው ምክንያት ዘመናዊነት በመሆኑ በቀጣይ ወጣቱ በባለቤትነት ባህላዊ ትውፊቱን ሳይለቅ ወደነበረበት ለመመለስ ከሚመለከተው ባለድርሻ አካል በቅንጅት ሊሰራበት እንደሚገባም ተናግረዋል።

አዳብና መክፈቻ በአል አናቲ // ethio gurage caltural music mesekel

Поделиться в:

Доступные форматы для скачивания:

Скачать видео mp4

  • Информация по загрузке:

Скачать аудио mp3

Похожие видео

ጉራግኛ ጭፈራ በሶዶ ክስታኔ ቡኢ ቁ.፪

ጉራግኛ ጭፈራ በሶዶ ክስታኔ ቡኢ ቁ.፪

ውሎ አዳር - የእናት እጆች በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ  መንጠር  ቀበሌ

ውሎ አዳር - የእናት እጆች በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ መንጠር ቀበሌ

የቆነጃጅቱ የጭፈራ ውድድር

የቆነጃጅቱ የጭፈራ ውድድር

//አራዳ ቅዳሜ//

//አራዳ ቅዳሜ// "ሆዴ ከጮኸ ጉዳዩ ትኩረት ያጣል🤣😂 በሳቅ ፍርስ የሚያደርግ ኮሜዲ

January 8, 2025

January 8, 2025

በጉራጌ አለ ቅጥ ጦርነት ያለ ቅጥ ውበት #gurage #ethiopiantour #travel #guragegna_music

በጉራጌ አለ ቅጥ ጦርነት ያለ ቅጥ ውበት #gurage #ethiopiantour #travel #guragegna_music

አዝናኝ የመስቀል ቆይታ በጉራጌ በጠንክር ቶቶት ትውልድ ቤት/እናቱ መረቁን#mese

አዝናኝ የመስቀል ቆይታ በጉራጌ በጠንክር ቶቶት ትውልድ ቤት/እናቱ መረቁን#mese

ባህላዊ የጉራጌ ክትፎ አዲስ አበባ ውስጥ 🇪🇹

ባህላዊ የጉራጌ ክትፎ አዲስ አበባ ውስጥ 🇪🇹

✅ የገጠር እናቶችን ያስደሰትንበት ልዩ የገበያ ውሎ ❤  የደሴ ሰኞ ገበያ ማራኪ ገፅታ ! Dessie monday market. #wollo   #market

✅ የገጠር እናቶችን ያስደሰትንበት ልዩ የገበያ ውሎ ❤ የደሴ ሰኞ ገበያ ማራኪ ገፅታ ! Dessie monday market. #wollo #market

teka asefa#guragegna zefen teyte ተካ ቴየቴ ተካ አሰፋ

teka asefa#guragegna zefen teyte ተካ ቴየቴ ተካ አሰፋ

መስቀል በጉራጌ how mwskel celebrated in gurage Ethiopia . part 1 Girum TV

መስቀል በጉራጌ how mwskel celebrated in gurage Ethiopia . part 1 Girum TV

ታታሪዋ ጋዜጠኛ መቅደስ ጎሳዬ የሀገራችንን ባህል በማስተዋወቅ ላይ የምትገኝ እህታችን ናት እንሾሽላዋ-ዝ- በወኔቦ ባት(ባንድ)

ታታሪዋ ጋዜጠኛ መቅደስ ጎሳዬ የሀገራችንን ባህል በማስተዋወቅ ላይ የምትገኝ እህታችን ናት እንሾሽላዋ-ዝ- በወኔቦ ባት(ባንድ)

ውረድ እስክስታ :- 🥳  አዲስ ምርጥ የገጠር ድራማ (ልዩ ፕሮግረም)  Fikat Entertainment ፍካት ቲቪ

ውረድ እስክስታ :- 🥳 አዲስ ምርጥ የገጠር ድራማ (ልዩ ፕሮግረም) Fikat Entertainment ፍካት ቲቪ

በፍፁም ያልጠበኩት ነገር  በመስቀል ጉራጌ  ገጠመኝ #gurage #habesha #ethiopian #meskel #seyaethiopia

በፍፁም ያልጠበኩት ነገር በመስቀል ጉራጌ ገጠመኝ #gurage #habesha #ethiopian #meskel #seyaethiopia

መስቀልን በጉራጌ ደመራ ሀይሉ ፈረጃ ቤተሰቦች ቤት ከዝነኛ አርቲስቶች ጋር (3) MESKEL IN GURAGE  (3 ) #gurage #guragignaculture

መስቀልን በጉራጌ ደመራ ሀይሉ ፈረጃ ቤተሰቦች ቤት ከዝነኛ አርቲስቶች ጋር (3) MESKEL IN GURAGE (3 ) #gurage #guragignaculture

//የቤተሰብ መገናኘት//

//የቤተሰብ መገናኘት// "የአባቴን መልክ እህቴ ላይ አየሁት" ከአዳማ እስከ አስመራ የዘለቀው ናፍቆት በደስታ ተቋጨ //ቅዳሜን ከሰአት//

ወዳጅነት አደባባይ የመጀመሪያ ህልም

ወዳጅነት አደባባይ የመጀመሪያ ህልም

ማእዛ አብ ሂወታ ዝተፈተነትሉ ጥያቄ😱ዉልድ ካብ ዉልድ አዳልያ😱

ማእዛ አብ ሂወታ ዝተፈተነትሉ ጥያቄ😱ዉልድ ካብ ዉልድ አዳልያ😱

ክትፎ የሚጠጣበት ደንጌሳት በጋራ የሚያከብሩት የመስቀል በአል

ክትፎ የሚጠጣበት ደንጌሳት በጋራ የሚያከብሩት የመስቀል በአል

КАВКАЗ! Редкие кадры из ЖИЗНИ ПАСТУХОВ! Рецепт настоящего БЕШБАРМАКА! Хычины! Жизнь балкарцев

КАВКАЗ! Редкие кадры из ЖИЗНИ ПАСТУХОВ! Рецепт настоящего БЕШБАРМАКА! Хычины! Жизнь балкарцев

© 2025 dtub. Все права защищены.

  • Контакты
  • О нас
  • Политика конфиденциальности

Контакты для правообладателей: [email protected]