Dess - ደስ - Tesfa Ale - ተስፋ አለ ft Kidus Eliyas - ቅዱስ ኤሊያስ (Reggae Remix) Ethiopian Music 2025
Автор: Dess ደስ
Загружено: 2025-06-19
Просмотров: 26317
#newmusic #ethiopianmusic #rap
ደስ + ቅዱስ ኤልያስ - ተስፋ አለ
ነጋ ጠባ እሩጫ ወዲህ ወዲያ መበካከን
እረፍት አያልቅ ልቤ አያልቅለት ሁሉ ጅምር
አለም ተጭኖብኝ ከጀርባዬ አትላስ ሆኜ
ሁሉ እንዳማረበት ፈገግ ይላል ጥርሴ ሆዬ
ደስተኛ ነው ምን ጎደለበት
ይለኛል ያየ እሱ ምን አለበት
በአለም ግርፋት እየደማ ቆስሎ ጎኔ
ይደብቅልኛል መጋረጃው ፈገግታዬ
ጥርሴን አትመኑት ፈገግታዬ ውሸታም ነው
ስንቱን እንዳዘለ ብኩን ልቤ ነው የሚያውቀው
መከዳት መገፋት እንዲሁ መዳከሩን
የአለምን ክፋት ማን አውቆት ህመሙን
እየበገነ ውስጤ እያለቀ
ጥርሴ ላመሉ እንዲሁ እየሳቀ
ደስ ደስ አለው ዙርያዬ ይለኛል
የምሆነውን ማን ያይልኛል
ጎንህ ለአንተ የሚገደው ብዙ አለ አንተን ያለ
ሸክምህ አይበልጥም ከላይ ከፈጠረህ
አዋ ተስፋ አለ
ስንቱ አመለጠ ላይ ላዩን እየሳቀ
ውስጡን ይዞ አምቆ በዝምታ እያለቀ
ከአለም ተደብቆ ለብቻው እየደማ
በሳቅ ተሸፍኖ ስንቱ እራሱን ተቀማ
በሚጣደፍ አለም በማይሞላ ብኩን ክፉ ኑሮ
እያፎካከረ የእሱን ከእዚያ እንደው አወዳድሮ
ከተስፋው ተጣልቶ ነገን ከእሩቅ ፈርቶ እየኖረ
ስንቱ ሄደ ሸሸ ትንሽ ሳይዘልቅ ወድቆ እንደጀመረ
ህመሙን የደበቀ መች መድሀኒት አግኝቶ
መቆዘም መድበን እንጂ እራስ ከእራስ ተጣልቶ
በቃ ከእንግዲህ ሀዘኔን በሳቅ አልደብቅም
ብቻዬን ሆኜ በሀሳብ ተይዤ አልማቅቅም
ከእንግዲህ ሳቄ እየዋሸ
ህመሙን ላይድን እያሸ
ከሰው ፊት ደስታ አቀብሎ
አያለቅስ ደበቅ ብሎ
ጎንህ ለአንተ የሚገደው ብዙ አለ አንተን ያለ
ሸክምህ አይበልጥም ከላይ ከፈጠረህ
አዋ ተስፋ አለ
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: