Популярное

Музыка Кино и Анимация Автомобили Животные Спорт Путешествия Игры Юмор

Интересные видео

2025 Сериалы Трейлеры Новости Как сделать Видеоуроки Diy своими руками

Топ запросов

смотреть а4 schoolboy runaway турецкий сериал смотреть мультфильмы эдисон
dTub
Скачать

ቅዱስ ስምኦን (ጫማ ሰፊው) - ክፍል 1 / Saint Simon - Part 1

Автор: የቅዱሳን ታሪክ / Yekidusan Tarik

Загружено: 2018-11-14

Просмотров: 243476

Описание:

ቅዱስ ስምኦን (ጫማ ሰፊው
ተአምረ ማርያም ላይ ከተጻፉት እና በትርጓሜ ወንጌልም ላይ በማቴ5÷29 ለሚገኘው ቃል እንደ ታሪካዊ ማስረጃ ከሚቀርቡት ታሪኮች አንዱ የስምዖን ጫማ ሰፊው ታሪክ ነው፡፡
በ979 ዓም የፋጢማይድ ሥርወ መንግሥት ግብጽን በሚያስተዳድርበት ወቅት በከሊፋ አል ሙኢዝ ሊ ዲን ኢላህ አል ፋጢሚ ዘመን እንዲህ ሆነ፡፡

ለሥልጣን ሲል ወደ እስልምና የተቀየረ ያዕቆብ ኢቢን ቂሊስ የሚባል አንድ አይሁዳዊ ነበር፡፡ ይህ አይሁዳዊ ምንም እንኳን ለሥልጣን ሲል እስልምናን ቢቀበልም ልቡ ግን ከአይሁድ ጋር ነበር፡፡ ክርስቲያኖችንም በጣም ይጠላ ነበር፡፡ ይህ ጥላቻው የመጣው በከሊፋው ዘንድ በሚወደድ እና እርሱ ይቀናቀነኛል ብሎ በሚያስበው በአንድ ክርስቲያን ምክንያት ነበር፡፡ ይህ ክርስቲያን ቁዝማን ኢቢን ሚና ይባል ነበር፡፡
ከሊፋ አል ሙኢዝ ደግ፣ ምክንያታዊ እና በሰዎች ነጻነት የሚያምን ዕውቀትንም የሚወድድ መሪ ነበር ይባላል፡፡ ምሁራን ሲከራከሩ መስማት የሚወድድ ሌላው ቀርቶ የእስልምና ምሁራን እስልምናን ከሚቃወሙ ሰዎች ጋር በነጻነት እንዲከራከሩ የሚፈቅድ ሰው ነበረ፡፡

ይህንን ጠባዩን የሚያውቀው ያዕቆብ ሙሴ የተባለውን የአይሁድ ረቢ ጠርቶ ከፓትርያርኩ ጋር እንዲከራከር እና ፓትርያርኩን እንዲያሳፍረው መከረው፡፡ ሙሴም ጥያቄውን ለከሊፋው አቀረበ፡፡ ከሊፋውም ለፓትርያርኩ መልእክት ላከ፡፡
በቀጠሮው ቀን በወቅቱ የእስክንድርያ ፓትርያርክ የነበረው አብርሃም ሶርያዊ በሃይማኖት ዕውቀቱ እና ትምህርቱ የታወቀውን ሳዊሮስ ዘእስሙናይን ይዞት መጣ፡፡ ሳዊሮስ ዘእስሙናይ «በከሊፋው ፊት ይሁዲን መናገር መልካም አይደለም» አለው፡፡
ይህንን ቋንቋ ሙሴ በሌላ ተርጉሞ «አላዋቂ ብለህ ሰደብከኝ» ሲል ተቆጣ፡፡
ከሊፋ አል ሙኢዝም «መከራከር እንጂ መቆጣት አያስፈልግህም» አለው፡፡
ያን ጊዜ ሳዊሮስ «አላዋቂ ብዬ የተናገርኩህ እኔ ሳልሆን ያንተው ነቢይ ኢሳይያስ ነው» ብሎ በትንቢተ ኢሳይያስ 1÷3 ላይ ያለውን ጠቀሰ፡፡ ከሊፋው ገረመውና «እንዲህ የሚል የእናንተ ነቢይ አለ?» ሲል ሙሴን ጠየቀው፡፡ ሙሴም «አዎ አለ» አለው፡፡ አባ ሳዊሮስም «እንዲያውም እንስሳት ከአንተ እንደሚሻሉም ገልጧል» አለው፡፡ ይሄን ጊዜ ከሊፋው ሳቀ፡፡ ክርክሩም እንዲቆም አዘዘ፡፡
ይህ ሁኔታ ያዕቆብን አበሳጨው፡፡ ራሱ ባመጣው ጣጣ በከሊፋው ፊት መዋረዱም ቆጨው፡፡ ስለዚህም ክርስቲያኖቹን የሚያጠቃበት ሌላ መንገድ መፈለግ ጀመረ፡፡ ሙሴንም አንዳች ጥቅስ ከወንጌል እንዲፈልግ ነገረው፡፡

ሙሴ በመጨረሻ በማቴ 17÷20 ያለውን «የስናፍጭ ቅንጣት ታህል እምነት ቢኖራችሁ ይህንን ተራራ ከዚህ ተነሣ ብትሉት ይሆናል» የሚለውን አገኘ፡፡ ለያዕቆብም ነገረው፡፡ ያዕቆብም ወደ ከሊፋው በማምጣት «በክርስቲያኖች መጽሐፍ ላይ እንዲህ ስለሚል ይህንን ፓትርያርኩ ያሳየን» አለው፡፡ ከሊፋው ተገረመ፡፡ ፓትርያርኩንም ጠርቶ ጠየቀው፡፡ አብርሃም ሶርያዊ ይህ ቃል በእውነት እንዳለ ነገረው፡፡
ከሊፋውም «በእውነት የክርስቲያኖች ሃይማኖት እውነት ይሁን ውሸት ለመፈተኛ ይህ ጥሩ አጋጣሚ ነው፡፡ ይህንን ማድረግ ካቃታቸው ግን ሕዝቡን እያታለሉ ነውና መቀጣት አለባቸው» ብሎ አሰበ፡፡
ከሊፋ አል ሙኢዝ ለአባ አብርሃም አራት ምርጫ አቀረበለት

1. የሙካተምን ተራራ ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ ማዛወር ወይም
2. እስልምናን ተቀብሎ ክርስትናን መተው ወይም
3. ግብጽን ትቶ ወደ ሌላ ሀገር መሄድ ወይንም
4. በሰይፍ መጥፋት

ፓትርያርክ አብርሃም ውሳኔውን ለማሳወቅ የሦስት ቀን ጊዜ ጠየቀ፡፡ ከከሊፋው ዘንድ ከወጣ በኋላም ጳጳሳቱን፣ መነኮሳቱን፣ ካህናቱን፣ ዲያቆናቱን እና ምእመናኑን ሰበሰበ፡፡ ያጋጠመውንም ነገር ነግሮ በመላዋ ግብጽ የሦስት ቀን ጾም እና ጸሎት አወጀ፡፡

በሦስተኛው ቀን ማለዳ ቅድስት ድንግል ማርያም ለአባ አብርሃም ሶርያዊ ተገለጠችለት፡፡ «ይህንን ነገር የሚያደርግልህ አንድ ሰው አለ፡፡ ወደ ከተማው ገበያ ስትወጣ አንድ ዓይና የሆነ በገንቦ ውኃ የተሸከመ ሰው ታገኛለህ፡፡ እርሱ ይህንን ተአምር ያደርግልሃል» አለቺው፡፡
አባ አብርሃም ወዲያው ከመንበረ ጵጵስናው ወጥቶ ወደ ከተማው ገበያ መንገድ ጀመረ፡፡ በመካከሉም አንድ በገንቦ ውኃ የያዘ ሰው አገኘ፡፡ ያም ሰው አንድ ዓይና ነበረ፡፡ ጠራውና ወደ ግቢው አስገባው፡፡ የሆነውንም ነገረው፡፡
ያ ሰው «እኔ ኃጢአተኛ ነኝ፤ ይህ እንዴት ይቻለኛል» አለው፡፡
አባ አብርሃምም ያዘዘቺው ድንግል ማርያም መሆንዋን ነገረው፡፡
ያ ሰው ስምዖን ጫማ ሰፊው ይባላል፡፡ አንዲት ሴት እየደጋገመች መጥታ «ይህንን ዓይንህን እወድደዋለሁ» ብትለው ጫማ በሚደፋበት ጉጠት አውጥቶ የሰጣት እርሱ ነው፡፡

«አባቴ ሕዝቡን ወደ ተራራው ሰብስብ፡፡ እኔ ከአንተ አጠገብ እሆናለሁ፡፡ በአራቱም አቅጣጫ አንድ መቶ አንድ መቶ ጊዜ ኪርያላይሶን በሉ፡፡ ከዚያም ስገዱ፡፡ ከስግደቱ በኋላ ስታማትብ ተራራው ይነሣል » አለው፡፡
አባ አብርሃም ወደ ከሊፋው ሄዶ ተራራውን እንደሚያነሡት ነገረው፡፡

ኅዳር 15 ቀን 975 ዓም ሙስሊሞች፣ ክርስቲያኖች፣ አይሁድ፣ ሌሎችም ተሰበሰቡ፡፡ በአራቱም አቅጣጫ ጸሎተ ዕጣን ተደርሶ ኪርያላይሶን ተባለ፡፡ ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ ሰገዱ፡፡ ከስግደት ተነሥተው ጸጥ ሲሉ ኃይለኛ ድምፅ ተሰማና ተራራው ካለበት ተነሣ፤ ፈቀቅም አለ፡፡ እንደገና ሰገዱ፤ አሁንም ተነሥቶ ፈቀቅ አለ፡፡ ለሦስተኛ ጊዜ ሰገዱ ተነሥቶ ወደ ምሥራቅ ሄደ፡፡ በዚህ ጊዜ ከሊፋው በከፍተኛ ድምፅ ጮኸ፡፡ «በቃ፣ በቃ በዚህ ከቀጠለ ከተማዋ ትፈርሳለች» አለ፡፡ ክርስቲያኖቹ በደስታ አምላካቸውን አመሰገኑ፡፡ ከሳሾቻቸው አፈሩ፡፡ ስምዖን ጫማ ሰፊው ግን ጠፋ፡፡
አባ አብርሃም በብርቱ አስፈለገው፡፡ ከዚያ በኋላ ግን ሊያገኘው አልቻለም፡፡ አባ አብርሃም ሶርያዊ ይህንን የድንግል ማርያምን ተአምር ለማስታወስ ከነቢያት ጾም ጋር ተያይዞ እንዲጾም አዘዘ፡፡ በገና ጾም የመጀመርያዎቹ ሦስት ቀናት ይህንን ተአምር ለማስታወስ የምንጾማቸው ናቸው፡፡
ዛሬ ተራራው ከሦስት ቦታ ተከፍሎ ይታያል፡፡ ከምዕራብም ወደ ምሥራቅ ሸሽቷል፡፡ «ሙከተም» ማለትም «የተቆራረጠ» ማለት ነው ይባላል፡፡ ይህ ተራራ ዛሬ በአሮጌዋ ካይሮ ይገኛል፡፡

ከዚህ ተአምር በኋላ ከሊፋ አል ሙኢዝ ለቤተ ክርስቲያን ብዙ ነገር አድርጓል፡፡ አያሌ የፈረሱ አብያተ ክርስቲያናት ተጠግነዋል፡፡ አዳዲሶቹም ተሠርተዋል፡፡ ይህ ተአምር የግብጽ ፓትርያርኮች ታሪክ በተሰኘው ጥንታዊ መጽሐፍ እና በሌሎችም መዛግብት ተመዝግቧል:: በተአምረ ማርያም ላይ የምናገኘው ታሪክ ከእነዚህ ጥንታውያን መዛገብት የተገኘ ነው፡፡ በሌላም በኩል ተራራው እና በአሮጌዋ ካይሮ የመዓልቃ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ዙርያ የተደረጉ የአርኬዎሎጂ ቁፋሮዎችም ይህንን መስክረዋል፡፡
በኋላ ግን ቦታው ሆን ተብሎ የካይሮ የቆሻሻ መጣያ ተደረገ፡፡ ክርስቲያኖቹ ወደ አካባቢው የሚጣለውን ቆሻሻ በመጥረግ ታሪኩ እንዳይጠፋ ታገሉ፡፡ በመጨረሻም ነገር ሁሉ ለበጎ ነውና ቆሻሻዎቹን እንደገና ለአገልግሎት በማዋል /ሪሳይክሊንግ/ መጠቀም ጀመሩ፡፡ ዛሬ ለብዙዎች የሥራ እድል ከፍቶላቸዋል፡፡

የአል ሙከተም ተራራ ተፈልፍሎ የስምዖን ጫማ ሰፊው ቤተ ክርስቲያን ተሠርቷል፡፡ የቤተ ክርስቲያኑ መቅደስ ክፍት ነው፡፡ ወንበሩ 25000 ምእመናን ይይዛል፡፡ የስምዖን ዐጽምም በመዓልቃ ቤተ ክርስቲያን በተደረገው ቁፋሮ ተገኝቶ በዚሁ የተራራ ቤተ ክርስቲያን በክብር አርፏል፡፡
----------------------------------------
ዲ.ን ዳንኤል ክብረት

ቅዱስ ስምኦን (ጫማ ሰፊው) - ክፍል 1 / Saint Simon - Part 1

Поделиться в:

Доступные форматы для скачивания:

Скачать видео mp4

  • Информация по загрузке:

Скачать аудио mp3

Похожие видео

ቅዱስ ስምኦን (ጫማ ሰፊው) - ክፍል 2 / Saint Simon - Part 2

ቅዱስ ስምኦን (ጫማ ሰፊው) - ክፍል 2 / Saint Simon - Part 2

ቅድስት እንባ መሪና  part-1 / Kidest Emba Merina  - Ye Kidusan Tarik

ቅድስት እንባ መሪና part-1 / Kidest Emba Merina - Ye Kidusan Tarik

ቅዱስ ሙሴ ፀሊም መንፈሳዊ ፊልም || saint moses black spritual full orthodox movie

ቅዱስ ሙሴ ፀሊም መንፈሳዊ ፊልም || saint moses black spritual full orthodox movie

135ኛ የህይወት ገጠመኝ፦ከገጠር የመጡ ወላጆችና የጠፉ ልጆቻቸው በአዲስ አበባ መንገድ ላይ

135ኛ የህይወት ገጠመኝ፦ከገጠር የመጡ ወላጆችና የጠፉ ልጆቻቸው በአዲስ አበባ መንገድ ላይ

የግብፃዊቷ ቅድስት ማርያምና የአባ ዞሲማ ታሪክ  / St Mary The Egyptian & Aba Zosima - ሙሉ ታሪክ

የግብፃዊቷ ቅድስት ማርያምና የአባ ዞሲማ ታሪክ / St Mary The Egyptian & Aba Zosima - ሙሉ ታሪክ

ራሄል ማን ናት ? - የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ - መባዕ ቲቪ @Meba_tv

ራሄል ማን ናት ? - የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ - መባዕ ቲቪ @Meba_tv

Ethiopia:- የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ መዝሙሮች  ስብስብ || Kidus Georgis Mezmur || Saint George

Ethiopia:- የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ መዝሙሮች ስብስብ || Kidus Georgis Mezmur || Saint George

Мэл Гибсон говорит впервые: «До сих пор никто не может это объяснить»

Мэл Гибсон говорит впервые: «До сих пор никто не может это объяснить»

Jesus Christ Film in Tigrigna Language  ናይ የሱስ ፊልም ብትዓርኛ

Jesus Christ Film in Tigrigna Language ናይ የሱስ ፊልም ብትዓርኛ

ሶምሶን ክፍል 1 || ሺህውን በአህያ መንጋጋ || somson full story

ሶምሶን ክፍል 1 || ሺህውን በአህያ መንጋጋ || somson full story

ይስሀቅ እና ርብቃ - የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች 7 -  መንፈሳዊ ፊልም በአማርኛ - @meba-tv - Eotc tv - ስንክሳር

ይስሀቅ እና ርብቃ - የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች 7 - መንፈሳዊ ፊልም በአማርኛ - @meba-tv - Eotc tv - ስንክሳር

አባ መቃርስ - ክፍል - 1 / Aba Mekars   Part - 1  Ye Kidusan Tarik

አባ መቃርስ - ክፍል - 1 / Aba Mekars Part - 1 Ye Kidusan Tarik

በእግዚአብሔር ፊት የሚያስከብሩን 3 ነገሮች || ርእሰ ሊቃውንት የኔታ አባ ገብረኪዳን ግርማ || Aba Gebrekidan New Sibket  ||

በእግዚአብሔር ፊት የሚያስከብሩን 3 ነገሮች || ርእሰ ሊቃውንት የኔታ አባ ገብረኪዳን ግርማ || Aba Gebrekidan New Sibket ||

በአስገራሚ እና አስደናቂ ክስተቶች የተሞላው የታላቁ ነብይ ኤልያስ ሙሉ ታሪክ!!!//story of Elijah

በአስገራሚ እና አስደናቂ ክስተቶች የተሞላው የታላቁ ነብይ ኤልያስ ሙሉ ታሪክ!!!//story of Elijah

ፍካሬ ኢየሱስ - Fkare Eyesus ||| Ethiopian Orthodox Tewahido Amharic Sermon

ፍካሬ ኢየሱስ - Fkare Eyesus ||| Ethiopian Orthodox Tewahido Amharic Sermon

የእማሆይ ኄራኒ አስደናቂ ህይወት ክፍል አንድ  #tesfa_eyerusalem  #ቅድስት_ኄራኒ #መንፈሳዊ_ፊልም  #ፊልም

የእማሆይ ኄራኒ አስደናቂ ህይወት ክፍል አንድ #tesfa_eyerusalem #ቅድስት_ኄራኒ #መንፈሳዊ_ፊልም #ፊልም

CATH፣አንቀፀ ጥበብ |መንፈሳዊ ፊልም |ቅዱስ  ኣባ ኖፌር ባሕታዊ| Orthodox Film | St.Abba Nofer | 1ይ ክፋል | 2024 ዓ.ም.ፈ

CATH፣አንቀፀ ጥበብ |መንፈሳዊ ፊልም |ቅዱስ ኣባ ኖፌር ባሕታዊ| Orthodox Film | St.Abba Nofer | 1ይ ክፋል | 2024 ዓ.ም.ፈ

🔴ሕሊናችሁ ጋር ታረቁ||እጅግ ግሩም ትምህርት||በርእሰ ሊቃውንት አባ ገ/ኪዳን ግርማ||abagebrekidansibket||@meazakidusan

🔴ሕሊናችሁ ጋር ታረቁ||እጅግ ግሩም ትምህርት||በርእሰ ሊቃውንት አባ ገ/ኪዳን ግርማ||abagebrekidansibket||@meazakidusan

ቅዱስ አባ ጳውሊ ወ አባ እንጦንስ | Antony the Great and St Paul the first Hermit

ቅዱስ አባ ጳውሊ ወ አባ እንጦንስ | Antony the Great and St Paul the first Hermit

ያዕቆብ እና ኤሳው  - የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች 9 -  መንፈሳዊ ፊልም በአማርኛ - @meba-tv - Eotc tv - ስንክሳር

ያዕቆብ እና ኤሳው - የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች 9 - መንፈሳዊ ፊልም በአማርኛ - @meba-tv - Eotc tv - ስንክሳር

© 2025 dtub. Все права защищены.

  • Контакты
  • О нас
  • Политика конфиденциальности

Контакты для правообладателей: [email protected]