Ethiopia:ተፈፀመ
Автор: 7 Tv
Загружено: 2025-04-02
Просмотров: 499
#Ethiopia #7Tube የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት “እንበለ መከራ ኢይትረከብ ጸጋ እግዚአብሔር፤ ያለ መከራ የእግዚአብሔር ጸጋ አይገኝም” በማለት ያስረዳሉ። የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ራሷና ሙሽራዋ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ራሱ ታሞ ጤነኛ የሚሆን አካልና ሙሽራዋ መከራ ሲቀበል ያለ መከራ የምትቀመጥ ሙሽሪት አይኖሩም፡፡ ራሷ፥ ጉልላቷ መስቀል ተሸክሞ አካሉም እንደሱ መስቀል ተሸክማ እንድትከተለው አዟታል፡፡ ሙሽሪትን በሞቱ እንድትመስለውና የትንሣኤው ተካፋይ እንድትሆን ጠርቷታል፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ የተባረከ የመስቀል ጉዞ፣ የተቀደሰው ይህ ጥሪና በዚህ ጥሪ መሠረት የመስቀል ጉዞውን የመሳተፍ ጸጋም በአላዋቂዎች ዘንድ ሞኝነት በአፅራረ ቤተ ክርስቲያን ዘንድ ደግሞ መሸነፍ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ ለእኛ ለምናምነው ግን የክርስቶስ የመስቀሉ ጉዞ ሞኝነትም መሸነፍም ሳይሆን የድል አድራጊነትን ምሥጢር የማዳኑን ኃይል ሰውን ከፈጠረበት ይልቅ ያዳነበትን ረቂቅ ጥበብ የምንረዳበት ነው፡፡ ነገረ መስቀሉን እያሰቡ በመከራውና በሞቱ ክርስቶስን የመሰሉት ሁሉ የሚዋጋቸውን ጠላት ድል እንዳደረጉበት ቅዱሳት መጻሕፍት አብነቶቻችን ናቸው፡፡
እንግድህ ወደተነሣንበት ርእሳችን ስንመጣ ቅዱሳን ሐዋርያቱ በክርስቶስ ስም ከሚደርስባቸው መከራ ይልቅ ስለ ስሙ በሚቀበሉት መከራ የሚያገኙት ጸጋ እጅግ የሚበዛ መሆኑን በመረዳ ነውና ሁልጊዜም ከከሳሾቻቸው ፊት ደስ እያላቸው ይወጡ ነበር፡፡ በዚህ መከራቸውም በሞቱ መስለውታል የትንሣኤውም ተካፋዮች ሆነዋል፡፡
እኛስ በሕይወት ዘመናችን በምናደርገው ክርስቲያናዊ ጉዞ ሁሉ ክርስቶስን በሞቱ መስለነው የትንሣኤው ተካፋዮች እንሆን ዘንድ ይፍቀድልን
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: