የቅዱሳን አርእስት/
Автор: ሙራደ ቃል Murade Qal
Загружено: 2025-01-30
Просмотров: 848
የቅዱሳን አርእስት/ተክለሃይማኖት ፀሐይ
አኮቴት
አዲስ ለማ
የቅዱሳን አርእስት የዋሻው ብርሃን
የጸሎት ባለቤት የነዳያን መድኅን
ገና ስትወለድ አምላክ የመረጠህ
የድውያን ሕመም ፈዋሹ አንተነህ/2/
ተክለሃይማኖት ፀሐይ
ተክለሃይማኖት ፀሐይ የኢትዮጵያ ሲሳይ
ምዕራፈ ቅዱሳን /2/ በነፍስም በሥጋ አትርሳን።
ገና በሦስት ቀን በሕፃንነትህ
ጌታን አወደሰው ቅዱስ አንደበትህ
ቀድሞም እግዚአብሔር አስቦሃልና
በወጣትነትህ ወጣህ ለምነና/2/
አዝ------------
ሌትና ቀን ሳትመርጥ ክረምትና በጋ
ስትጸልይ ውለህ ስትጸልይ አነጋህ
በመቆምህ ብዛት አንድ እግርህ ሲነሣ
ጸሎትህን ፈጸምክ ለሥጋህ ሳትሣሣ/2/
አዝ----------
ምንኛ ድንቅ ነው ቅዱስ የአንተ ብርታት
7 ዓመት ሙሉ በአንድ እግርህ ጸሎት
የዓለም ግሣንግሷ ሀብቷ ሣይስብህ
ለኢትዮጵያ ጸለይክ ቆመህ በአንድ እግርህ/2/
አዝ ---------
የሃይማኖት ተክል የኢትዮጵያ አባት
ምሕረትን ከአምላክህ ላገርህ አሠጣት
እኛንም አግዘን ጽድቅን እንድንሠራ
በተሠጠህ ሥልጣን ጠብቀን አደራ/2/
#ethiopianmezmur #ethiopianorthodoxmezmur #ethiopianorthodoxtewahdo #teklehaymanot #tewahdomezmur #tewahdo_tewahido #tewahdo #ethiopianorthodoxchurch #ethiopianorthodoxtewahedochurch #ethiopianorthodoxtewahdochurch #ethiopianorthodoxmezmurplaylist #mezmur #mezmurorthodoxethiopia #mezmur_orthodox_ethiopian_ethiopian_orthodox_mezmur_ethiopian_drama_adey_drama #mezmure #mezmuretewahido #mezmurorthodoxethiopian #addisababa #addislemma
#addis lemma #addislema
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: