ዳንኤል: ሉዓላዊ በሆነው በእግዚአብሔር በመታመን መጽናት //እንዳሻው ነጋሽ// Daniel: sovereignty of God, perseverance/ Endashaw
Автор: Endashaw Negash
Загружено: 2020-12-04
Просмотров: 561
የትንቢተ ዳንኤል መጽሐፍ ማእከላዊ ጉዳይ ሉዓላዊ በሆነው በእግዚአብሔር መታመን መጽናት ነው። እግዚአብሔር ታሪክን የሚቆጣጠር እና የሚመራ ሉዓላዊ አምላክ ነው። የዓለም መንግሥታት ሁሉ በእርሱ ቁጥጥር ሥር ናቸው። በጭቆና እና በልዩ ልዩ መከራ ውስጥ የሚያልፉ ሁሉ በእርሱ በመታመን ሊጽኑ እንደሚገባ ይህ መጽሐፍ ያስተምራል። እግዚአብሔር በእርሱ በመታመን የሚጸኑትን የሚያድን፣ የሚታደግ ሃያል አምላክ መሆኑን የዳንኤልና የጓደኞቹ ታሪክ ያሳያል። የመጽሐፉ የመጀመሪያዎቹ 6 ምእራፎች በታሪክ መልክ የቀረቡ ሲሆን ቀሪዎቹ ምእራፎች (7-12) በአቡቀለምሲሳዊ የሥነ ጽሑፍ ቅርጽ የቀረቡ ናቸው። ይህቺን አጭር ቪድዮ በመመልከት የዳንኤልን መጽሐፍ ትኩረት በጥቂቱም ቢሆን መገንዘብ ይቻላል።
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: