Alegn Yale (አለኝ ያለ) | Soreti Moges |
Автор: Soreti Moges
Загружено: 2021-09-16
Просмотров: 20726
ግርግሩ በዝቷል... በዝቷል በመንገዱ
ሁሉ ይሰለፋል እንደ አመጣጡ
ተራው የደረሰው ወቶ በተራው ይቆማል
ሀብት ንብረቱን ሁሉን ያስቆጥራል
እኔም በተራዬ በአደባባዪ ላይ
ቆምኩኝ በህዝብ ፊት ያለኝን ላሳይ
ከቶ ዝም አልልም ስሙኝ አወራለሁ
አለኝ ያለው ሁሉ ምንም እንደሌለው
የለውም አለኝ ያለ
ከኢየሱስ የጎደለ
ደሀ እርሱ ነው አለኝ ያለ
ከኢየሱስ የጎደለ
1.እያለው የሌለው ፍፁም የከሰረ
ጥሮ ግሮ ለፍቶ ባዶ እጁን የቀረ
አለምን አትርፎ ከህይወት የጎደለው
እንደምን ተጎዳ እርሱ ሰው ምስኪን ነው
የለውም አለኝ ያለ
ከኢየሱስ የጎደለ
ደሀ እርሱ ነው አለኝ ያለ
ከኢየሱስ የጎደለ
2.በንዋይ በገንዘብ ሰው እንዴት ይመካል
የህይወትስ ጌታ በምን እንቁ ይተካል
ሊሰማ ለሚወድ አንድ እውነት ይሄ ነው
ከክርስቶስ ውጪ ሙሉነት ባዶ ነው
የለውም አለኝ ያለ
ከኢየሱስ የጎደለ
ደሀ እርሱ ነው አለኝ ያለ
ከኢየሱስ የጎደለ
ሀብት ቢሆን ብልጥግና
ያለውና የሚመጣው ገና
ረብ የሌለው እንደ ጉድፍ ነው
ጌታን ከማወቅ አላስተያየው
የለውም አለኝ ያለ
ከኢየሱስ የጎደለ
ደሀ እርሱ ነው አለኝ ያለ
ከኢየሱስ የጎደለ
Do not Forget to subscribe to my channel
Connect with Soreti on socials below:
Instagram
/ soretimoges
Facebook
/ soreti313
YouTube
https://www.youtube.com/channel/UC4C2...
The album, #Kasenebetkegn, is available now everywhere:
songwhip
https://songwhip.com/soretimoges/kase...
Apple
/ album .
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: