06 Hamlet Beljun | FITH | ፊትህ
Автор: Hamlet Beljun
Загружено: 2025-09-11
Просмотров: 33986
Click This Link 👉 / @hamletbeljun #SUBSCRIBE
TO OUR YOU TUBE CHANNEL TO GET NOTIFICATIIONS OF NEW POSTS
ፊትህ 6
ፊት 'ማይነሳኝ ፊትህ የሚቀበለኝ
እንደ ጠዋት ፀሀይ ዘውትር ሚያሞቀኝ
ምቾቴ ነው ፊትህ ወዳንተ እሮጣለሁ
'ምትወደኝ ጌታ ፊት ነፍሴን አፈሳለሁ
ካንተ ላትለያይ ተገምዳ ህይወቴ
በምትገኝበት መኖር ነው ምቾቴ
እጅህን እይዛለሁ ላይለቅ የያዘኝን
የትም ብትሰደኝ ከኔ ጋር እስካለህ አይገደኝ
ደጃፌን ስዘጋው በመንፈስህ ልሰወር
ለካ ከዚህ ዓለም ሀሳብ እየራቅኩኝ ነበር
ቀድሞ የሚያባብለኝ የሚያስጎመጀኝ
ተራ ሆኖ አየሁት መልክህ ሲሳልብኝ
ስፈልገው ያንተን ፊት ተራመድኩኝ በጽናት
ስፈልግህ በመልካም ቀኔ አልፎኝ ሄደ ጥፋት ከኔ
ስፈልግህ ቀርበህ ሳለህ ገኖልኛል ምህረትህ
የፈለኩህ በጉብዝናዬ ዋስትናዬ ነህ ለማምሻዬ
ያንተ ፊት የኔ ምቾት
መገኘትህ ለኔ ስኬት
ፊት 'ማይነሳኝ ፊትህ የሚቀበለኝ
እንደ ጠዋት ፀሀይ ዘውትር ሚያሞቀኝ
ምቾቴ ነው ፊትህ ወዳንተ እሮጣለሁ
'ምትወደኝ ጌታ ፊት ነፍሴን አፈሳለሁ
ካንተ ላትለያይ ተገምዳ ህይወቴ
በምትገኝበት መኖር ነው ምቾቴ
እጅህን እይዛለሁ ላይለቅ የያዘኝን
የትም ብትሰደኝ ከኔ ጋር እስካለህ አይገደኝ
አሃ! የምታስብለኝ በየማለዳው
ያልደረስኩበትን እየገለጥከው
ስንቱን ለቅቄ ጣልኩኝ ወዳንተ ስል ጠጋ
ከህይወት ሚያጎድለኝን ረብ የሌለውን ዋጋ
ስፈልገው ያንተን ፊት ተራመድኩኝ በጽናት
ስፈልግህ በመልካም ቀኔ አልፎኝ ሄደ ጥፋት ከኔ
ስፈልግህ ቀርበህ ሳለህ ገኖልኛል ምህረትህ
የፈለኩህ በጉብዝናዬ ዋስትናዬ ነህ ለማምሻዬ
ያንተ ፊት የኔ ምቾት
መገኘትህ ለኔ ስኬት
©Hamlet Beljun Copyright
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: