አስጊ ሁኔታዎችን በጥበብ ተጋፈጡ! || በዶ/ር ኢዮብ ማሞ || Dr. Eyob Mamo || Risk Management and Risk Taking
Автор: Dr. Eyob Mamo
Загружено: 2024-01-02
Просмотров: 8456
አስጊ ሁኔታዎችን በጥበብ ተጋፈጡ
1. በሕይወትህ “አደጋን” በመፍራት አስፈላጊ የሆኑን ውሳኔዎችን ለመውሰድ ትቸገራለህ ?
2. ማድረግ ስለምትፈልጋቸው ነገሮች ብዙ ስታልም፣ ሆኖም በአንዱም ነገር ላይ እርምጃ ከመውሰድ ስትዘገይ ራስህን ታገኘዋለህ?
3. ለማድረግ የምትፈልጋቸው ብዙ ነገሮች እያሉ ከፍርሃት የተነሳ ወደ ኋላ ትላለህ?
4. ወደ አንድ ግብ ለመገስገስ ስታስብ አእምሮህን የሚሞላው ሊከሰት የሚችለው ክፉ ገጠመኝ ነው?
5. አንተ የፈራሃቸውን ውሳኔዎች ሌሎች ሰዎች እንዲወስኑልህ መልቀቅ ይቀናሃል?
6. ውሳኔዎችህን የሚነዳው ምክንያታዊ ስሌት ሳይሆን ጭፍን ፍርሃት እንደሆነ ታስባለህ?
7. የአንድ ነገር ውጤት የሚወሰነው በእድል ምክንያት ነው የሚል እምነት አለህ?
8. በሰዎች ላይ የደረሱ አስቸጋሪ ገጠመኞች ሰዎቹን ከግባቸው እንዴት እንዳሰናከላቸው ማንበብና መስማት ትኩረትህን ይስበዋል?
9. አንድን እቅድ ስታወጣ ሊደርሱ ለሚችሉ እንቅፋቶች አብረህ የመፍትሄ እቅድ ከማውጣት ይልቅ እንደማይደርሱ ማሰብን ትመርጣለህ?
10. ምንም ነገር ከመጀመርህ በፊት ሊከሰቱ ለሚችሉ እንቅፋቶች በቅድሚያ ሙሉ መልስ ማግኘት እንዳለብህ ታስባለህ?
ከላይ ለተጠየቁት አስር ጥያቄዎች ከግማሽ በላይ ለሆኑት “አዎ” የሚል መልስ ከሰጠህ በዚህ ምእራፍ ለተጠቀሱት ነጥቦች አስፈላጊ ትኩረት በመስጠት ለውጥን ለማስተናገድ ጥረት አድርግ፡፡
1ኛ እውነታ፡- ማደግን እስካላቆምኩ ድረስ ፍርሃት ሊሄድ አይችልም፡፡
2ኛ እውነታ፡- አንድን ነገር የማድረግን ፍርሃት የማስወገጃው ብቸኛ መንገድ ወጥቶ ያንን የምንፈራውን ነገር ማድረግ ነው፡፡
3ኛ እውነታ፡- በራሴ ላይ ባለኝ አመለካከት ጥሩ ስሜት እንዲሰማኝ የማድረጊያው ብቸኛ መንገድ መውጣት … ማድረግ ነው፡፡
4ኛ እውነታ፡- ከዚህ በፊት ወደማላውቀው ክልል ውስጥ ስገባ ፍርሃት የሚሰማኝ እኔ ብቻ አይደለሁም፤ ይህ ሁሉም ሰው የሚጋራው ስሜት ነው፡፡
5ኛ እውነታ፡- ስጋቴን ተጋፍጬ ለመሄድ አቅም እንዳጠረኝና እንዳቃተኝ ሲሰማኝ በዚያ ፍርሃት ውስጥ ከመኖር ይልቅ ስጋቴን ተጋፍጬ በማለፍ የሚመጣው ፍርሃት እጅግ የተሻለና አናሳ ነው::
መንስኤው
ስሜታዊነት ሲልቅ
የብቃት ጉድለት
ቅድመ-ልምምድ
መዘዙ
አለመሻሻል
በሌሎችላይጥገኛመሆን
ኑሮንአለማጣጣም
መፍትሄው
ምክንያታዊነትን ከስሜታዊነት ጋር አመዛዝን
ስጋትን ከስኬት ጋር አመዛዝን
ስሌትን ወደ ተግባር ለውጥ
ራስህን መዝነው
#riskmanagement #risktaking
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: