Sandwich Bread የሳንዱች ዳቦ
Автор: Melegna | መለኛ
Загружено: 2025-10-21
Просмотров: 3325
ዳቦ በቅርቡ አንድ ትልቅ ሱፐር ማርኬት ከምለው ከገዛሁት በኃላ በውስጡ በጣም ስል የሆነ የብረት ስባሪ አጊኝቼ ነበር ፤ ያገኘሁትም ዳቦውን አፌ ውስጥ በማላምጥበት ጊዜ ነው ፡፡ በዛው ሰዓት የወሰንኩት ነገር ቢኖር ዳቦ ፈፅሞ ከዛ ሱፐርማኬት ላለመግዛት እና ዳቦን ውጪ ላይ መግዛት ለመቀነስ ነው ፡፡
ከዚህ በፊት ያጋጠመኝ የሻገተ ዳቦ እና የደረቀ ዳቦ ነው ፡፡ እናንተም በቤት ውስጥ ዳቦ መጋገር ከፈለጋችሁ ከባድ እንዳይመስላችሁ ፡፡
የግብዓት አይነት እና መጠን
300 ግራም ፉርኖ ዱቄት
ቆንጆ ዳቦ እንድታገኙ የምትጠቀሙት የዱቄት አይነት አንደኛ ደረጃ የሚባለው ቢሆን ይመረጣል
1 የሾርባ ማንኪያ እርሾ
በቤት ውስጥ ለእንጀራ ያዘጋጃችሁት የሀበሻ እርሾ ካለ እሱን መጠቀም ትችላላችሁ
እርሾው ቶሎ ኩፍ እንዲልላችሁ እና ትንሽ ቁምጣጤውን ለማስተካከል አንድ ቁንጥር ስኳር መጨመር ትችላላችሁ
ግማሽ የሾርባ ማንኪያ ቤኪንግ ፓውደር
ግማሽ የሾርባ ማንኪያ ጨው
2 የሾርባ ማንኪያ የምግብ ዘይት
3 ኩባያ ውሃ
አቦካክ እና ኩፍታ
የመጀመሪያውን ዙር ካቦካችሁ በኃላ ለ45 ደቂቃ በደንብ ሸፍኖ ደረቅ እና እርጥበት የማያገኘው ቦታ ማቆየት
ሁለተኛውን ዙር ሊጡን እጃችሁን ውሃ ውስጥ እየነከራችሁ ከለጠጣችሁት በኃላ ሸፍኖ ለ30 ደቂቃ ኩፍ ማድረግ
ጠረጴዛ ላይ ዱቄት በትንሹ ነስንሳችሁ የሳንዱች ዳቦ ቅርፅ ማስያዝ
ቅርፁን ካስያዛችሁ በኃላ ሸፍናችሁ ለ10 ደቂቃ የመጋገሪያ ትሪው ላይ ማሰረፍ
አበሳሰል
የመጋገሪያ ምድጃችሁን ለ5 ደቂቃ በ200ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ማጋል
ሊጡን አስገብቶ ለ20 ደቂቃ የላይኛውም የታችኛውም እንደበራ ማብሰል
አቀማመጥ
ዳቦው ለቀናት ቆንጆ ሆኖ እንዲቆይ በንፁህ እና ደረቅ በሆነ ላስቲክ ሸፍኖ ማስቀመጥ
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: