ሕማማት ቅዳሜ/ቀዳም ሥዑር/
Автор: 21Tube ሃያአንድ ቲዩብ
Загружено: 18 апр. 2025 г.
Просмотров: 645 просмотров
ቀዳም ሥዑር፤
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ ፲፫ቱን መከራ መስቀል ከተቀበለ በኋላ ሠርክ ፲፩ ሰዓት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከመልዕልተ መስቀል አውርደው በአዲስ በፍታ ገንዘው በአዲስ መቃብር ቀብረውታል። በዚህም በአካል ሥጋ ሙስና መቃብርን ለማጥፋት ወደ መቃብር፥በአካለ ነፍስ ደግሞ ነፍሳትን ለማውጣት ወደ ሲኦል ወርዷል።መለኮት ግን ከሥጋም ከነፍስም ጋር በተዋህዶ ነበረ።
ይህች ዕለት ከወትሮው በተለየ መልኩ ስለ መከራ መስቀሉ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች።በሥርዓተ ጾም ቅዳሜ አትጾምም ነበርና ነው።የጀመሩትም ቅዱሳን ሐዋርያት ናቸው።ምክንያቱም ጌታ በሦስተኛው ቀን እንደሚነሣ ነግሯቸው ስለ ነበረ ከስቅለት እስከ ትንሣኤ ጾመዋል።በዚህም በዓመት አንድ ጊዜ የጾም ቀን ተደርጋ ስለምትቆጠር “ሥዑር” እየተባለች ትጠራለች።
በዚህች ዕለት ሥርዓተ ማኅሌቱ ዕዝሉ እየተቃኘ፥ እየተመጠነ፥እየተዘመመ፥እየተመረገደ፥እየተጸፋ ያድራል፡፡ጧት ደግሞ አቡን፥መዋሥዕት፥ውዳሴ ማርያም ዜማ ተደርሶ “ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ፤ ” በሚለው ሰላም ይጠናቀቃል፡፡ከዚህም ጋር ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው ቃጭል ሲያቃጨሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቁ ምእመናን ትልቅ ብሥራት ነው፡፡
በዕለቱ የወይራ ቅጠልና ርጥብ ቄጠማ ይዞ ማመስገን አለ።ይህም በጥፋት ውኃ ጊዜ ኖህ የውኃውን መጉደል እንድታረጋግጥ የላካት ርግብ የወይራ ቅጠል በስንጥሯ ይዛ በመምጣት እንዳበሠረችው ሁሉ በጌታችን ሞትና ትንሣኤም የኃጢአት ማዕበል መቆሙን፥የኃጢአት ባሕር መጉደሉን ለማብሠር፥”አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን የኖረ የሰው ልጅ በደል ተደመሰሰ” ለማለት ነው።ቃለ ዓዋዲ (ቃጭል) እየመቱም “ገብረ ሰላመ በመስቀሉ፥ትንሣኤሁ አግሀደ፤በመስቀሉ ሰላም አደረገ፥ትንሣኤውንም ገለጠ፤” በሚል ኃይለ ቃል በያሬዳዊ ዜማ ይዘምራሉ።በተጨማሪም “ጌታ ተመረመረ፥ዲያብሎስ ታሰረ፤”ይላሉ።ምእመናንም ርጥቡን ቄጠማ ተቀብለው እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡ይኸውም የአክሊለ ሦክ መታሰቢያ ነው።ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከትም ይሰጣሉ።
በዚህች ዕለት እነ ማርያም መግደላዊትና ሌሎች ሴቶች የጌታን ውለታውን እያስታወሱ ሽቱ በመያዝ ወደ መቃብሩ ስፍራ እየተመላለሱ ማልቀሳቸውም ይታሰባል።በአይሁድ ሥርዓት የመቃብር ስፍራን ሽቶ መቀባት ባህል ነበርና።ሴቶቹ ለጊዜው አይሁድን ቢፈሩም በድብቅ አድርገውታል።
ጧት ላይ ዲያቆኑ ቃጭል እየመታ ከፊት ሲቀድም ሌላው መቋሚያ ይዞ መከተሉ ለእነዚህ ሴቶች ምሳሌነት አለው። ምክንያቱም ጠባቂዎቹ ወደ መቃብሩ ስፍራ አላስደርስ ብለው በበትር ሲያባርሯቸው እያለቀሱ ለመሮጣቸው ምሳሌ ነው።
የዕለቷን በረከት ያሳድርብን፤

Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: