በኤሊያስ መልካ የተቀናበሩ የተመረጡ ሙዚቃዎች||Elias Melka Produced Music Mix
Автор: Muler Tube
Загружено: 30 сент. 2024 г.
Просмотров: 460 просмотров
ኤልያስ መልካ
መስከረም 24/2012.. ታዋቂው የሙዚቃ አቀናባሪ ኤሊያስ መልካ ባደረበት ህመም ትናንት ሌለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። ከሙዚቃ አቀናባሪነቱ ሻገር ጊታሪስት፣ ገጣሚና የዜማ ደራሲው ኤሊያስ መልካ ትናንት ሌሊት ህይወቱ ማለፉን የሰሙ ጥልቅ ሀዘናቸውን በተለያዩ መንገዶች እየገለጹ ነው። ኤሊያስ በስኳር ህመም ሲሰቃይ መቆየቱ ይነገራል። ከዚህ ጋር በተያያዘም ኩላሊቱ መስራት አቁሞ እንደነበር የቅርብ ወዳጆቹ ይገልጻሉ። እድሜው በ40ዎቹ መጀመሪያ ላይ የሆነው የሙዚቃ አቀናባሪ ኤሊያስ መልካ የተወለደው አብነት አዲስ ከተማ አካባቢ ነው። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በሃይሉ ተስፋዬ ትምህርት ቤት፤ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በከፍተኛ ሰባት ትምህርት ቤት ተከታትሏል። በየካቲት 2011 ዓ.ም በፋና ቴሌቪዥን ፋና ቀለማት ፕሮግራም "ሙዚቃን የኖረው የሙዚቃ አቀናባሪ ኤሊያስ መልካ" በሚል የቀረበው ዶክመንተሪ ኤሊያስ በትምህርቱ በጣም ጎበዝና ታታሪ እንደነበር የቅርብ ወዳጆቹ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። ኤሊያስ መልካ ወደ ሙዚቃ ህይወት ከመግባቱ በፊት በጣም ጎበዝ ኳስ ተጫዋች እንደነበረም ወዳጆቹ እማኝነታቸውን ይሰጣሉ። ቁመቱ አጭር በመሆኑ ጓደኞቹ "ትንሹ ማራዶና" በሚል ቅጽል ስም እንደሚጠሩትም ይነገራል። ባለው የኳስ ጨዋታ ክህሎትም ኤሊያስ ወደ ፊት ጥሩ ኳስ ተጫዋች እንጂ ሙዚቀኛ ይሆናል ብሎ የጠበቀ እንዳልነበር ጓደኞቹ ይገልጻሉ። ኤሊያስ መልካ በልጅነቱ የቀለም ቆሮቆሮዎችን ሰብስቦ በእንጨት በመምታት የሚያወጣቸው ድምጾች በጣም ያስገርማቸው እንደነበርም ነው ጓደኞቹ የሚናገሩት። ኤሊያስ መልካ በ1987 ዓ.ም ወደ ያሬድ ሙዚቃ ቤት በመግባት ተምሮ ቼሎና ሊድ ጊታር ይጫወት ነበር። ከሙዚቃ መምህራኑ እዝራ አባተ፣ አክሊሉ ዘውዴ እና ሌሎች ባለሙያዎች ጋር በመዲና ባንድ ውስጥ ሰርቷል። ከመዲና ባንድ በተጨማሪ ኤሊያስ በዜማ ላስታስና አፍሮ ሳውንድ ባንዶች የተጫወተ ሲሆን፤ ከ30 በላይ ሙሉ አልበሞችን አቀናብሯል። ኤሊያስ መልካ ከአለማየሁ እሸቴ፣ ፍቅር አዲስ ነቅዓጥበብ፣ ከአረጋኸኝ ወራሽ፣ ከመሐሙድ አህመድ፣ ከዘሪቱ ከበደ፣ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)፣ ሚካኤል በላይነህ፣ ኃይሌ ሩትስና ከሌሎች ድምጻዊያንም ጋር ሰርቷል። ከአልበሞች በተጨማሪ በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ሕብረ ዝማሬዎችን ማቀናበሩ ይታወቃል። ከእነዚህም መካከል መላ መላ፣ ማለባበስ ይቅር፣ ለአፍሪካ ሕብረት፣ በትራፊክ አደጋ መከላከል ላይ ያተኮሩት ይጠቀሳሉ። ከሙዚቃ ማቀናበር ስራው በተጨማሪ በተወሰኑ ኮንሰርቶች ላይ ከባንዶቹ ጋር በመሆን ከታዋቂ ድምጻዊያን ጋር የሰራ ሲሆን፤ በሚሊኒየም አዳራሽ ከዘሪቱ ከበደ ጋር የሰራው ኮንሰርት በዋንኛነት ይጠቀሳል። በገና ስቱዲዩን በማቋቋም የሙዚቃ ማቀናበር ስራውን የጀመረው ኤሊያስ፤ የሚሰራቸው ስራዎች በጣም ታታሪ ጎበዝ ለሙዚቃ የተሰጠ መሆኑን የሚያሳይ እንደሆነ ድምጻዊያንና የሙዚቃ አስተማሪዎቹ ይመሰክራሉ። ድምጻዊያን ኤሊያስ የሚሰራቸው የሙዚቃ ስራዎች ማንነቱን ስብዕናውን በጣም እንደሚገልጹና በየጊዜው በዓለም ላይ ካለው የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ለውጦች ጋር ራሱን በማማሻልና በማብቃት ሁሌም ሙዚቃ የሚፈልገው ደረጃ ላይ የሚገኝ ከያኒ እንደበርም ከእርሱ ጋር የሰሩ ድምጻዊያን ይገልጻሉ። ኤልያስ በዘመናዊው የኢትዮጵያ ሙዚቃ አሻራቸውን ካሳረፉ ወጣት ባለሙያዎች መካከል አንዱ እንደሆነ የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ።ሙዚቃ አቀናባሪ ኤሊያስ ሰውን መርዳት የሚወድ፣ ጨዋ፣ ተጫዋችና ተግባቢ፣ ደግና ከራሱ ይልቅ ሌሎችን የሚያስቀድም ጥሩ ስብዕና ያለው እንደሆነም የቅርብ ወዳጆቹ ይናገራሉ። ታዋቂው የሙዚቃ አቀናባሪ ኤሊያስ መልካ በተለያዩ ሥራዎቹ የተለያዩ ሽልማቶችንና እውቅናን አግኝቷል። ኤልያስ መልካ መስከረም 24 ቀን 2012 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
Elias Melka
Elias Melka Geresu (December 10,1977 – October 4,2019) was a prominent Ethiopian record producer and songwriter, celebrated for his pivotal role in modern Ethiopian music. He produced over 40 albums, including Teddy Afro's debut "Abugida" in 2001. Elias Melka was instrumental in shaping the careers of many artists, such as Zeritu Kebede and Gossaye Tesfaye. Beyond music, Elias Melka advocated social responsibility through songs addressing HIV/AIDS and traffic safety. Elias Melka also founded the Awtar music app to support fair compensation for musicians. Melka passed away at 42 due to complications from diabetes and kidney failure.
#ሙዚቃ
#ኤሊያስመልካ
#elias
#elíasmedina
#አቀናባሪ
#ephremtamiru
#music
#DonkeyTube
#EBS
#ethiopian
#etv
#ethiopianmusic
#ሊድጊታር

Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: