የሕያዋን አምላክ
Автор: Abba Dawit Wubishet - አባ ዳዊት ውብሸት
Загружено: 2025-04-27
Просмотров: 237
This song is based on Psalm 119, which is commonly used during a funeral procession in the Ge'ez Liturgical tradition. It can be used during the funeral rite and related occasions.
ይህ መዝሙር በመዝሙር 119 ላይ የተመሰረተ ሲሆን ለቀብር ስርዓት ከሚካተቱት ጸሎቶች መካክል አንዱ ነው። ይህንን መዝሙር ከሃዘን ጋር በተያያዙ ጊዜያቶች መጠቀም ይቻላል።
የሕያዋን አምላክ
እግዚአብሔር የሙታን አምላክ አይደለም
የሕያዋን እንጂ የዘለዓለም (ማር 12፡27)
(መዝ. 119፡ 1፣ 17፣ 49፣73፣ 113፣ 161)
አሌፍ በአካሄዳቸው ቅኑዎች የሆኑ
በሕጉ መሰረት የሚመሩ ብፁዓን ይባሉ፡፡
ጋሜል በሕይወት እንድኖር ቃልህን እንድንጠብቅ
ለእኔ ለአገልጋይህ አዛኝ ሁን አታርቅ ፊትህን
ዛይ የተስፋ ቃልህን ለእኔ እንደሰጠህ
በእርሱ እመካለሁ በአዳኝነትህ በቸርነትህ
ዮድ አንተ የፈጠርከን ሕያው ያደረከን
መከተል እንድንወድ ሕግህን ከቶ እንዳንርቅህ፡፡
ሳምኬት የማይታመኑትን ሁሉ እተዋለሁ
ሕግህን የሚወዱ እቀርባለሁ ወዳጅ እሆናለሁ፡፡
ሳን ብርቱዎች ከፉብኝ በእኔም ተነሱብኝ
ቃልህን እንዳከብር ብርታት ሁነኝ በተስፋ አግዘኝ
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: