🌼 ተለቀቀ 🌻 ሆ ብለን መጣን 🌼 የአዲስ ዐመት ዝማሬ 🌼 New Addis Amet Mezmur 2024
Автор: አርያም ሚዲያ - Aryam Media
Загружено: 2024-09-07
Просмотров: 466636
#የመዝሙሩ_ግጥም
የመዝሙሩ ግጥም
ሆ ብለን መጣን
እሰይ ደስ ደስ ይበለን ደስ ደስ ይበለን
ዐዲሱ ዐመት መጣልን ደስ ደስ ይበለን(2)
እሰይ ደስ ደስ ይበላችሁ ደስ ደስ ይበላችሁ
ቅዱስ ዮሐንስ ትመጣላችሁ ደስ ደስ ይበላችሁ(2)
ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(፪)
ጌቶች አሉ ብለን
ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(፪)
እሜቴ አሉ ብለን
ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(፪)
ዘመን መጣ
የደፈረሰ ሃሌ ሉያ ወንዝ ሲጠራ ሃሌ ሉያ
በመስከረም ወር ሃሌ ሉያ ሲያብብ አዝመራ ሃሌ ሉያ
የረከሠ ልብ ሃሌ ሉያ ያደፈ ልብስ
ጥዬ መጣሁኝ ሃሌ ሉያ እንድታደስ
መድኃኔዓለም ኧኸ
ቸር መሃሪ ነህ ሚመስልህ የለም
ድንግል ሆይ ኧኸ
መርከባችን ነሽ ታሻግሪናለሽ
ልጫማ ቃሉን ሃሌ ሉያ ለብሼ ወንጌል ሃሌ ሉያ
ባሪያ ልሁንህ ሃሌ ሉያ ልጅህ ባልባል ሃሌ ሉያ
ማቄን ቀድጄ ሃሌ ሉያ ካባ ልደርብ ሃሌ ሉያ
ለኔስ ይሻላል ሃሌ ሉያ ወደአንተ መቅረብ ሃሌ ሉያ
አዶናይ በረከትህን ላክ ከሠማይ (2)
እንቁጣጣሽ አሁንም ደግሞ ደግሞ ያምጣሽ (2)
ትናንትን አለፍኩ ሆነህ ጋሻዬ
ነገዬን ስራው ቸር እረኛዬ
ንስሃ ሆኖኝ ገፀ በረከት
ዘመኔ ይመር ላሸብርቅበት
መድኃኔዓለም
ቸር መሃሪ ነህ ሚመስልህ የለም
ድንግል ሆይ
መርከባችን ነሽ ታሻግሪያለሽ
አደይ የብር ሙዳይ ኮለል በይ
ኧኸ ዐደይ የአምላክ እናት ድንግል ነይ
ማረኝ ኧኸ
ወደ መቅደስህ
ጠርተ'ህ አስገባኝ
የልጅነት ኧኸ
መተላለፌን አታስብብኝ
ቢሉኝም ኧኸ
አምሽቶ መጣ
ከቤትህ አልውጣ
ክፈለኝ ኧኸ
ደጉ ጌታዬ
አይነስ ዋጋዬ
ይቺን አመት ኧኸ
አንተው ተወኝ
ልብህ ይዘንልኝ
(እቴ አበባሽ እቴ አበባዬ አዬ እቴ አበባዬ...)
ለብቻ
ይቺን አመት ተወኝ ጌታዬ - ተወኝ ይቺን ዓመት
ፍሬን አፍርቼ እንዳብብበት
ተወኝ ይቺን አመት
ተወኝ ይቺን አመት (2*)
ወጥቼ አልቅር
ቤትህ መልሰኝ
ተወኝ ይቺን ዓመት
ለንስሃ ዕድሜን ለግሠኝ
ተወኝ ይችን ዓመት
ቤት ጓዳዬንም ላስተካክለው
ተወኝ ይችን ዓመት
ህዝቅያስንም እንድመስለው
ተወኝ ይችን ዓመት(2)
በንጉስ ቀኝ የምትቆሚ
ማርያም የኔ እመቤት
ስለፅድቄ ሁሌ ቅደሚ
ማርያም የኔ እመቤቴ
ማራት ብለሽ አስምሪኝና
ልቀኝልሽ በአዲስ ምስጋና
ማርያም የኔ እመቤት(2)
---------------------------------------------
ድንግል ማርያም ኧኸ
የምህረት- ዝናብ
መንፈሣዊት- መርከብ
የብርሃን - ድንኳን
ተስፋ ነሽ - ለሃጥዓን(2*)
ለመስቀል ለታ ለደመራው
በአዲሱ ዓመት በል ማረኝ ብዬ
ልቆጠር መጣሁኝ ልጅህ ተብዬ
በአለም መኖር አልጠቀመኝም
ከፀፀት በቀር አልተረፈኝም
የሠጠኸኝን ሙሽርነት ልብስ
አሣድፌያለሁ በኃጢዓት መርከስ
የጥምቀት ድርብ በፍታዬ የለም
መብራት ዘይቴ አልተዘጋጀም
የተካፈልኩት አልቋል በመርገም
አብሮኝ ያጠፋው ወዳጄም የለም
አንተ ግን አለህ ለዘለዓለም (2*)
ከብረው ይቆዮን ከብረው
የአለምን ሃጥያት ንቀው
ሆናችሁ ልባም ሙሽራ
ብርሃናችሁ እንዲያበራ
ወደ ቤቱ ገስግሣችሁ
ዘይት መብራቱን ይዛችሁ
ከብረው ይቆዮን ከብረው
ከብረን እንቆይ ከብረን
በፆም በፀሎት ፀንተን
አስራቱን ለእርሱ አውጥተን
ዝክር ምስክር ነውና
ከብረን እንቆይ በጤና
ግጥም ፡ ወ/ሮ ሰሎሜ ተክለ ያሬድ
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: