እነማን ነበሩ? እነማን አለፉ? እነማን ተረፉ? ክፍል 2 የ 2011 የክተራና የጥምቀት በዓል አከባበር በጎንደር
Автор: SelamtaLondon
Загружено: 2023-10-21
Просмотров: 287
ከአራት ዓመታት በፊት እጅግ በደመቀ ሁኔታ በተከበረው የ 2011 ዓመተ ምሕረት የከተራና የጥምቀት በዓል ላይ የተካፈሉትን በዓል አክባሪዎች ስንመለከት ባልሳሳት ዘጠና በመቶው ታዳሚ ወጥቶች ነበሩ ለማለት እንደፍራለን። ከዚህም በላይ ብዙ የውጭ ሀገር ጎብኝዎች ያለምንም ሥጋት እየተንቀሳቀሱ መታሰቢያ ምስሎችን ሲቀርጹ፣ ከሕዝቡ ጋር ተቀላቅለው ሰምተውና ጓጉተው የመጡበትን ጉዳይ ሲፈጽሙ ይታዩ ነበር። ከዚያ ወዲህ በትግራይ፣ በአፋርና በአማራ ክልሎች ውስጥና ኦሮሚያን ጨምሮ ከሞላ ጎደል ባብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ የአስተዳደር ክፍሎች ውስጥ የውጭ ጠላት ሳይመመጣ ልጆቿ እርስ በራቸው ሲተላለቁ በየዕለቱ መስማትና ማየት እንደጀንበር መውጣትና መጥለቅ የተረጋገጠ ዕውነት እይመሰለ በመኼድ ላይ ይገኛል። ይህ መጠፋፋት ቀርቶ አበረን በሠላምና በዕኩልነት መኖርና ማደግ እንድንችል ተቀራቦ ከመነጋገር በስተቀርና፣ በሚመሳስሉብት ላይ አጠንክሮ በመሥራት ለማይግባቡበት ጉዳይ መፍትሔ በሠላማዊ መንገድ ከመፈለግ ይልቅ ሳንጃ መማዘዙ የትም እንደማያደርስ ምክንያታዊ ለኾን ሰው ግልጽ ነው። በዚህ አለመግባባት የተነሳ ሕይወታቸው ባጭር የተቀጩ ወጣቶች ቁጥር ስንት ይኽን? ቤቱ ይቁጠረው። እግዚአብሔር ሀገራችንን ያልተዛባ ፍርድ፣ እኩልነትና ሠላም የሠፈነባት ምድር ያድርግልን። ከስሕተታችን ተምረን ወደፊት በቀና መንገድ እንድንጓዝ ለመሪዎችቹም የተጣለባቸን ወይም ሀገርን የመምራት ኃላፊነት አለብን ብለው የሚያምኑትን ያህል ቃላቸውን እንዲያከብሩ ልቡና ይስጣቸው። ለሕዝቡም መብትና ግዲታውን ለመጠበቅና ለማስጠበቅ በጎጥና በጎሣ ሚዛን ሳይኾን፣ በችሉታ ላይ የመሠረተ ምርጫ እንዲያደርግና ጉድለት ሲያይ እንዲስተካከል መጠየቅና የማይኾን ሲኾን ደግሞ የተከለውን ወይም የተተከለበት ነቅሎ በሚስማማው መተካት እንዲችል ችሎታና ቀና መንፈስ እንዲኖረው ምኞቴ ነው። የታሪክ ፍርድ ጎሣና ጎጥ ወይም ሃይማኖትን መሠረት አያደርግምና ማንኛችንም ብንኾን ከታሪክ ፍርድ ስለማናመልጥ ከመቃብር በላይ የሚውል መልካም ሥራ እንጂ የሚያዋርድ ሥራ ሠርተን አንለፍ።
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: