ሙሐመድ ነቢና ﷺ | ምርኩዝ 31 | "የከውኑ ሞገስ 7" | የኅብረት ነሺዳ | New Ethiopian Nesheed
Автор: Minber TV
Загружено: 2025-08-26
Просмотров: 967307
የከውኑ ሞገስ 7 የኅብረት ነሺዳ
****
አዝማች 1
ሙሐመድ ነቢና
ፍቅር ነሁ ሰኪና
ሙሐመድ ነቢና
የጀነት ጎዳና
ከመካ ኑሩ ፈንጥቆ
ዓለምን ኳለው አድምቆ
ከመካ ብርሃኑ ዘልቆ
ምድር ላይ ታየ አሸብርቆ፡፡
ዘማች 1
ፉኣድ መልካ
በምድር ቋንቋ ባለም ልሳን
ሰው አለኝ ባለው የፍቃር ቃል፣
ብጀምር እንጂ ሃቢቢዋ
አንቱን ባወድስ መች ይበቃል፣
ሐሩን ከድር
በኸልቁ ቁጥር ዳር እስከ ዳር
ሲመሽ ሲነጋ ቀንም ማታ፣
ይውረድ ሰለዋት ይስፈን ሰላም
ኣንዳች ሳይጎድል ሳይቆም ላፍታ፡፡
አስማማው አህመድ
በሳር ቅጠሉ በአዝመራው፣
ባፈራው ፍሬ በዘለላው፣
በፍጥረቱ ልክ በዓደዱ፣
ይስፈን ራህመቱ ነቢ ውዱ።
አብዱረሂም ከማል
በጠብታው ልክ በሚዘንበው፣
ከውቅያኖሱም በሚተነው፣
ባሸዋው መጠን ከበረሃ፣
ይውረድ ሶለዋት በኛ ጧሃ።
አቡበክር ኢብራሂም
ህያው በሆነ በሩህ ታስሮ፣
ቀድሞን በሄደ በምድር ኖሮ፣
በሚራመደው እስከ ቂያም፣
በቁጥሩ ያህል ላንቱ ሰላም።
****
ሙሐመድ ነቢና
ፍቅር ነሁ ሰኪና
ሙሐመድ ነቢና
የጀነት ጎዳና
ከመካ ኑሩ ፈንጥቆ
ዓለምን ኳለው አድምቆ
ከመካ ብርሃኑ ዘልቆ
ምድር ላይ ታየ አሸብርቆ፡፡
አስማማው አህመድ
በቀለሙ አይነት ባዋፋቱ፣
በንጋት ዜማው በቅኝቱ፣
በቁጥሩ መጠን ሰለዋቱ፣
ይውረድ ቀን ከሌት ይስፈን ባንቱ።
ሐሩን ከድር
ከጥልቁ ባህር በሚዋኘው፣
ልኩ መጠኑ ሩቅ በሆነው፣
በሚሳበውም በደረቱ፣
በእጥፍ ይውረድ ሰላም ባንቱ።
ፉኣድ መልካ
ሸክሙ የበዛበት አቅም ያጣ፣
ምህረት ፍለጋ ቆርጦ የወጣ፣
ባነባው መጠን ጠዋት ማታ፣
ይስፈን ሰለዋት በኛ ዓይነታ።
አብዱረሂም ከማል
በዘመን ቁጥር በሰው መልክ፣
ይውረድ ራህመቱ ያለ ልክ፣
ከመላእክቱ ቁጥር ልቆ፣
ይስፈን ራህመቱ ባንቱ ደምቆ።
አቡበከር ኢብራሂም
በኡሁድ ግዝፈት በተራራው፣
በጠጠሩ ልክ በአቧራው፣
ለአማላጄ ለቂያም ቀን፣
ይውረድ ራህመቱ ያለ መጠን።
የኅብረት መሸጋገሪያ
ሰለዋቱላህ ወሰላሙሁ
ዓለይከ ሃዲ ያ ሙከረሙ
ሰለዋቱላህ ወሰላሙሁ
ዓለይከ ሃዲ ያ ሙከረሙ
ሰለዋቱላህ ወሰላሙሁ
ዓለይከ ሃዲ ያ ሙከረሙ
ሰለዋቱላህ ወሰላሙሁ
ዓለይከ ሃዲ ያ ሙከረሙ
****
ፉኣድ መልካ (እንጉርጉሮ)
ሃዘን መከራው ሲያስጨንቀኝ
ዱንያ ስትጨልም ሰውም ሲርቀኝ
ሃሌን ማደሻ ለኔ እንደገና
ሰለዋት እንጂ ምን አለኝና።
ስንኩል ህይወቴን መጠገኛ
ካዘን ጭንቀቴ ፈውስ ማግኛ
ተስፋ ማደርገው ምን አለኝ
ሰለዋት እንጂ ሚያፅናናኝ
ሐሩን ከድር
የህልሜ ጣዕም ሽልማቴ፣
የሌት አጫዋች ነሁ ድምቀቴ፣
አቡበከር ኢብራሂም
አይኔን ከድኜ ‘ምጠብቀው፣
ቀን በሰለዋት ስደምቅ ነው።
አስማማው
የረሳሁትን ማስታወሻ
ህመም ስቃዬን ፍፁም መርሻ
አብዱረሂም
ስምዎን አንስቼስ አልሰስትም
ሰላም ባንቱ ላይ መቼም የትም
የኅብረት መሸጋገሪያ
ሰለዋቱላህ ወሰላሙሁ
ዓለይከ ሃዲ ያ ሙከረሙ
ሰለዋቱላህ ወሰላሙሁ
ዓለይከ ሃዲ ያ ሙከረሙ
ሰለዋቱላህ ወሰላሙሁ
ዓለይከ ሃዲ ያ ሙከረሙ
ሰለዋቱላህ ወሰላሙሁ
ዓለይከ ሃዲ ያ ሙከረሙ
Copyright @MinberTV
👨👩👧👦 Join Minber Family 🔗 https://t.me/Minber_Merkuz_Discuss
★★★★★
የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ሊንኮች👇🏽 ይወዳጁን 👍🏽 ያጋሩ ⤴️
📍YouTube 👉 / @minbertv1
📍Facebook👉 / minbertv1
📍Telegram👉 https://t.me/minbertv
📍TikTok 👉 / minber_tv
📍Instagram 👉 / minbertv
📍X / Twitter 👉 / minbertv
📍Website 👉 https://www.minbertv.com
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: