🔴አዲስ ዝማሬ ጾም ትፌውስ ዲያቆን ዘማሪ እንዳለ ደረጄ deacon zemari endale dereje
Автор: Deacon Endale Dereje
Загружено: 2025-03-04
Просмотров: 10963
#ethiopia ##religion #subscribe #duet #mezmur #orthodox #
❤ #ጾም_ትፌውስ
🔴🔴
💙
🔷🔴🔷🔴🔷
ጾም የነፍስን ቁስል - ትፈውሳለች
የሥጋንም ምኞት - ሁሉ ትገታለች
ሊቁ እንዳስተማረን - በድጓ በቃሉ
ጎበዞች በእርሷ - አርምሞን ያውቃሉ(፪)
🔷🔴🔷
ዓይን መጥፎ ከማየት - ይጹም ካ'ጉል ነገር
አንደበት ይከልከል - ክፉ ከመናገር
ለጌታ ይገዛ -መላ ሁለንተና
እንዲመጣ ምሕረት - እንዲርቅ ፈተና
🔷🔴🔷
በጾም ወደ መቅደስ - ወደ አምላክ መገሥገሥ
ልክ እንደ ዳንኤል - ያቀዳጃል ሞገስ
በልዑላኑ ዘንድ - የምታሰጥ ግርማን
ጾም ናት መከበሪያ - 'ምታሠምር ዓላማን
🔷🔴🔷
ልባችን ይንበርከክ - ለቃሉ ይገዛ
ፍቅራች እንዲጸና - ሰላሙም እንዲበዛ
በጾምና ጸሎት - ትድናለች ሀገር
ነነዌን ዐይተናል -መዓት ስትሻገር
🔷🔴🔷
እንደ ሐዋርያቱ - እንደ ጻድቃን አበው
በጾም እና ሱባዔ - ነው ሕይወት 'ሚዋበው
የአርምሞ እኅት - የጸሎት እናት
የነፍሳችን ፈዋሽ - መድኃኒት ጾም ናት።
🔷🔴🔷
✍©ግጥም ቸርነት አንቄ (የጽዮን ሎሌ)
ዜማ ዲያቆን እንዳለ ደረጄ
🔴
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: