Track 19 Yemiyamir Kal | የሚያምር ቃል | Aster Abebe Vol 2
Автор: Aster Abebe Official
Загружено: 5 окт. 2024 г.
Просмотров: 734 787 просмотров
Experience the beautiful track "Yemiyamir Kal" by Aster Abebe in this video from her Vol 2 album. Listen and enjoy the soulful melodies and powerful Message.
#asterabebe
#Asterabebenewmezmure
#Yemiyamirkal
#mezmure
Executive Producer
Sofi Girma
Music Production
Heaven's Touch Studios
Music Arrangement
Illasha Fekadu
Bass
Amanuel Wolde
Guitar
Bereket Demeke
Mixing and Mastering
Robel Dagne
Lyrics
ሚዛኑ ተዛብቷል ብዬ ላልኩት ጉዳይ
አንተም ቸል ያልከኝ መስሎኝ የማልታይ
ማጉረምረም ልጀምር ለምንን ላበዛ
ላትጽናና ነፍሴ ለሊቱን በሙሉ እጆቼን ሳነሳ
ላፍታ አንተን አሰብኩ ልቤን ደስደስ አለው
ለቃልህ እንዲተጉ አይኖቼን ያዝካቸው
ለሊት ነው ግን ከልቤ ጋራ ተጨዋወትኩኝ
ነፍሴን በቃልህ አነቃቅተሃት ቆምኩኝ በረታሁኝ
ላፍታ አንተን አሰብኩ ልቤን ደስደስ አለው
ለቃልህ እንዲተጉ አይኖቼን ያዝካቸው
ለሊት ነው ግን ከልቤ ጋራ ተጨዋወትኩኝ
ነፍሴን በቃልህ አነቃቅተሃት ቆምኩኝ በረታሁኝ
የተናገርከው ቃል አላለፈም
ባህሪህ የሁሌ ነው አትጥልም
አቅምን አገኘሁ ቃልክን ሳጠነጥን
ስራህን ስጫወት ስናገር ምግባርህን
ሰው መታመን ሳይችል ከስፍራው ቢታጣ
አትልም የዛሬ አመት ላትደርስ ላትመጣ
እምነቴ ተረድቶ በአንተ አቅም አግኝቼ
ስንቴ ካልከኝ ደረስኩ እጆቼን ተይዤ
እምነቴ ተረድቶ በአንተ አቅም አግኝቼ
ስንቴ ካልከኝ ደረስኩ እጆቼን ተይዤ
1. ጆሮዬ ሰምቶ የነጻሁበት
የሳተ ጎዳናዬን ያቀናሁበት
የሚያምር ቃል ህይወት ማስዋቢያ
እንደመስታወት ጉድፍን ማያ
ነቅቼ ሰማሁ መልካም አገኘኝ
አዕምሮዬን አድሶ ቀናውን አሳየኝ
መልኩን መምሰያ አብ እንደሚወደው
ድፍረቴ አይደል የአፍህ ቃል ነው
የሚደንቅ ምክር (2)
ስንቴ አመለጥኩበት ከጠላት ሽብር
የሚደንቅ በረከት (2)
ስንቱን የመከራ ዘመን አለፍኩበት
የሚደንቅ ምክር (2)
ስንቴ አመለጥኩበት ከጠላት ሽብር
የሚደንቅ በረከት (2)
ስንቱን የመከራ ዘመን አለፍኩበት
2.ለነፍሴ እስትንፋስ ለአጥንቴ ጤና
የሚጣፍጥ ነገር እንደ ወለላ
ለቆዳዬ ወዝ ዘይት የሆነ
ድርቀቴን ገፎ እንዲህ ያስዋበ
እድሜ ማርዘሚያ ቀን መጥገቢያዬ
የነገዬ ሙላት መዳረሻዬ
አቋራጭ አይደል መስራቴ ለፍቶ
ቃልህ ይሞላዋል ቀድሞልኝ ወጥቶ
3. የቀኑን ክፋት ማሸንፍበት
ትናንት ዘርቼ ዛሬ የማጭድበት
መለምለሚያዬ እንደ ሰማይ ጠል
አቅም ማግኛዬ እንድጠነክር
የሚቆራርጥ በሁለቱም አፍ
የተሳለ ነው ልክ እንደ ሰይፍ
አጥንት ጅማቴን ዘልቆ የሚገባ
የሚለውጠኝ ነው ነገዬን ማስዋቢያ
የሚደንቅ ምክር (2)
ስንቴ አመለጥኩበት ከጠላት ሽብር
የሚደንቅ በረከት (2)
ስንቱን የመከራ ዘመን አለፍኩበት
የሚደንቅ ምክር (2)
ስንቴ አመለጥኩበት ከጠላት ሽብር
የሚደንቅ በረከት (2)
ስንቱን የመከራ ዘመን አለፍኩበት
/ hallelujah
https://open.spotify.com/album/68Nsi4...
Unauthorized distribution and reupload of this content is strictly prohibited
Copyright © Aster Abebe

Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: