ኢትዮጵያን አስብልን | Aster Abebe | Yosef Kassa | EECB Worship Teams | New Ethiopian Gospel Song 2025
Автор: Ethiopian Evangelical Church In Boston
Загружено: 2025-04-18
Просмотров: 80549
ኢትዮጵያን አስብልን | የፀሎት መዝሙር ለኢትዮዺያ
የእግዚአብሔር ክንድ ሆይ፥ ተነሥ፥ ተነሥ፥ ኃይልንም ልበስ፤ በቀድሞው ወራትና በጥንቱ ዘመን በነበረው ትውልድ እንደ ሆነው ተነሥ። ረዓብን የቈራረጥህ ዘንዶውንም የወጋህ አንተ አይደለህምን?
ኢሳይያስ 51:9
Awake, awake, arm of the Lord, clothe yourself with strength! Awake, as in days gone by, as in generations of old. Was it not you who cut Rahab to pieces, who pierced that monster through?
Isaiah 51:9 NIV
Redemption pictures presents
Music arrangement and mixing: Dr. Bereket Alemayehu, Zoe Studio Hawassa
Vocals: Gospel singer Aster Abebe, Tsega Alemayehu,
Aleta Wondo Full Gospel Church Zema Choir
Song lyrics
ኢትዮጵያን አስብልን
አቤቱ ፀሎታቸን መልስልን
ኢትዮጵያን አስብልን
ጌታ ሆይ እንባችንን አብስልን
ምድራችንን ጎብኝልን
ምህረትህ ይብዛ ማረን እንላለን
እጆቻችንን ወዳንተ ዘርግተን
ከክፉ መንገድ እንመለሳለን
ከእግርህ ስር ወድቀን እንጮሀለን
በእውነት ፊትህን ፈልገን
መጥተናል ይቅር በለን
የእግዚአብሔር ክንድ ሆይ ተነስ
ተነስ ተነስ
ዘንዶውን የወጋህ አንተ አይደለህ
ረአብን የቆራረጥክ
አንተ አይደለህም ወይ (4X)
ተነስ ተነስ
እጅህም ይዘርጋ ፊትህን መልስ
እንደቀድሞው ሀይልን ልበስ
ተነስ ተነስ
እጅህም ይዘርጋ ፊትህን መልስ
ዛሬም ና ተንቀሳቀስ
አቤቱ ፀሎታችን መልስልን
ኢትዮጵያን አስብልን
ጌታ ሆእ እንባችንን አብስልን
ምድራችንን ጎብኝልን
ጨለማው አልቆ ለቆ ሁሉን ስፍራ
የወንጌል ብርሀን በምድሪቱ ይብራ
ጉስቁልናችን ቀርቶልን አበሳ ሰላምና ፈውስ እረፍት ይሁን ይብዛ
በረከትንም አፍስሰህ አሳየን አትረፍርፈህ
የእግዚአብሔር ክንድ ሆይ ተነስ
ተነስ ተነስ
ዘንዶውን የወጋህ አንተ አይደለህ
ረአብን የቆራረጥክ
አንተ አይደለህም ወይ (4X)
ተነስ ተነስ
እጅህም ይዘርጋ ፊትህን መልስ
እንደቀድሞው ሀይልን ልበስ
ተነስ ተነስ
እጅህም ይዘርጋ ፊትህን መልስ
ዛሬም ና ተንቀሳቀስ
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: