አዲስ መዝሙር || ሰላምከ ወረድኤትከ || በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰ/ት ት/ቤት
Автор: Genete tsige ገነተ ጽጌ
Загружено: 2023-07-29
Просмотров: 19326
አዲስ የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙር || ሰላምከ ወረድኤትከ || በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰ/ት ት/ቤት መዝሙር እና ኪነጥበብ ክፍል የተዘጋጀ ።
New ethiopian orthodox tewahdo mezmur by menagesha genetetsige stgeorge Sunday school mezmur and art department.
የመዝሙር ግጥም
ሰላምከ ወረድኤትከ በላዕሌነ ያዕርፉ
ጥዑመ ዜና /፮/ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ለስም አጠራርኽ ሰላም
ማኅቶት ዘዲበ ተቅዋም
የአእላፍ ሰማዕታት አለቃ
ፍጡነ ረድኤት ዋስ ጠበቃ
ጊዮርጊስ ንብለከ ነግሀ ወሠርከ
እምነ ልብነ ናፈቅረከ
ፈረስኽ ነው ጸዐዳ
ጊዮርጊስ ሰማዕት ዘልዳ
ፈጥነኽ 'ምትደርስ 'ምትራዳ
አማላጅነትኽ የተረዳ
ጊዮርጊስ ንብለከ ነግሀ ወሠርከ
እምነ ልብነ ናፈቅረከ
ቢያይል የሥቃይ ሞገዱ
ጸንተኻል ሳይበግርኽ አንዱ
የተሰጡኽ ሰባት አክሊላት
ጊዮርጊስ መክብበ ሰማዕት
ጊዮርጊስ ንብለከ ነግሀ ወሠርከ
እምነ ልብነ ናፈቅረከ
ገድልን ፈጽመኻል በድል
ጊዮርጊስ ኃያል መስተጋድል
ሰማዕተ ኢየሱስ ክርስቶስ
ገባሬ መንክራት ውዱስ
ጊዮርጊስ ንብለከ ነግሀ ወሠርከ
እምነ ልብነ ናፈቅረከ
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: