የአረፍተ ነገር አይነቶች - ነጠላ ዐ.ነገር እና ውስብስብ አ/ነገር Grade 6 Amharic
Автор: Educational Media ET
Загружено: 2025-04-03
Просмотров: 4815
የአረፍተ ነገር አይነቶች - ነጠላ እና ውስብስብ ዐ.ነገር | Grade 6 Amharic
በዚህ ቪዲዮ ውስጥ የአረፍተ ነገር አይነቶችን እና ልዩ አይነታቸውን እንመረምራለን። ነጠላ እና ውስብስብ የአረፍተ ነገር ልዩነቶች ምንድን ናቸው? ለአስተማማኝ እና ቀላል ማረዳዳት ይህን ቪዲዮ እስከ መጨረሻው ይመልከቱ።
አረፍተ ነገር ማለት:- በስርአት የተደራጀ
የቃላት ስብስብ ሆኖ ሙሉ ትርጉም እና
ስሜት የሚሰጥ ነው።
በአንድ ዐ.ነገር ውስጥ የዐ.ነገሩ ባለቤት
እና ማሰሪያ አንቀፅ ሊኖር ይገባል።
ማሰሪያ አንቀፅ ማለት ድርጊቱን የሚያመለክት
ወይም የአረፍተ ነገሩ መቋጫ ነው።
ለምሳሌ:-
1) ልጁ ኳስ ይጫወታል።
ባለቤቱ "ልጁ" የሚለው ሲሆን፤
ማሰሪያ አንቀፁ ደግሞ "ይጫወታል"
የሚለው ነው።
በ1 ዐነገር ውስጥ ያለው ግስ አንድ ብቻ ከሆነ፤ የሚያስተላልፈውም ሃሳብ 1 ብቻ ነው።
ዐነገሮች በፅሁፋችን ውስጥ ስንጠቀም ልከኛ
መሆን አለባቸው።
በጣም ከረዘሙ ሃሳብን በቀላሉ ለመረዳት
ያስቸግራሉ።
ዐነገር በ2 ይከፈላል።
1ኛ ነጠላ ዐነገር እና
2ኛ ውስብስብ ዐነገር ናቸው።
ነጠላ ዐነገር የሚባለው በዐነገሩ ውስጥ ያለው
ግስ 1 ብቻ ሲሆን ነው።
ውስብስብ ዐነገር የሚባለው በዐነገሩ ውስጥ
የሚኖረው ግስ 2 እና ከዚያ በላይ ሲሆን ነው።
ምሳሌ:-
1. የክፍላችን ተማሪ ተሸለመ።
(ግሱ "ተሸለመ" የሚለው ብቻ ነው)
ስለዚህ ዐነገሩ "ነጠላ ዐነገር ነው"
2. በትምህርት ውድድር አንደኛ የወጣው
ተማሪ ተሸለመ።
(ግሱ 2 ነው"የወጣው እና ተሸለመ" )
ስለዚህ ዐነገሩ "ውስብስብ ዐነገር ነው"
3. በሀይሉ እንደመጣ ገላውን ታጠበ።
(ባለ 2 ግስ ነው "እንደመጣ እና ታጠበ")
ዐነገሩ ውስብስብ ነው።
4. ልጁ ኳስ ተጫወተ።
(ግሱ "ተጫወተ" የሚለው ብቻ ነው)
ስለዚህ ዐነገሩ ነጠላ ዐነገር ነው።
የተማሪዎች ጭውውት....
የትምህርቱ ዋና ዋና ሃሳቦች
• አረፍተ ነገር ማለት:- በስርአት የተደራጀ
የቃላት ስብስብ ሆኖ ሙሉ ትርጉም እና
ስሜት የሚሰጥ ነው።
• 2 አይነት ዐነገሮች መኖራቸውን።
• ነጠላ እና ውስብስብ ዐነገሮች ተብለው
እንደሚጠሩ።
• ነጠላ ዐነገር በውስጡ 1 ግስ የሚይዝ መሆኑን።
• ውስብስብ ዐነገር 2ና ከዚያ በላይ ግስ የሚይዝመሆኑን ተምረናል።
የማጠቃለያ ጥያቄዎች
1. በውስጡ 1 ግስ ብቻ ያለው ዐነገር ነጠላ ዐነገር ይባላል። ሀ) እውነት ለ) ሀሰት
2. በውስጡ 2 እና ከዚያ በላይ ግስ የያዘ ዐነገር ምን
ይባላል? ሀ) ውስብስብ ዐነገር ለ) ነጠላ ዐነገር
3. ኢትዮጵያዊው አትሌት 1ኛ ወቶ ተሸለመ። ይህ ዐነገር ምን አይነት ዐነገር ነው?
ሀ) ነጠላ ለ) ውስብስብ
4. ተፈሪ እየሮጠ ተመልሶ ሄደ። የዐነገሩ አይነት ምን
ይባላል?
5. እንግዶቹ ተመለሱ። በዚህ ዐነገር ውስጥ ስንት
ግስ አለ?
📌 ተዋዋል ቀልል ለመስማማት ዝርዝሮች:
⏱ Time Stamps:
00:00 - ማስታወሻ
01:20 - አረፍተ ነገር ምንድነው?
03:45 - የአረፍተ ነገር ዓይነቶች
06:30 - ነጠላ እና ውስብስብ ዐ.ነገር ልዩነት
10:15 - ምሳሌዎች
12:30 - መደምደሚያ
✅ ይሰብሱን ለተጨማሪ ቪዲዮዎች 👉 [ / @addisababa_edu_media
👍 እባኮትን ቪዲዮውን ከወደዱት (Like) እና ያጋሩ (Share)!
📢 አስተያየት አልዎት? እባኮትን አስተያየት ይስጡ።
https://t.me/Booksandtextbooks
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: