Abba Dawit's song: Geta Yekirbelegn; የአባ ዳዊት ውብሸት መዝሙር፡ ጌታ አምላኬ ይቅር በለኝ
Автор: Abba Dawit Wubishet - አባ ዳዊት ውብሸት
Загружено: 2022-07-29
Просмотров: 2342
Abba Dawit's song: Geta Yekirbelegn;
የአባ ዳዊት ውብሸት መዝሙር፡ ጌታ አምላኬ ይቅር በለኝ
Lyrics, የመዝሙር ግጥም
የዳዊት ልጅ ማረኝ ምሕረት አውርድልኝ
በርጠሜዎስ የምባል ብርሃን የናፈቀኝ
ድምጼን አሰማሁ ማንም ሳያግደኝ
ና ብለህ ጠርተኸኝ ማየትን አስቻልከኝ
ጠቢባንን ብዬ ሀብቴንም ጨርሼ
እንዲያው ስንከራተት መልሼ መልሼ
ልብስህን ስነካ ሊሆን የሚበጀኝ
መዳኔ ታውቆኛል ኃይልህ ስላገዘኝ
መስማትና አንደበት ፍጹም የተሳነኝ
ዝግትግት ያሉብኝ ሁሉ ያልሆኑልኝ
ጣቶችህ ይዳስሱኝ ሕይወትን ይዝሩልኝ
ኤፋታህ በልና ሁሉን ክፈትልኝ
እንደ እሾህ የሚወጋ እረፍት የማይሰጠኝ
በሰዎች መካከል ሰላም የሚነፍገኝ
ከአንተ ሌላ ወዴት ለፈውስ እሮጣለሁ
ጸጋህ ይበቃኛል በአንተ እረካለሁ
ጣራው ተሸንቁሮ ወርጄ ከእግርህ ስር
አምኜ መጣሁኝ ኃጢአቴን ልትምር
ቃልህን ሰምቼ አልጋዬን ስሸከም
ልራመድ በቃሁኝ ሲያዩኝ በመገረም
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: